Here you can explore some general information about the project. See also Beta maṣāḥəft institutional web page. Select About to meet the project team and our partners. Visit the Guidelines section to learn about our encoding principles. The section Data contains the Linked Open Data information, and API the Application Programming Interface documentation for those who want to exchange data with the Beta maṣāḥǝft project. The Permalinks section documents the versioning and referencing earlier versions of each record.
Click to get back to the home page. Here you can find out more about the project team, the cooperating projects, and the contact information. You can also visit our institutional page. Find out more about our Encoding Guidelines. In this section our Linked Open Data principles are explained. Developers can find our Application Programming Interface documentation here. The page documents the use of permalinks by the project.
Descriptions of (predominantly) Christian manuscripts from Ethiopia and Eritrea are the core of the Beta maṣāḥǝft project. We (1) gradually encode descriptions from printed catalogues, beginning from the historical ones, (2) incorporate digital descriptions produced by other projects, adjusting them wherever possible, and (3) produce descriptions of previously unknown and/or uncatalogued manuscripts. The encoding follows the TEI XML standards (check our guidelines).
We identify each unit of content in every manuscript. We consider any text with an independent circulation a work, with its own identification number within the Clavis Aethiopica (CAe). Parts of texts (e.g. chapters) without independent circulation (univocally identifiable by IDs assigned within the records) or recurrent motifs as well as documentary additional texts (identified as Narrative Units) are not part of the CAe. You can also check the list of different types of text titles or various Indexes available from the top menu.
The clavis is a repertory of all known works relevant for the Ethiopian and Eritrean tradition; the work being defined as any text with an independent circulation. Each work (as well as known recensions where applicable) receives a unique identifier in the Clavis Aethiopica (CAe). In the filter search offered here one can search for a work by its title, a keyword, a short quotation, but also directly by its CAe identifier - or, wherever known and provided, identifier used by other claves, including Bibliotheca Hagiographica Graeca (BHG), Clavis Patrum Graecorum (CPG), Clavis Coptica (CC), Clavis Apocryphorum Veteris Testamenti (CAVT), Clavis Apocryphorum Novi Testamenti (CANT), etc. The project additionally identifies Narrative Units to refer to text types, where no clavis identification is possible or necessary. Recurring motifs or also frequently documentary additiones are assigned a Narrative Unit ID, or thematically clearly demarkated passages from various recensions of a larger work. This list view shows the documentary collections encoded by the project Ethiopian Manuscript Archives (EMA) and its successor EthioChrisProcess - Christianization and religious interactions in Ethiopia (6th-13th century) : comparative approaches with Nubia and Egypt, which aim to edit the corpus of administrative acts of the Christian kingdom of Ethiopia, for medieval and modern periods. See also the list of documents contained in the additiones in the manuscripts described by the Beta maṣāḥǝft project . Works of interest to Ethiopian and Eritrean studies.
While encoding manuscripts, the project Beta maṣāḥǝft aims at creating an exhaustive repertory of art themes and techniques present in Ethiopian and Eritrean Christian tradition. See our encoding guidelines for details. Two types of searches for aspects of manuscript decoration are possible, the decorations filtered search and the general keyword search.
The filtered search for decorations, originally designed with Jacopo Gnisci, looks at decorations and their features only. The filters on the left are relative only to the selected features, reading the legends will help you to figure out what you can filter. For example you can search for all encoded decorations of a specific art theme, or search the encoded legends. If the decorations are present, but not encoded, you will not get them in the results. If an image is available, you will also find a thumbnail linking to the image viewer. [NB: The Index of Decorations currently often times out, we are sorry for the inconvenience.] You can search for particular motifs or aspects, including style, also through the keyword search. Just click on "Art keywords" and "Art themes" on the left to browse through the options. This is a short cut to a search for all those manuscripts which have miniatures of which we have images.
We create metadata for all places associated with the manuscript production and circulation as well as those mentioned in the texts used by the project. The encoding of places in Beta maṣāḥǝft will thus result in a Gazetteer of the Ethiopian tradition. We follow the principles established by Pleiades and lined out in the Syriaca.org TEI Manual and Schema for Historical Geography which allow us to distinguish between places, locations, and names of places. See also Help page fore more guidance.
This tab offers a filtrable list of all available places. Geographical references of the type "land inhabited by people XXX" is encoded with the reference to the corresponding Ethnic unit (see below); ethnonyms, even those used in geographical contexts, do not appear in this list. Repositories are those locations where manuscripts encoded by the project are or used to be preserved. While they are encoded in the same way as all places are, the view offered is different, showing a list of manuscripts associated with the repository.
We create metadata for all persons (and groups of persons) associated with the manuscript production and circulation (rulers, religious authorities, scribes, donors, and commissioners) as well as those mentioned in the texts used by the project. The result will be a comprehensive Prosopography of the Ethiopian and Eritrean tradition. See also Help page for more guidance.
We encode persons according to our Encoding Guidelines. The initial list was inherited from the Encyclopaedia Aethiopica, and there are still many inconsistencies that we are trying to gradually fix. We consider ethnonyms as a subcategory of personal names, even when many are often used in literary works in the context of the "land inhabited by **". The present list of records has been mostly inherited from the Encyclopaedia Aethiopica, and there are still many inconsistencies that we are trying to gradually fix.
This section collects some additional resources offered by the project. Select Bibliography to explore the references cited in the project records. The Indexes list different types of project records (persons, places, titles, keywords, etc). Visit Projects for information on partners that have input data directly in the Beta maṣāḥǝft database. Special ways of exploring the data are offered under Visualizations. Two applications were developed in cooperation with the project TraCES, the Gǝʿǝz Morphological Parser and the Online Lexicon Linguae Aethiopicae.
Help

You are looking at work in progress version of this website. For questions contact the dev team.

Hover on words to see search options.

Double-click to see morphological parsing.

Click on left pointing hands and arrows to load related items and click once more to view the result in a popup.

Do you want to notify us of an error, please do so by writing an issue in our GitHub repository (click the envelope for a precomiled one).
On small screens, will show a navigation bar on the leftOpen Item Navigation
Edit Not sure how to do this? Have a look at the Beta maṣāḥǝft Guidelines!
Hide pointersClick here to hide or show again the little arrows and small left pointing hands in this page.
Hide relatedClick here to hide or show again the right side of the content area, where related items and keywords are shown.
EntryMain Entry
TEI/XMLDownload an enriched TEI file with explicit URIs bibliography from Zotero API.
SyntaxeSee graphs of the information available. If the manuscript contains relevant information, then you will see visualizations based on La Syntaxe du Codex, by Andrist, Canart and Maniaci.
RelationsFurther visualization of relational information
TranscriptionTranscription (as available). Do you have a transcription you want to contribute? Contact us or click on EDIT and submit your contribution.

Saint Petersburg, Institut Vostočnyh Rukopisej Rossijskoj Akademii Nauk, IV Ef. 27

Daria Elagina

This manuscript description is based on the catalogues listed in the catalogue bibliography

Work in Progress
https://betamasaheft.eu/IVEf27
Institut Vostočnyh Rukopisej Rossijskoj Akademii Nauk[view repository]

Collection:

Other identifiers: Platonov cat. II.7

  • Citation URI: https://betamasaheft.eu/IVEf27
  • Collection API: https://betamasaheft.eu/api/dts/collections?id=https://betamasaheft.eu/IVEf27
  • Navigation API: https://betamasaheft.eu/api/dts/navigation?id=https://betamasaheft.eu/IVEf27
  • Document API: https://betamasaheft.eu/api/dts/document?id=https://betamasaheft.eu/IVEf27

Alignment Start a translation alignment with Alpheios Alignment. You can also add morphological annotations there. See instructions in GitHub.
Versions See parallel versions if any is available
Quotations Check for marked up quotations of a passage in this section
back to top
እኔ፡ እግዚአብሔር፡ በጽድቅ፡ ጸሩኁህ፡ እጅኽንም፡ ያዝሁኽ፡ ጠበቅሁኽም፡ ለሕዝብም፡ ኪዳን፡ አደረግሁኽ፡ ለአሕዛብም፡ ብርሃን። የዕውርን፡ ዓይን፡ ትከፍት፡ ዘንድ፡ የተጋዘውንም፡ ትከፍት፡ ዘንድ፡ የተጋዘውንም፡ ከግዞት፡ ታወጣ፡ ዘንድ፡ ከግዞት፡ ቤት፡ ጨለማ፡ የተቀመጡት። ፩ ፩ እንዳለ፡ ሰውን፡ እጅግ፡ ደስ፡ የምታሰኘው፡ ብርሃንን፡ ማየት፡ ከሥራትም፡ መፈታት፡ ናት። እንዲሁም፡ ደግሞ፡ ተሁሉ፡ ነገር፡ የበለጠች፡ እውነት፡ ናት። ጨለማም፡ በብርሃን፡ ፊት፡ መቆም፡ እንዳይችል፡ አሰትም፡ በእውነት፡ ፊት፡ መቆም፡ አይቻላትም። ወውእቱሰ፡ ቀታሌ፡ ነፍሰ፡ ሰብእ፡ ውእቱ፡ እምትካቱ፡ ወኢይቀውም፡ በጽድቅ፡ እስመ፡ አልቦ፡ ጽድቅ፡ በኀቤሁ። ወሶበሂ፡ ይነብብ፡ ሐ | ሰተ፡ እምዚአሁ፡ ይነብብ፤ እስመ፡ ሐሳዊ፡ ውእቱ፡ ወአቡሃ፡ ለሐሰት። ፩ እንዳለ፡ አሰት፡ ጨለማ፡ ከሰይጣን፡ ወጣች። ሰውም፡ እግዜር፡ የሰጠውን፡ ቅንየቀ ና፡ ጽድቅ፺፡ ብርሃንን፡ ትቶ፡ ወደርሱ፡ ስለ፡ ተጠጋ፡ ባሰት፡ ተሸፈነ። የጸጋውም፡ ብርሃን፡ ተገፎ፡ የውርደትና፡ የድንቍርናን፡ ምልክት፡ የምትሆንን፡ ቈርበት፡ ለበሰ። ፪ እውነት፡ ብርሃንንም፡ ስለ፡ ተወ፡ ወደ፡ ረጅም፡ አሰተኛ፡ አምልኮ፡ የጨለማ፡ ገደል፡ ወደቀ። ነገር፡ ግን፡ መሐሪ፡ እግዚአብሔር፡ በመልኩና፡ በምሳሌው፡ የፈጠረውን፡ ሰው፡ ሊረሳ፡ አልተቻለውም። ቀድሞ፡ እርሱን፡ ደስ፡ ለማሰኘት፡ በቀላይ፡ ፊት፡ የነበረን፡ ጨለማ፡ ሊያርቅ፡ ብርሃን፡ ይሁን፡ ፫ ብሎ፡ እንደ፡ ፈጠረለት፤ ኋላም፡ ወ | ደ፡ ብርቱ፡ የክህደት፡ ጨለማ፡ ገደል፡ ወድቆ፡ መውጣት፡ ተስኖት፡ ሲጨነቅ፡ ቢያየው፡ ፈጣሪው፡ ራራለት። ጨለማውን፡ ካራቀች፡ ከፊተኛይቱ፡ ብርሃን፡ የበለጠችን፡ የክብሩን፡ ፀዳል፡ ጮራ፡ ሰደደለት፡ ፩ በፊት፡ ስለ፡ ወደደው፡ በመልኩና፡ በምሳሌው፡ ፈጠረው። ነገር፡ ግን፡ ነውረኛ፡ ሰው፡ ይህነን፡ መልክ፡ ስላበላሽ፡ መሐሪ፡ እግዚአብሔር፡ እርሱን፡ እንዲያድስ፤ ከፊተኛውም፡ የበለጠን፡ ሽልማት፡ ሊሰጠው፤ በጸጋው፡ ሊያበራለት፡ ሰው፡ ሆኖ፡ በባርያ፡ መልክ፡ ታይቶ፡ እንዲመራው፡ አንዱን፡ ልጁን፡ ሰደደለት። በጣይ ሃን፡ ፡ ጨለማን፡ የምታርቅ፡ ብርሃን፤ ብርድንም፡ የምታጠፋ፡ ሙቀት፡ እንዳሉ፡ እናውቃለን። የየመይታይ፡ እግዜር፡ አብ፡ የክብሩ፡ ጮራ፡ | ጌታችን፡ የሱስ፡ ክርስቶስም፡ ዘርእየ፡ ኪያየ፡ ርእዮ፡ ለአብ፡ ፩ እንዳለ፤ ለማይታዩ፡ ሁለት፡ አካላት፤ እርሳቸው፡ ሁሉን፡ የሚቺል፡ የብርሃን፡ ምንጭ፡ አብ፤ በኃጢአት፡ ብርድም፡ ለደነዘዘች፡ ነፍስ፡ የሚያሞቅ፡ ሙታም፡ የነበረችውን፡ ቅጽበት፡ የሚያድን፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ ናቼው፤ ባንዲት፡ የመለኮት፡ ባሕርይ፡ ሶስት፡ አካላት፡ እንዳሉ፡ ገለጠ። ይህነንም፡ እንድናውቅ፡ ሐዋርያቶቹን፡ ሒዱ፡ ዓለምን፡ ሁሉ፡ አስተምሩ። ወእንበስመ፡ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ እያላችኍም፡ አጥምቁዋቸው፡ አለ። ፪ በወንጌል፡ ዮሐንስም፡ አብ፡ እንደ፡ ላከኝ፡ እኔም፡ እንዲሁ፡ እናንተን፡ እልካችኋለኍ፡ አለ። ፫ የጌታችን፡ የየሱስ፡ ክርስቶስ፡ የሐዋርያት | ና፡ የተከታዮቻቸውም፡ መልእክተኝነት፡ ከዚያች፡ ካንዲት፡ ያምላክ፡ ሥልጣን፡ የወጣች፡ ናት። እንዲህ፡ ከሆነ፡ በዚያ፡ ዘመን፡ ደቀመዛሙርቱንና፡ አርድእቱን፡ ባለቤቱ፡ አዘዘ። ከዚያ፡ ጊዜ፡ ዠምሮ፡ እስከ፡ ዛሬ፤ እስካለም፡ ፍጻሜም፡ በምስለኔው፡ በሮም፡ ርእሰ፡ ሊቃነ፡ ጳጳሳት፡ ቃል፡ የሚልክና፡ የሚያዝ፡ ጌታችን፡ የ፡ ክ፡ ነው። የከዋክብትን፡ ቍጥር፡ ለማወቅ፡ አንችልም። ነገር፡ ግን፡ ከሁላቼው፡ በላይ፡ ያለ፡ ጣይ፡ አንድ፡ ብቻ፡ እንደ፡ ሆነ፡ እናያለን። እንደዚሁም፡ ደግሞ፡ በቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ጳጳሳትና፡ መምህራን፡ መልእክተኞችም፡ ምንም፡ ቢበዙ፤ አለቃቸው፡ አንድ፡ ብቻ፡ እንደ፡ ሆነ፡ ግልጥ፡ ነው። ይህም፡ ሊታወቅ፡ ጌታችን፡ የ፡ ክ፤ ባለ | ቤቱ፡ ወኢትረስዩ፡ አበ፡ በዲበ፡ ምድር፡ እስመ፡ ፩ውእቱ፡ አቡክሙ፡ ሰማያዊ። ወኢተሰመዩ፡ መምህራነ። እስመ፡ ፩ መምህርክሙ፡ ውእቱ፡ ክርስቶስ ። ፩ ብልዋል። እንዲህ፡ ካለን፡ መንፈሳዊ፡ ወይም፡ ሥጋዊ፡ አባት፡ ካምላካችን፡ ከመድኃኒታችንም፡ የሚለየን፡ ቢሆን፡ እርሱን፡ አባት፡ እንዳናደርግ፡ ይከለከለናል። ስለዚህ፡ ከሮም፡ ርእሰ፡ ሊቃነ፡ ጳጳሳት፡ ካንዱ፡ ከምስለኔው፡ ጋራ፡ አንድነትን፡ የማያደርግ፡ መምር፡ ሌላ፡ አባትና፡ ሌላ፡ ክርስቶስን፡ እንዲፈልግ፡ ይገልጣል። ዛሬ፡ በሮም፡ ያለ፡ በቅዱስ፡ ጴጥሮስ፡ ወምበር፡ ተቀምጦ፡ ያለ፡ ጳጳስ፡ የጴጥሮስ፡ ተከታይ፡ የጌታችንም፡ ምስለኔ፡ እርሱ፡ ብቻ፡ እንደ፡ ሆነ፡ ባለቤቱ፡ ጌታችን፡ የ፡ ክ፡ አን | ተ፡ ኰኵሕ፡ ወዲበ፡ ዛቲ፡ ኰኵሕ፡ አሐንጻ፡ ለቤተ፡ ክርስቲያንየ፡ ወኢይኄይልዋ፡ አናቅጸ፡ ሲኦል፡ አለው። ፩ ዳግመኛም፡ ወይከውና፡ ፩ደ፡ መርዓተ፡ ለ፩ ኖላዊ። ፪ ብሎ፡ አንዱን፡ ጴጥሮስን፡ ብቻ፡ ሶስተግዜ፡ እየመላለስ፡ ረዓይኬ፡ አባግዕየ። ረዓይኬ፡ መሐስእየ። ረዓይኬ፡ አባግዕየ፡ እንዳለው፡ ተጽፍዋል። ሌትና፡ ቀን፡ የተለዩ፡ ናቸው። ጨለማ፡ በሌት፡ ይሠለጥናል። እንደርሱም፡ ሁሉ፡ ባሰተኛ፡ አምልኮ፡ የሚኖሩ፡ በድንቍርና፡ ጨለማ፡ ናቸው። አለቃቸውም፡ መልአከ፡ ጽልመት፡ የተባለ፡ ሰይጣን፡ ነው። በቀን፡ ግን፡ የሚገዛ፡ ጣይ፡ እንደ፡ ሆነ፡ እንደዚኸውም፡ ደግሞ፡ በቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ካቶሊካዊት፡ ሐዋርያዊት፤ ሮማዊት፤ | የሚገዛ፡ በምስለኔውም፡ ወትሮ፡ የሚያበራ፡ የማይጠፋ፡ የጽድቅ፡ ጣይ፡ ጌታችን፡ የ፡ ክርስቶስ፡ ነውና፡ ከምስለኔው፡ ጋራ፡ አንድነት፡ ያላቼው፡ ሁሉ፡ በብርሃን፡ ውስጥ፡ ይኖራሉ። ነቢይ፡ ዘካርያስ፡ እንዲህ፡ ስትልም፡ ንገረው። እንዲህ፡ ይላል፡ እግዚአብሔር፡ የሠራዊት፡ ጌታ፡ እነሆ፡ አንድ፡ ሰው፡ ስሙን፡ ጭብጭቦ፡ የሚሉት። እርሱም፡ ከስፍራው፡ ይጨበጭባል፡ የእግዚአብሔርንም፡ መቅደስ፡ ይሠራል። እርሱ፡ የእግዜርን፡ መቅደስ፡ ይሠራል። እርሱም፡ ክብርን፡ ይሽከማል፡ ይቀመጥማል፡ በዙፋኑም፡ ላይ፡ ይነግሣል። በዙፋኑም፡ ላይ፡ ካህን፡ ይሆናል። የሰላም፡ ምክርም፡ በለዚያ፡ በሁለቱ፡ ማኸል፡ ይሆ | ናል። አለ። ፩ ይህ፡ ቃል፡ ለጊዜው፡ ቤተ፡ መቅደስ፡ ለማደስና፡ ለመሥራት፡ ከዳዊት፡ ወገን፡ ለተመረጠው፡ ለዘሩባቤልና፡ ለሊቀ፡ ካህናት፡ የሱኢ፡ ነው፡ የተነገረ። ነገርግን፡ ዓይነተኛ፡ ምሥጢሩ፡ ሰውን፡ ለሆነ፡ ለእግዚአብሔር፡ አብ፡ ልጅ፡ ብርሃን፡ ነው። ከራሱ፡ የሚጨበጭብ፡ እንዳለ፡ ከዳዊት፡ ዘር፡ በድንግልና፡ በታላቅ፡ ታምራት፡ ተወለደ። ዘሩባቤል፡ ፈርሳ፡ የነበረችን፡ አንዲት፡ ቤተ፡ መቅደስ፡ ብቻ፡ ሠራ። የትሩፋቱ፡ ኃይል፡ ደምበር፡ የሌለው፡ ጌታችን፡ የሱስ፡ ክርስቶስ፡ ግን፡ በኃጢአት፡ ወድቆ፡ ባድማ፡ ሁኖ፡ የነበረን፡ ዓለም፡ ሁሉ፡ አሥነሳ፡ አደሰም። ሽልማቱንም፡ ቅድስናና፡ ጻድ | ድቅነት፡ ንጽሕናንም፡ ናቸው፡ እንጂ፡ እንደ፡ ሰሎሞን፡ ቤተ፡ መቅደስ፡ ሽልማት፡ መሬታውያን፡ ያይዶሉ፤ ላለም፡ ሁሉ፡ የምትበቃን፡ አንዲት፡ የተቀደሰችን፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ በከበረ፡ ደሙ፡ ላባቱ፡ ለእግዜር፡ አብ፡ ሠራ። መጣፍም፡ እንዳለነ፡ በርስዋ፡ በዙፋኑ፡ ላይ፡ ተቀምጦ፡ የሚነግሥና፡ የሚፈርድም፡ ባለቤቱ፡ ከሆነ፤ ይህም፡ ቃል፡ አነ፡ እሄሉ፡ ምስሌክሙ፡ እስከ፡ ኀልቀተ፡ ዓለም፡ ካለው፡ ጋራ፡ ከገጠመ፤ ሮማዊት፡ ቤተ፡ ክርስቲያንና፡ በርስዋ፡ ያለን፡ ምስለኔውን፡ ጳጳስ፡ መስደብ፡ ከነዚያ፡ ከገዳዮቹ፡ ከአይሁድ፡ ስድብ፡ የከፋች፡ ናት። እንግዴህ፡ በክፋቱና፡ በቸልታው፡ ካልሆነ፡ እውነት፡ ጣይ፡ ያለበትን፡ ለማየትና፡ | ለማወቅ፡ የሚሳነው፡ የለም። እንዳትሞት፡ ይህችን፡ ፍሬ፡ አትብላ፡ ብሎ፡ ነግሮት፡ ሳለ፡ በልቶ፡ ርግመትንና፡ ሞትን፡ ስለምን፡ በላያችን፡ አስመጣብን፡ እያሉ፡ ባዳም፡ ላይ፡ ይፈርዳሉ። እንደዚህም፡ ደግሞ፡ በትምርትዋ፡ ባምልኮዋም፡ ሥራት፡ እውነተኝነት፡ እንደ፡ ጣይ፡ ላለም፡ ሀሉ፡ የምታበራን፡ በቸርነቱ፡ ብዛት፡ ሠርቶቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ሠርቶ፡ በኃይሉም፡ አጥንቶ፤ ለእመ፡ ኢሰምዓ፡ ለቤተ፡ ክርስቲያን፡ ይኩንከ፡ ከመ፡ ዓረማዊ፡ ወመጸብሐዊ። ፩ ያለውን፡ ረስተው፡ ወይም፡ ንቀው፤ የእግዜርን፡ ርግመትና፡ መቅሠፍት፡ በላያቼውና፡ በዘመዶቻቼው፡ ባጋራቼም፡ ላይ፡ በመንግሥታቼውም፡ ላይ፡ አወረዱ። ከብርሃን፡ የወጣ፡ ብርሃ | ን፡ ካምላክም፡ የተወለደ፡ አምላክ፡ የዘላለምም፡ ጥበብ፡ በታላቅ፡ ችሎቱና፡ ብልሃቱ፡ እንዲያጠናት፡ አውቆ፡ ወኢይኄልዋ፡ አንቅጸ፡ ሲኦል፡ ፩ ባይል፡ መናፍቃን፡ ሮማዊት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ አሰትን፡ በመናገርዋ፡ ወደቀች፡ ፈረሰችም፡ እያሉ፡ የተመረጡትን፡ ስንኳ፡ ባሳቱ፡ ነበር፡ ይመስለኛል። ዳግመኛም፡ ከመ፡ ይኩና፡ ፩ደ፡ መርዔተ፡ ለ፩ ኖላዊ፡ ባይል፡ ከነዚያ፡ ተጠንቀቅ፡ ካለኝ፡ የበጎችን፡ ልብስ፡ ለብሰው፡ የሚመጡብኝን፡ ተኵሎች፡ ለይቼ፡ ማወቅ፡ ባልተቻለኝም፡ ነበረ። በግም፡ የተባለ፡ ጌታችን፡ የ፡ ክ፡ ነው። ነገር፡ ግን፡ አሰተኛ፡ መምር፡ በውጭ፡ የርሱን፡ አብነትንና፡ ሥልጣንን፡ ይዞ፡ በጾምና፡ በተጋድሎ፡ በማስተማርና፡ በመመጽወት፡ ይመጣል። ዳግመ | ኛም፡ ቅዱስ፡ ጳውሎስ፡ ወይትሜሰል፡ ከመ፡ መልአከ፡ ብርሃን፡ ፩ እንዳለ፡ ጌታችን፡ የ፡ ክ፡ ም፡ ወእምፍሬሆሙ፡ ተአምርዎሙ፡ ፪ እንዳለ፡ የብርሃን፡ ልብስ፡ ለብሶ፡ ምግባሩም፡ መልካም፡ ከሆነ፡ ማወቁ፡ አሽቸጋሪ፡ ነው። ነገር፡ ግን፡ እንደዚህ፡ ያለን፡ ቢመጣብኝ፡ መዠመርያ፡ በትዕምርተ፡ መስቀል፡ ፊቴን፡ አማትቤ፡ የማን፡ ወገን፡ ነህ፤ የላከኸስ፡ መነው፡ ብዬ፡ እጠይቀዋለኍ። ተኵላ፡ መሆኑን፡ የምታስታውቀው፡ ናትና፤ እርሱም፡ ፊቱን፡ ያከፋል፡ ። ይናደድማል። የመልከ፡ ጽልመት፡ መልእክተኛና፡ ወገን፡ መሆኑን፡ ይገልጣል። በሮም፡ ያለን፡ የጌታችነን፡ ምስለኔን፡ ይሰድባል። መንፈስ፡ ቅዱስም፡ በርስዋ፡ አድሮ፡ ያለ፡ በርሱ ም፡ የሕይወት ፡ ትምርት፡ ትንፋሽን፡ የምታስተ | ነፍን፡ ቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ይሰድባል። አይሁድ፡ የጌታችነን፡ በጕነት ና፡ ታምራትን፡ እያዩ፡ በቅናት፡ እየተነደዱ፡ መግደሉን፡ እንዳላፈሩ፤ እህም፡ በመንፈሳዊ፡ ወቶት፡ አጥብታ፡ ያሳደገችውን፡ እናቱን፡ መስደብ፡ አያሳፍረውም። በስምዓ፡ ፪ወ፫ ይቁም፡ ኵሉ፡ ነገር፡ ፩ የሚል፡ ሕግ፡ በልቡና፡ በቅዱሳት፡ መጻሕፍት፡ ተጽፎ፡ ሳለ፡ ይህነን፡ ትቶ፦ ስድስት፡ መቶ፡ ፴፮ት፡ ጳጳሳት፡ ከጌታችን፡ ምስለኔ፡ ከሮም፡ ጳጳስ፡ ጋራ፡ አንድ፡ ሁነው፡ በኬልቄዶን፡ የወሰኑዋትን፡ ሃይማኖት፡ ሰደበ። ግርምቢጥ፡ መሆኑን፡ ልቡ፡ ሲመሰክርለት፡ ሳለ፡ እኒህን፡ አሰተኞች፡ ናቼው፡ አለ። እርሳቸው፡ ያወገዙትን፡ አንድ፡ ባሕርይ፡ ያለውን፡ ግን፡ እውነተኛ፡ ነው፡ አለ። እህዲህ፡ ከሆነ፡ ግ | ን፡ ወነአምን፡ በአሐቲ፡ ቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ እንተ፡ ላዕለ፡ ኵሉ፡ ጉባዔ፡ ዘሐዋርያት፡ ፩ የተበለውን፡ ቃል፡ አያምንምና፡ ጌታችን፡ ይኩንከ፡ ከመ፡ ዓረማዊ፡ ወመጸብሐዊ፡ እንዳለ፡ ዓረመኔ፡ መሆኑን፡ ገለጠ። ከብርሃንም፡ ጨለማን፡ አብልጦ፡ ወደደ። ስለዚህም፡ ምስጋና፡ ይግባውና፡ ጌታችን፡ ወአብደረ፡ ሰብእ፡ ጽልመተ፡ እምብርሃን፡ ፪ ያለው፡ እርሱን፡ ነው። | እኔም፡ ባለማወቄ፡ በዚህ፡ ጨለማ፡ ውስጥ፡ ነበርኍ። ነገርግን፡ ምሕረቱ፡ የበዛች፡ አምላክ፡ ከዚህ፡ ጨለማ፡ እንዲያወጣኝ፡ ማርካኝም፡ ከነበረች፡ ከፈርዖን፡ እጅ፡ ሊያስለቅቀኝ፡ ከዘላለም፡ ሞትም፡ ያድነኝ፡ ዘንድ፡ ክቡር፡ ያዕቆብ፡ መክእክተኛውን፡ | ሰደደልኝ፡ ፩ ከመጡም፡ ዠምሮ፡ እስከ፡ ዕረፍትም፡ ቀን፡ ድረስ፡ አንዲት፡ ቀን፡ ስንኳ፡ ሳያርፉ፡ ኸያ፡ ሁለት፡ ዓመት፡ ስለኔ፡ ከመልከ፡ ጽልመት፡ ጭፍራ፡ ጋራ፡ ተዋጉ። ጭፍራውም፡ በሶስት፡ ክቢ፡ ስለመጣብዎ፡ ውጊው፡ እጅግ፡ ብርቱ፡ ነበረ። በወንጌል፡ የተነገሩቱ፡ ዝናብና፡ ጐርፎች፡ ነፋሶችም፡ በዚያ፡ በእግዜር፡ ባርያ፡ ቤት፡ ላይ፡ ወረዱበት፡ ገፉትም። ነገር፡ ግን፡ በሃይማኖትና፡ በተስፋ፡ በፍቅርም፡ ኃይላት፡ የታጠቁ፡ ነበሩና፡ ትሕትናና፡ የዋህነት፡ ትዕግሥትም፡ የልብዎ፡ መሠረቶች፡ ነበሩና፡ አቈሰሉዎ፡ እንጂ፡ መጣልዎ፡ አልተቻላቸውም። ደቂቀ፡ እጓለ፡ እመሕያው፡ ስነኒሆሙ፡ ኃፅ፡ ወኵናት፡ ወልሳኖሙኒ፡ በሊሕ፡ መጥናሕት፡ ፪ እንዳለ፡ | ከጠላት፡ የተላኩ፡ ክፎች፡ መርዝ፡ የተቀቡ፡ ጦርንና፡ ፍላጻ፡ ወረወሩብዎ። እርሱም፡ ግን፡ መንፈሳዊ፡ ዓርበኛ፡ ለቄሣር፡ ከነበረቱ፡ ከነዚያ፡ ጀግኖች፡ ዓለምን፡ ሁሉ፡ ካንቀጠቀጡቱ፡ የሚበልጡ፡ እውነተኛ፡ ጀግና፡ የሮም፡ ሰው፡ ነበሩና፡ ጦሩን፡ ፍላጣውንም፡ እየነቀሉ፡ ወደፊት፡ ገፉ፡ እንጂ፡ ወደኋላ፡ አንደግዜ፡ ስንኳ፡ ፊትዎን፡ አለመለሱም። እስመ፡ ፍቅር፡ ከመ፡ ሞት፡ ጽንዕት፡ ፩ እንዳለ፡ የኢትዮጵያን፡ ሕዝብ፡ እንዲወዱ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ በሞንስኘር፡ ደዢቆብ፡ ልብ፡ አሳድርዋት፡ የነበረችን፡ ፍቅር፡ እሳት፡ ወሁ፡ ሁሉ፡ ተሰብስቦ፡ ማጥፋትዋን፡ አልተቻለውም። | ምንም፡ ሁሉ፡ ባይሆን፡ እንደችሎቴ፡ ገድልዎን፡ የምትናገር፡ መጻፍ፡ ሌላን፡ | ጽፌ፡ አለኍ። ነገር፡ ግን፡ ልበ፡ ቅን፡ ሰው፡ የዚያ፡ እርስዎን፡ የሚነቅፍ፡ ነገር፡ ሰምቶ፡ ወይም፡ በርስዎ፡ ላይ፡ የጻፈውን፡ አንብቦ፡ እውነት፡ እንዳይመስለው፡ በመስደብዎም፡ እንዳይጐዳ፡ የዚያን፡ የነቀፈዎን፡ ነገር፡ ምክንያቱንና፡ ተሳቢውን፡ እንዲያይ፡ ከዚያው፡ ጥቂቱን፡ ልጽፍለት፡ ፍቅሩ፡ አተጋችኝ። | እንደ፡ ተጻፈ፡ ቅዱሳን፡ ሐዋርያት፡ በርናባስና፡ ጳውሎስ፡ ያሳመኑዋቸውን፡ አሕዛብ፡ ቢጽ፡ ሐሳውያን፡ወመሀርዎሙ፡ ለሕዝብ፡ ወይቤልዎሙ፡ እም፡ ከመ፡ ኢትትገዘሩ፡ በሕገ፡ ሙሴ፡ ኢትክሉ፡ ሐይወ። ወተሐውኩ፡ ሕዝብ፡ ፈድፋደ፡ ፩ እያሉ፡ አወኩዋቼው። በክቡር፡ አባታችን፡ ላይም፡ እንደርሱ፡ ሆነ። ካገረዎ፡ የመጡ፡ አንዳንድ፡ ሰዎች፤ ሙሴ፡ ደዢቆብ፡ የስ | ብከትዎን፡ አደራረግ፡ አላወቁበትም። የወደቀን፡ ሰው፡ በራሱ፡ ብትደግፈው፡ ቶሎ፡ ይነሣል። በ ግሩ፡ ግን፡ ብታነሣው፡ መከራን፡ ለመጨመር፡ ነው፡ እንጂ፡ ለማሥነሳቱ፡ አይደለም። ሙሴ፡ ደዢቆብም፡ ዓይነተኞች፡ መምሮች፡ ባሉባቼው፡ አገሮች፡ በጐንደር ና፡ በጎዣም፡ ስብከትን፡ እንዳይዠምሩ፡ በዳርቻ፡ በደናቁርቶች፡ አገር፡ ዠመሩ፡ አሉ። ሌሎቹም፡ ደግሞ፡ በዚያ፡ በገንዘባችን፡ ባልና፡ ምሽት፡ እያጋባበት፡ እኛ፡ በራብና፡ በርዝና፡ እንጨነቃለን። ገንዘብን፡ በመስጠት፡ ነው፡ ነው፡ እንጂ፡ በእውነት፡ ወደ፡ ካቶሊክ፡ ሃይማኖት፡ ያስመለሰው፡ የለውም፡ ብለው፡ ወዳለቃቼው፡ ጻፉ። አበ፡ ምኔቱም፡ ይህነን፡ አምነው፡ እንዲህ፡ ከሆነስ፡ ተመልሶ፡ እንዲመጣ፡ ገንዘብን፡ አንስደዱለት፡ ብለው፡ አዘዙ። ሞንስኘር፡ | ደዢቆብም፡ ከሶስት፡ በቀር፡ ሌላ፡ እንዳልቀረልዎ፡ አይተው፡ በዚህ፡ ምክንያት፡ ተጨነቁ። ስለዚህም፡ ብድርን፡ ፈልገው፡ ወደ፡ ሙሴ፡ ዴጉቴን፡ ምጽዋ፡ ኮንሱል፡ ፈረንሳዊ፡ ላኩ። ነገር፡ ግን፡ መልእክተኞች፡ ወደ፡ ድሆኖ፡ ሲደርሱ፡ ወደ፡ እስክንድርያ፡ ሊሔዱ፡ በጀልባ፡ ተጫኑ። ምሽታቸው፡ በምንኵሉ፡ ነበሩና፡ ወረቀቱን፡ አይተው፡ እጅግ፡ አዘኑ። ጌታው፡ ሳሉ፡ ትላንትና፡ መጥታችኍ፡ ብትሆኑ፡ መልካም፡ ነበረ። እኔ፡ ግን፡ ሴት፡ ነኝና፡ ላበድር፡ አልችልም። ነገር፡ ግን፡ እስኪ፡ ወሬ፡ እንኳ፡ ቢገኝ፡ ይዛችኁላቼው፡ ልትመለሱ፡ ቆዩ፡ አሉነ። ባራተኛው፡ ቀን፡ ይመስለኛል፡ ሳይታሰቡ፡ እነሆ፡ ሞንሰኘር፡ ማሳያ፡ በእስላሞች፡ ጀልባ፡ ካጋራቼው፡ ወደ፡ ምጽዋ፡ ደረሱ። መምጣትዎም፡ በ፲፰፴፱ኝ፡ ዓመተ፡ ሥጋዌ፡ ሞን፡ ደ፡ ሮም፡ ከተመለሱ፡ በኋላ፡ በ፮ኛ፡ ዓ፡ ይመስለኛል፡ ሆነ፡ ስለዚህ፡ የርሳቼው፡ መምጣት፡ ላባታችን፡ ደስ፡ የሚያሰኝ፡ ጭንቅትዎንም፡ የሚያቀል፡ ምስክርንም፡ የሚሆን፡ ሆነ። ይህም፡ ባባታችን፡ ገድል፡ ተጽፍዋል። ዳግመኛም፡ ሞን፡ ደ፡ የነቀፉ፡ ሌሎች፡ አሉ። | ፍራንሲያ፡ ኮንሱል፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ከመንግሥታቼው፡ ተልከው፡ ወዳጼ፡ ቴዎድሮስ፡ መጥተው፡ ነበሩና፡ ያዩትን፡ የሰሙትንም፡ ጽፈዋል። ወዳግራችንም፡ የገቡበት፡ ዘመን፡ ባለቤታቼው፡ በጻፉት፡ በዚያው፡ መጻፍ፡ በነዚያ፡ ቍጥር፡ ባ፲፰፷፫ ዓመተ፡ ምሕረት፡ ነው። ንጉሥ፡ ወደ፡ ሌላ፡ ሔደው፡ ነበሩና፡ በጋፋት፡ ወደ፡ ነበሩቱ፡ ፕሮተስታንቲ፡ ገባኍ፡ ይላሉ። |
Alignment Start a translation alignment with Alpheios Alignment. You can also add morphological annotations there. See instructions in GitHub.
Versions See parallel versions if any is available
Quotations Check for marked up quotations of a passage in this section
back to top
መዠመርያ፡ ክፍል። | የሰሙት፡ ነገር፡ ሁሉ፡ መስልዋቼው፡ ጽፈዋል። በ፴፱ኛ፡ ገጽ፡ አባ፡ ሳፔቶ፡ የካፑሲን፡ ወገን፡ ከሮም፡ ፕሮፖጋንዳ፡ ተልከው፡ ወደ፡ ሐበሻ፡ መጡ፡ ይላሉ። ግን፡ ሙሴ፡ ሳፔቶ፡ የላዛሪስቲ፡ | ወገን፡ ነበሩ፡ እንጂ፡ የካፑሲን፡ አይደሉምና፡ ተሳስተዋል። በዚያም፡ ቀጥለው፡ ነገር፡ ግን፡ ያበሻ፡ ጳጳስ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆቢስ፡ ባ፲፰፻፵ ወደዚኸው፡ አገር፡ እስኪመጡ፡ ድረስ፡ ሚሲዮን፡ አልተሠራቸም፡ ነበረች፡ ብለዋል። በዚያ፡ ጊዜ፡ ጳጳስነት፡ አልተሾሙም፡ ነበርና፡ ይህም፡ ውሽት፡ ነው። | ፩ በዚኸውም፡ ገጽና፡ በሚከተለው፡ ሙሴ፡ ደዢቆብን፡ እነቅፋለኍ፡ የኢምፖሊቲክ፡ መደባለቅና፡ ልክ፡ በሌለው፡ በሐበሻ፡ ባለገሮች፡ ሥራ፡ ሥሮቻቼው፡ አሳዛኞች፡ ከሚሆኑ፡ ከነዚያ፡ ሰዎች፡ አንዱ፡ እርሱ፡ ነበር። | ፪ ቄስ፡ ከመሆኑም፡ በፊት፡ ሰይፍ፡ አልነበረውም፡ ላለማለት፡ አልደነቅም። ወደማይለወጡም፡ አሳቦቹ፡ ለማስገዛት፡ የምትቃጠልና፡ ብርቱ፡ ፍትወት፡ | የማትታመንም፡ ብርቱ፡ ጥናት፡ ያኖር፡ ነበረ። ከዚህም፡ ፫ ጋራ፡ የማይለወጥ፡ ፍቅርና፡ ትዕግሥት፡ ነበረው። በሐዋርያነቱም፡ ባንዳቻቼው፡ ዓመቶች፤ ደምበር፡ የሌለው፡ እጅግ፡ የወጣ፡ ስም፡ በዚህች፡ ፬ አገር፡ ባሉቱ፡ ሕዝብ፡ ክርስቲያንና፡ እስላሞች፡ ላይ፡ ነበረው። እጅግ፡ የከበረ፡ ውቤም፡ ባቡነ፡ ያዕቆብ፡ ቤት፡ አጠገብ፡ ሲያልፍ፡ ከበቅሎው፡ ሳይወርድ፡ ምንም፡ አላለፈም። እስላሞችስንኳ፡ ይህችነን፡ ክብር፡ ለርሱ፡ ይሰጣሉ። ዛሬም፡ ደግሞ፡ ቅዱስ፡ ያዕቆብ፡ ከማለት፡ በቅር፡ በሌላ፡ አይጠሩትም። እምበረሚ፡ የምትባል፡ በበምጽዋ፡ አጠገብ፡ አለች። ሸኽ፡ መሀመድ፡ ወድዓሊ፡ የሚባል፡ በዚያም፡ ወገን፡ ሁሉ፡ በስላምነት፡ አምልኮ፡ አለቃ፡ የሚሆን፡ ከጥቂት፡ በቅር | ም፡ እንደ፡ ነቢይ፡ ክብር፡ የከበሩ፡ በዚኸው፡ አገር፡ አለ። ከዚህ፡ ወደምጽዋ፡ ለምን፡ በእግርዎ፡ ይሔዳሉ፡ ሳሉት፡ ለኔ፡ ይልቅ፡ ላምላክ፡ አጠገብ፡ የሆነ፡ በባለጸግነትም፡ ከፍ፡ ያለ፡ ስለ፡ ሃይማኖቱም፡ ፍቅር፡ ያቀረባት፡ አቡነ፡ ያዕቆብ፡ ምጽዋ፡ እስከ፡ ከረን፡ ያምስት፡ ቀን፡ መንገድ፡ በእግሩ፡ ከሔደ፡ እኔ፡ ይልቅ፡ ያ፬ት፡ ሰዓት፡ መንገድን፡ እንዴት፡ በበቅሎ፡ መቀመጤ፡ ፈከጋችኍ፡ አላቼው። | ፭ ይህ፡ እውነተኛ፡ ታላቅ፡ ሰው፡ ከግድፈት፡ በቀር፡ ሌላ፡ አልነበረውም። እርሱ፡ ከፕሮፖጋንዳ፡ የተላከ፡ ሲሆን፡ ለሁሉ፡ የባላገር፡ ሁከት፡ መቈያ፡ ሆነ። | አቡኖችን፡ ለመምረጥ፡ ታላቅ፡ ችሎት፡ የነበራት፡ የጐንደር፡ ከተማ፡ ነበረች። ሙሴ፡ ደዢቂብም፡ እንደ፡ ልቡ፡ አሳብ፡ አንዱ | ን፡ አለቃ፡ ወደ፡ ችሎት፡ የምትወስድን፡ ሁከተኛ፡ የመግዛት፡ ብልሃት፡ ተስፋን፡ ማድረግ፡ በቻለ፡ ነበረ፡ የሚሻትንም፡ ግፈኛ፡ ፈተና፡ አምልኮ፡ በክርክር፡ ብልሃት፡ ባመጣ፡ ነበረ፡ ይላል። |
chapter ()
Alignment Start a translation alignment with Alpheios Alignment. You can also add morphological annotations there. See instructions in GitHub.
Versions See parallel versions if any is available
Quotations Check for marked up quotations of a passage in this section
back to top
፪ኛ፡ ክፍል። | ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ የሚነቅፉበት፡ ፩ ምክንያት፡ ከመጡ፡ በኋላ፡ በ፪ኛው፡ ዓመት፡ ከደጃዝማች፡ ውቤ፡ ተለምነው፡ አቡንን፡ ሊያመጡ፡ ከላኩዋቸው፡ ሰዎች፡ ጋራ፡ ወደ፡ ግብጽ፡ በመመለስዎ፡ ነው። ፪ኛም፡ ከዚህ፡ በኋላ፡ ባ፲፯ ዓመት፡ ካገሩ፡ ገጅ፡ ከደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ጋራ፡ ስለ፡ ተፋቀሩ፡ ነው። ነገር፡ ግን፡ ጠማማ፡ አእምሮና፡ ክፉይቱ፡ ፈቃድ፡ ለሰድብ፡ ስላስቸኰሉዋቸው፡ ፪ኛውን፡ መዠመርያ፡ አደረጉ። እርሱን | ም፡ ሳይጨረሱ፡ በማኸል፡ አቡንን፡ ለማምጣት፡ ወደ፡ ምስር፡ ተመለ፡ ብለዋል። | ፩ ምላሽ፡ ስለመዠመርያው፡ አኃዝ፡ ሞንሰኘር፡ ደዳቆብን፡ ወዳገራችን፡ ከመጡ፡ ዥምሮ፡ እስከ፡ ዕረፍትዎ፡ ድረስ፡ በሥራትዎ፡ ቢሆን፡ ባነዋርዎ፡ ቢሆን፡ ለእግዜርና፡ ለሰው፡ የምትገባን፡ ፍቅር፡ ለመጠበቅ፡ ብዙ፡ መከራ፡ ተቀበሉ፡ እንጂ፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ አሳዛኞች፡ ከሚሆኑ፡ ከነዚያ፡ አንዱ፡ እርሱ፡ ነበረ፡ እንዳሉቱ፡ አይደለም። አቡነ፡ ሰላማ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ላይ፡ ብርቱ፡ ጠላት፡ እንዳልነበሩ፡ የሚጠረጥር፡ የለም፡ ነገር፡ ግን፡ ከጌታችን፡ ልደት፡ በኋላ፡ በኛ፡ ቍጥር፡ ባ፲፰፵፮፡ ዓመተ፡ ሥጋዌ፡ በሐምሌ፡ ወር፡ ስለ፡ ካቶሊካዊት፡ ሃይማኖት፡ የታሠሩን፡ መነኮሳት፡ በፊታቸው፡ አቁመው፡ ሲገሥፁ | ና፡ ሲወቅሱ፡ ያዕቆብ፡ እጅግ፡ መልካም፡ ሰው፡ ነው፡ ቅጣት፡ አይገባውም። እርሱ፡ እኔን፡ ትሰድባላችኍ፡ አሉዋቼው። ለዚህ፡ ቀንም፡ በፊት፡ በሰኔ፡ ወር፡ ኋላ፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ የተባሉን፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ በነፍስህ፡ እያዝኃለኍ፡ ይበሉኝ፡ እንጂ፡ አንገታንገቱን፡ በሰይፍ፡ ልበው፡ ቢሉዋቸው፡ አቡን፡ በዘመናችን፡ የወንጌልን፡ ሕግ፡ የፈጸመ፡ እንደ፡ ያዕቆብ፡ የለምና፡ አባርልኝ፡ እንጂ፡ ሞትስ፡ አይገባውም፡ አሉዋቸው። ኋላም፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢዕቆብን፡ እንዳመሰገኑ፡ የምሽታቸው፡ የእቴጌ፡ ጥሩ፡ ነሽ፡ ጠባቂ፡ ከነበሩቱ፡ ከጃንደረባ፡ ካባ፡ ወልደ፡ የሱስ፡ በመቅደላ ም፡ ታሥረው፡ ከነበሩ፡ ከሙሴ፡ መክሬር፡ ፈራንሳዊ፡ ወይም፡ የአስቢሠራ። በ | መቅደላም፡ ታሥረው፡ የነበሩቱ፡ የኤውሮታውያን፡ ግዛት፡ ጠባቂ፡ ካቶ፡ ሳሙኤል፡ ተከንቲባ፡ ዘርአይም፡ ጃንሆይ፡ ይህ፡ ግብጥ፡ ጳጳስ፡ ከደኅናው፡ ሰው፡ ካባ፡ ያዕቆብ፡ ጋራ፡ አጣላኝ፡ ሲሉ፡ ሰማነ፡ እንዳሉ፡ ሰማኍ። ሰይጣን፡ ወይም፡ እርሱ፡ ያደረበት፡ ተንቀሳቃሽ፡ ካልሆነ፡ በቀር፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ ባጋራችን፡ የሚነቅፍ፡ የለም። | ፪ ምላሽ፡ ስለ፡ ሁለተኛ፡ አኃዝ። | ቄስ፡ ሳይሆን፡ ሰይፍ፡ እንዳልነበረው፡ አልደነቅም፡ ያሉቱና፡ በ፪ኛው፡ አኃዝ፡ ያለ፡ ነገር፡ ሁሉ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ጨካኝ፡ ክፉ፡ ሰው፡ ነፍሰ፡ ገዳይ፡ ከሆኑ፤ ወደ፡ ክፋትም፡ የምትስባቸው፡ የተቃጠለች፡ ብርቱ፡ ፍትወት፡ ነበረችው፡ ካሉ፡ የሚጣላ፡ ነገር፡ ነውና፡ የኢትዮጵያ፡ ሰው፡ ሁሉ፡ እርሱን፡ ማመስገናቸው፡ ባሰት፡ ነው፡ የምነቅ | ፈው፡ እኔ፡ | ፫ ብቻ፡ እውነተኛ፡ ነኝ፡ ማለት፡ ነው። ነገር፡ ግን፡ በ፪ኛው፡ አኃዝ፡ ያለ፡ ነገራቸው፡ በ፫ኛው፡ አኃዝ፡ ካለው፡ ቃላቸው፡ ጋራ፡ እንዲጣለ፡ እነሆ፡ እናያለን። ከዚህም፡ ጋራ፡ የማይለወጥ፡ ፍቅርና፡ ትዕግሥት፡ ነበረው። ከክርስቲያንና፡ ከእስላሞች፡ በሐበሻ፡ ካሉቱ፡ ሁሉ፡ ልክ፡ የሌላት፡ መልካም፡ ወሬ፡ አለችው፡ ያሉቱ፡ ፍቅርና፡ ትዕግሥት፡ ደምን፡ ለማፍሰስ፡ ሰይፍና፡ ወደ፡ ኃጢአት፡ የምትነዳ፡ ተናዳጅ፡ ፍትወት፡ ካላቱ፡ ሰው፡ ልብ፡ ጋራ፡ ነበሩ፡ ማለት፡ እርስበርሱ፡ እጅግ፡ የተጣላ፡ ነገር፡ ነው። | ፬ ምላሽ፡ ስለ፡ ፬ኛ፡ አኃዝ። | ደጃዝማች፡ ውቤ፡ ወዳቡነ፡ ያዕቆብ፡ ቤት፡ ሲደርሱ፡ ከበ፡ ሳይወርዱ፡ አላለፉም፡ ያሉቱም፡ አሰት፡ ነው። ደግነትዎን፡ ግን፡ ስላወቁ፡ ሲያመሰግኑዎና፡ ሲወዱዎ፡ ነበሩ። | አንድ፡ ቀን፡ ለብቻዎ፡ ሳሉ፡ አለቃ፡ ሐብተ፡ ሥላሴ፡ የኔታ፡ ሆይ፡ የነፍስዎን፡ ነገር፡ ቢያስቡ፡ ቢቈርቡ፡ መልካም፡ በሆነ፡ ቢሉዋቸው፤ ደጃዝማች፡ በማን፡ ቄስ፤ የማደርገው፡ ብሆን፡ ባቡነ፡ ያዕቆብ፡ ብቻ፡ በቈረብኍ ነበረ፡ አሉዋቼው። አንድ፡ ጊዜም፡ በሥራዬም፡ ባለች፡ በዓዲ፡ መንጐንቲ፡ ሰፍረው፡ ሳሉ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ካጋሜ፡ ወደርሳቸው፡ በመጡ፡ ጊዜ፡ ቢገናኙዋቸው፡ ከዙፋንዎ፡ ተነሡ፡ ይላሉ። እህም፡ ከደጃዝማች፡ ውቤ፡ መገኘት፡ እጅግ፡ ድንቅ፡ ነው። የእምበረሚው፡ መሀመድም፡ እንዳባቱ፡ እንደ፡ ፊተኛው፡ መሀመድ፡ ከእስላሞች፡ ሁሉ፡ ክብርን፡ ይቀበል፡ ነበርና፡ አቡነ፡ ያዕቆብ፡ በጻድቅነት፡ ከኔ፡ ይበልጣል፡ ብሎ፡ የተናገረ፡ አይመስለኝም፡ በባለ፡ ጸግነት፡ እጅግ፡ ከፍ፡ ያለ፡ እርስዋንም፡ ስለ፡ ሃይማኖቱ፡ ጥቅም፡ ያቀረባት፡ ስላሉትም፡ ነገር፡ | ተናግሮ፡ ቅሉ፡ ቢሆን፡ እስላሞችና፡ መናፍቃን፡ የማያማንም፡ ዓመፀኛ፡ ሁሉ፡ ሃይማኖትን፡ እንዲይዝላቸው፡ አቡነ፡ ያዕቆብ፡ ገንዘብን፡ ይሰጡ፡ ነበሩ፡ ይላሉና፡ ከኔ፡ ይልቅ፡ ለእግዜር፡ የቀረበ፡ ነው፡ ካለው፡ ቃል፡ ጋራ፡ አይጋጠምም። ዳግመኛም፡ ሃይማኖትን፡ ሌላውንም፡ መንፈሳዊ፡ ነገር፡ የሚገዛና፡ የሚሸጥ፡ አታላይ፡ ስምዖን፡ መሰርይ፡ ይባላልና፡ እስከ፡ ዛሬ፡ ድረስ፡ ገና፡ ቅዱስ፡ ያዕቆብ፡ ከማለት፡ በቀር፡ በሌላ፡ አይጠሩትም። ብለው፡ ባለቤታቸው፡ ከመስከሩት፡ ጋራ፡ እንዳይጣላ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ወደ፡ ሃይማኖት፡ ለማስገባት፡ ሰውን፡ በብር፡ አልገዙም። ወደ፡ ከረን ም፡ እንዳልደረሱ፡ በሁሉ፡ ዘንድ፡ የታወቀ፡ ነውና። ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ግን፡ ከምጽዋ፡ ወደ፡ ከረን፡ መጣ፡ ማለታቸው፡ ውሽት፡ ነው። | ፭ ምላሽ፡ ስላ፭ኛው፡ አኃዝ። | | ባምስተኛውም፡ አኀዝ፡ እንዳየነ፡ ይህ፡ እውነተኛ፡ ታላቅ፡ ሰው፡ ከግድፈት፡ በቀር፡ ሌላ፡ አልነበረውም። ለሁሉ፡ የባላገር፡ ሁከት፡ መቈያ፡ እርሱ፡ ነበረ፡ ብለዋል። መሴ፡ ሌዤአን፡ ወዳገራችን፡ የመጡበት፡ አባታችን፡ አቡነ፡ ያዕቆብ፡ ካረፉ፡ በኋላ፡ ባ፬ኛው፡ ዓመት፡ ነው። ምስጋና፡ | ይግባውና፡ ጌታችን፡ የሱስ፡ ክርስቶስ፡ የሰላም፡ ባለቤት፡ ሲሆን፡ ኢያምጻእኩ፡ ሰላመ፡ ለብሔር፡ እንዳለ፧ ስለ፡ ሃይማኖቱ፡ ምክንያት፡ አባት፡ ከልጅ፡ ልጅም፡ ካባት፡ ወዳጅም፡ ከወዳጅ፡ ተጣልተዋልና፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብም፡ የሮማዊት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ እውነተኛ፡ መልእክተኛ፡ ነበሩና፡ ባጋሜ፡ ባለች፡ በጐልዓ፡ የተማሪን፡ ቤት፡ በሠሩ፡ ጊዜ፡ ካቶሊክን፡ ሃይማኖት፡ ባሰፉ፡ ጊዜ፡ አቡነ፡ ሰላማ፡ እጅግ፡ ተቈጡ፡ ወደርሱ፡ ሃይማኖት፡ የገባውን፡ ሁሉ፡ ዝረፉ፡ ግደሉ፡ ብለው፡ ገዘቱ። በወንጌል፡ እንደ፡ ተነ | ገረ፡ በዚህ፡ ምክንያት፡ ከዚያ፡ ጊዜ፡ ዥምሮ፡ እስካሁን፡ ድረስ፡ ከመታወክና፡ ከመታሠር፡ ካቶሊካውያን፡ አላረፉም። አቡነ፡ ሰላማን፡ ደስ፡ ሊያሰኙ፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ አባታችን፡ አቡነ፡ ያዕቆብን፡ ጐንደር፡ ወደ፡ መተማ፡ ሰደዱዋቸው። እርስዎ፡ ግን፡ የታሠሩትን፡ ልጆቹ፡ መጨረሻቸውን፡ እንዳውቅ፡ ነፍሴን፡ ለሞት፡ አሳልፌ፡ እሰጣለሁ፡ ብለው፡ ከዚያ፡ ተመልሰው፡ በጐንደር፡ አጠገብ፡ ወዳለች፡ አገር፡ ወደ፡ አደርጅኃ፡ በስውር፡ ገቡ። ነገር፡ ግን፡ አቡን፡ ሰምተው፡ የጣቍሳንና፡ ያደርጅኃን፡ ባላገሮች፡ ጠላቴን፡ እንዴት፡ ዕመጣችኍ፡ እንዴትስ፡ ሰደዳችሁት፡ ብለው፡ ባላገሮችን፡ ዓሠሩ፡ ገንዘባቸውንም፡ ያዙ። እኛን፡ ዕሥሮችን፡ የሚጠብቅ፡ ባቡን፡ ቤት፡ የነበረ፡ ሽማግሌ፡ ደኅና፡ ሰው፡ የነዚያን፡ ሰዎች፡ ጭንቅ፡ አይቶ፡ ራርቶላቸው፡ እኒህ፡ አባ፡ ያዕቆ | ብ፡ ምንኛ፡ ክፉ፡ ሰው፡ ናቸው፡ አሁን፡ ይህ፡ ሁሉ፡ መከራ፡ በርሳቼው፡ ጠንቅ፡ አይዶለምን፡ ሲል፡ ሰማነው። ሙሴ፡ ሌዢአንም፡ የሁሉ፡ ሁከት፡ መቈያ፡ እርሱ፡ ነበረ፡ ማለታቼው፡ ከንደርሱ፡ ካለ፡ ሰው፡ ሰምተው፡ ይሆናል። ዳግመኛም፡ | የትግሮች፡ ይልቁንም፡ ያጋሜ፡ መኳንንቶች፡ ለዳጃዝማች፡ ውቤ፡ አንገዛም፡ ብለው፡ ወትሮ፡ ጦር፡ ሁከት፡ ነበረ። ይህነን፡ ግን፡ ሙሴ፡ ሌዢአን፡ እንዳሉ፡ አቡነ፡ ያዕቆብ፡ ጐንደር፡ ጳጳስ፡ ሊሆኑ፡ ከሆነ፡ ፲፭ ዓመት፡ የሚያህል፡ በትግሬ፡ በግዛታቸው፡ ሲኖሩ፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ በመንግሥቴ፡ ሥራት፡ ገባህ፡ ሳይሉዋቼው፡ እንዴት፡ ታገሡዋቼው። ብለውስ፡ እንደሆን፡ ማን፡ ያውቃል፡ የሚልም፡ ቢኖር፡ ሙሴ፡ ሌዢአን፡ የከበረ፡ ውቤ፡ በሙሴ፡ ደዢቆብ፡ ቤት፡ ሲደርስ፡ ከበቅሎው፡ ሳይወርድ፡ አላለፈም፡ ያሉትን፡ ይመልከት። | ዳግመኛም፡ የልቡን፡ አሳብ፡ የሚያደርግለት፡ አንዱን፡ አለቃ፡ ቢያገኝ፡ [...]ommission by የሚሻትንም፡ | ግፈኛ፡ ፈተና፡ አምልኮ፡ በክርክር፡ ብልሃት፡ ሊያመጣ፡ በቻለ፡ ነበረ፡ ብለዋል። ሞንስኘር፡ ደዢቆብ፡ በፍጹም፡ ልብዎ፡ በብርቱም፡ መውደድ፡ የሰበኩዋት፡ ብዙ፡ ጊዜም፡ ስለርስዋ፡ ራስዎን፡ ለሞት፡ አሳልፈው፡ የሰጡላት፡ ተካቶሊክና፡ የሐዋርያዊት፡ የሮማዊት፡ ቤት፡ ክርስቲያን፡ ቅድስት፡ ሃይማኖት፡ ናት። ይህነንም፡ ከሙሴ፡ ሌዢአን፡ በቀር፡ ሁሉ፡ ያውቃል። ሰዎች፡ ካቶሊክን፡ ነህ፡ ወይስ፡ ፕሮተስታንት፡ ብለው፡ ቢጠይቁዋቸው፡ ሙሴ፡ ሌዢአን፡ ክርስቲያን፡ ነኝ፡ ሁሉም፡ ቢሆን፡ ግድ፡ የለኝም፡ እንዳሉ፡ ከኤዎሮፓውያን፡ ከሁለት፡ ሰምቼ፡ ስጠራጠር፡ ነበርኍ። አሁን፡ ግን፡ ባለቤታቸው፡ ግፈኛ፡ ፈተና፡ አምልኮ፡ ካሉዋት፡ የመናፍቃን፡ ወይም፡ እግዜር፡ የ | ለም፡ ከሚለው፡ ካመፀኛው፡ ወገን፡ እንደ፡ ሆኑ፡ ባለቤታቸው፡ ገለጡ። ካማራ፡ አገር፡ ወደ፡ ምጽዋ፡ ወረዱ። ከዚያም፡ አቡነ፡ ቢያንኬሪን፡ ለመገናኘት፡ ወይም፡ ለሌላ፡ ጕዳያቸው፡ አባታችን፡ አቡነ፡ ያዕቆብ፡ ካረፉ፡ በኋላ፡ ባ፬ኛው፡ ዓመት፡ ወደ፡ ሄየ፡ መጥተው፡ ነበሩ። ቤተ፡ ክርስቲያን፡ እጅ፡ የሚነሡ፡ መስሎነ፡ አስጊፀን፡ ደጁንም፡ ከፍተን፡ ብንቈያቸው፡ ዙረው፡ ስንኳ፡ አላዩትም። በዚያም፡ ሲሰነብቱ፡ | ጊዮግራፊያን፡ ለማድረግ፡ ወደ፡ ተራራው፡ ሲወጡ፡ ነበር፡ እንጂ፡ በእሑድ፡ ቀን፡ ስንኳ፡ ቅዳሴን፡ ለመስማት፡ ወደ፡ ቤተ፡ ክርስቲ፡ ምንምን፡ አልገቡም። ስከዚህም፡ በዚያ፡ ላሉ፡ ምዕመናን፡ ይህ፡ ዓመፃቸው፡ ዕንቅፋት፡ ሆነ። ቁመታቸው፡ እጅግ፡ አጭር፡ ልብሳቸውም፡ በራሳቸው፡ የትርኮች፡ ቀይ፡ ጠርቡሽ፡ ነጭ፡ ጠባብ፡ ቀሚስና፡ ሱሪ፡ እንዳረቦች፡ ያለ፡ | ነበረ። የሚቀመጡዋትም፡ በቅሎ፡ የከሣች፡ ግላስ፡ ስንኳ፡ ያልነበራት፡ እጅግ፡ የተቈራመደ፡ መሣርያ፡ ነበረች። ይህንን፡ መታገሣቸው፡ ድኃ፡ ነው፡ ተብለው፡ ወወምበዴ፡ ለመዳን፡ ያደረጉት፡ ይመስለኛል። ነረግ፡ ግን፡ የፍራንሲያ፡ ኰንሱል፡ ነኝ፡ እያሉ፡ እንዲህ፡ ሆኖ፡ መታያት፡ ለንጉሣቸውና፡ ላገራቸው፡ ታላቅ፡ ውርደትን፡ ሰጡ። እንግዴህ፡ ወዓለምሰ፡ ጸልኦሙ፡ እስመ፡ ኢኮኑ፡ እሙንቱ፡ እምዓለም፡ (ዮሐ፤ ፲፯ ፲፬።) ያለውን፡ ሳንረሳ፡ የሙሴ፡ ሌዜአን፡ መጻፍ፡ በሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ላይ፡ የጻፉትን፡ በቅን፡ ልብ፡ መንበብ፡ ይገባል። | ባንድ፡ አገር፡ በብርቱ፡ የተመሽገች፡ አምባ፡ ነበረች። በርስዋ፡ ያሉትን፡ ዓመፀኞች፡ ለማውረድ፡ ንጉሥ፡ ጦሩን፡ ብዙ፡ ጊዜ፡ ሰደደ። ወታደሮቹም፡ ጀግንነታቸውን፡ ሊያሳዩ፡ እየደነ | ፉ፡ ወዳምባው፡ እግር፡ ፊት፡ ለፊት፡ ቀረቡ። ነገር፡ ግን፡ ካምባ፡ ያሉቱ፡ በሰደዱት፡ መርግ፡ ተጨፈለቁ። አንዳንዱ፡ ግን፡ አምልጠው፡ ወሬውን፡ ለንጉሥ፡ ነገሩ። እርሱም፡ ይህነን፡ ሰምቶ፡ በማዘን፡ ሳለ፡ አንድ፡ ብልህ፡ አለቃን፡ አግኝቶ፡ ወደዚያው፡ አምባ፡ ሰደደ። ይህም፡ ሽፍቶች፡ የሚሸነፉባትን፡ ብልሃት፡ አሰበ። ስለዚህ፡ እነዚያ፡ ምንምን፡ ባላሰቡት፡ በማይጠረጥሩት፡ ቦታ፡ ገባባቸው። አይዝዋችኍ። ከጌታዬ፡ ላስታርቃችኍ፡ መጣኍ፡ እንጂ፡ እናንተን፡ ለመግደል፡ አልመጣሁም፡ አላቼው። አንዳለውም፡ ሆነ። እነዚህን፡ ይዞ፡ ወደ፡ ጌታው፡ በተመለሰ፡ ጊዜ፡ ከንጉሥ፡ ብዙ፡ ሞገስን፡ አገኘ፡ እነዚያንም፡ አስታረቀ። የመንግሥትም፡ ሰዎች፡ ይህን፡ ያህል፡ ዘመን፡ ብዙ፡ ሰዎችን፡ ያስገደለች፡ አምባ፡ ሽሮ፡ ሽፍቶችንም፡ ማርኮ፡ ወዳገሩ፡ | መመለሱን፡ አይተው፡ ሰምተውም፡ አደነቁ፡ እጅግም፡ አከበሩት። ክፉይቱ፡ ቅንዓት፡ ያደረችባቸው፡ ግን፡ አዘኑበት፡ ነቀፉትም። |
chapter ()
Alignment Start a translation alignment with Alpheios Alignment. You can also add morphological annotations there. See instructions in GitHub.
Versions See parallel versions if any is available
Quotations Check for marked up quotations of a passage in this section
back to top
፫ኛ፡ ክፍል። | ባ፭ኛው፡ አኃዝ፡ እንዳየነ፡ ሙሴ፡ ሌዢአን፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ወደ፡ ምስር፡ በመመለሳቸው፡ ነቅፈዋል። እግዜር፡ መግራት፡ ሃይማኖትም፡ የሌለው፡ ሳይመረምር፡ በሰው፡ ላይ፡ መፍረድ፡ ልማዱ፡ ነው። መጻፋቸውን፡ የምታነብ፡ ወንድሜ፡ ሆይ፡ አንተም፡ እንደርሳቸው፡ በጌታችን፡ በየሱስ፡ ክርስቶስ፡ በከበሩ፡ መልእክተኛ፡ ላይ፡ እንዳትሳደብ፡ ምክንያቱን፡ እገልጥልኃለኍ። መዠመርያ፡ ምክንያት፡ እንዲህ፡ ነው። የእስክንድርያ፡ ሊቀ፡ ጳጳሳት፡ ዲዮስቆሮስ፡ እንደ፡ ምዕራብ፡ ቍጥር፡ ከሥጋዌ፡ በኋላ፡ ባ፬፻፶፩ ዓመት፡ኬልቄዶን፡ ጉባዔ፡ ተገዝቶ፡ እ | ንደ፡ ተለየ፡ ታውቃለህ። ከርሱም፡ በኋላ ፡ በ፪፻፷፩ ዓመት፡ ይመስለኛል፡ አባ፡ ብንያሚን፡ ግብጽ፡ ሊቀ፡ ጳጳሳት፡ ተባለ። እርግጡን፡ አላወቅሁም፡ እንጂ፡ መናፍቅ፡ ጳጳስ፡ ወዳገራችን፡ መግባት፡ ከርሱ፡ ወይ፡ በርሱ፡ ጊዜ፡ ተዠመረ፡ ይላሉ። ካባ፡ ብንያሚን፡ ዠምሮ፡ ግን፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ። ወዳገራችን፡ እስከገቡበት፡ ድረስ፡ ፲፩፻ ከ፷ ዓመት፡ ይሆናል። ነገር፡ ግን፡ ባክሱም፡ ያለ፡ ታሪከ፡ ነገሥት፡ ከጌታችን፡ ልደት፡ በኋላ፡ ባ፲፬፻፴፩ኛ፡ ዓመት፡ በነበሩ፡ ባጼ፡ ዘርአ፡ ያዕቆብ፡ ጊዜ፡ ወበመንግሥቱ፡ ኮነ፡ ተቃሕዎ፡ በእንተ፡ ሃይማኖት፡ ወተዋሥአ፡ አባ፡ ጊዮርጊስ፡ ምስለ፡ አፍርንጂ፡ ይላልና፡ የሮማ፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ሰባክያንን፡ መስደድ፡ ከዚያ፡ በፊት፡ ወይም፡ ከዚያ፡ ዠምሮ፡ እስከዚህ፡ ድረስ፡ አላረፈችም። ነገር፡ ግን፡ ቅዱስ፡ ጴጥሮስ፡ ስን | ኳ፡ እግዚኦ፡ ግሙራ፡ ኢቦአ፡ ርኩስ፡ ብሎ፡ እንደ፡ ተከራከረ፡ ልማድ፡ ከሁለት፡ የበረታች፡ ናት። የኢትዮጵያ፡ ክርስቲያን፡ ወደ፡ እውነተኛይቱ፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ እንዲመለሱ፡ የከለከላቸው፡ ምክንያት፡ ፩ ኑፋቄው፡ የገባበት፡ የዘመን፡ ብዛት፤ ፪ኛም፡ ጭራሽ፡ ያገራችንን፡ ሰዎች፡ ልብ፡ ያጠና፡ ካቡነ፡ አልፎንሱስ፡ ማንደዝ፡ የካቶሊክ፡ ጳጳስ፡ ጋራ፡ ባ፲፮፻፲፯ ዓመተ፡ ሥጋዌ፡ የመጡ፡ የየሱሳውያን፡ ወገን፡ አባ፡ ሎቦ፡ በጻፉት፡ ያገራችን፡ ታሪክ፡ መጻፍ፡ በ፻፲፬ኛ በ፻፲፭ኛ፡ ገጽ፡ ካቶሊካዊት፡ ሃይማኖት፡ እንድትታመን፡ ያጼ፡ ሶስንዮስ፡ አዋጅና፡ ሹም፡ በግዛታቸው፡ ሁሉ፡ እንደ፡ ተደረገ፡ ይናገራል። በዚህ፡ ምክንያትና፡ የቤተ፡ ክርስቲያናችኍንም፡ ሥራት፡ ሁሉ፡ እንደ፡ ላቲን፡ አድርጉ፡ በማለት፡ የሆነን፡ ሁከት፡ የፈሰሰንም፡ ደም፡ ለመጻፍ፡ አይቻለኝም። ስ | ለዚህ፡ ያገራችን፡ ሰዎች፡ አንድ፡ ኤውሮፓዊን፡ ሲያዩ፡ ፊትህ፡ ይጥፋ፡ ይህ፡ የደመኞቻችን፡ ወገን፡ አይዶለምን፡ ስለምን፡ ደግሞ፡ ወዳገራችን፡ መጣ፡ እያሉ፡ እስከ፡ ዛሬ፡ ድረስ፡ ይራገማሉ። ፫ኛም፡ ሙሴ፡ ሌዜአን፡ በመጻፋቸው፡ እንዳሉ፡ የፕሮተስታንቲ፡ ወገን፡ ሙሴ፡ ሳሙኤል፡ ጉባ፡ በነዚያ፡ ቍጥር፡ ባ፲፷፻፴ ዓመተ፡ ሥጋዌ፡ ወዳገራችን፡ መጡ። ከርሳቸውም፡ በኋላ፡ ሙሴ፡ ኢዘንበርግና፡ ሌሎች፡ ፕሮተስታንቲ፡ መጡ። ባድዋ፡ መድኃኔ፡ ዓለም፡ ባሰም፡ በወንዙ፡ ዳርቻ፡ በብዙ፡ ወገን፡ የተከፋፈለን፡ ታላላቅ፡ ቤት፡ ሠሩ። ስለ፡ ስጦታቸው፡ ብዛት፡ ከገዞቹና፡ ከሹማምንቱ፡ ጋራ፡ ተሰማምተው፡ የነበሩ፡ ይመስለኛል። ይህም፡ ኑፋቄያቸውን፡ በግልጥ፡ እንዲናገሩ፡ አስደፈራቸው። ካህናቱና፡ ሕዝቡ፡ ይልቁን፡ በእግዝእትነ፡ ማርያም፡ ላይ፡ በመሳደባቸው፡ ተናደዱባቸው። ስለዚህ፡ አለቃ፡ ዕ | ንቈ፡ ሥላሴ፡ ከሳሻቸው፡ ሆኑ። ከነዚያም፡ በኋላ፡ በነዚያ፡ ቍጥር፡ ባ፲፰፻፴፱ኝ፡ ዓመተ፡ ሥጋዌ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ካገረዎ፡ ወዳገራችን፡ መጡ። ባድዋ፡ መድኃኔ፡ ዓለም፡ ተቀመጡ። መልካቸው፡ አንድ፡ ስለ፡ ሆነ፡ በሕዝቡ፡ ፊት፡ ከፕሮተስታንቶች፡ ተለይተው፡ አልታወቁም። ነገር፡ ግን፡ ተካህናቱ፡ አንዳንድ፡ ወደ፡ ቤትዎ፡ ሲሔዱ፡ ነበሩና፡ እርስዎም፡ ቅዳሴ፡ ከተጨረሰ፡ በኋላ፡ በእሑድ፡ ቀን፡ ወደ፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ይመጡ፡ ነበሩና፡ ያዕቆብ፡ የሚባለውስ፡ በቤቱ፡ |እግዝእትነ፡ ማርያም፡ ዕል፡ መስቀልም፡ በምኝታው፡ ላይ፡ ሰቅሎዋል፡ ክርስቲያን፡ ነው፡ ይሉ፡ ነበሩ። ሹማምቶችና፡ ታላላቆች፡ ነነ፡ የሚሉቱ፡ ግን፡ ከፕሮተስታንቲ፡ ተመክረው፡ ወይም፡ በፈቃዳቸው፡ ቢሆን፡ አላወቅሁም፡ ገንዘብ፡ ስጡነ፡ እያሉ፡ ሲያስጨንቁም፡ ነበሩ። እንግዲህ፡ እውነትን፡ የምትሻ፡ ወንድሜ፡ ሆይ፡ ስለማስ | በርትተዋልና፡ እንዲጠብቀን፡ አባ፡ ያዕቆብን፡ ካልሰጡን፡ በሁሉ፡ ያስጨንቁናል፡ ብለው፡ ነገሩ። ደጃዝማች፡ አባታችንን፡ ካድዋ፡ ወደ፡ ሰፈርዎ፡ አስጠርተው፡ ጳጳስን፡ ለማስመጣት፡ ፈልጌ፡ አለኍና፡ ሰዎቼንና፡ ዕቃውን፡ ለመጠበቅ፡ እስከ፡ ምስር፡ ድረስ፡ እንድትሔድልኝ፡ እለምንሃለኍ፡ አሉዎ። አባታችን፡ ይህነን፡ ሰምተው፡ እጅግ፡ ተጨነቁ። እሺ፡ ቢሉ፡ የምትመጣብዎን፡ ነቀፋ፡ አይሆንልኝምም፡ ቢሉ፡ ከገዡ፡ የምትመጣብዎን፡ መከራ፡ አሰቡ። አይሆንም፡ ቢሉ፡ የመናፍቅ፡ ጳጳስ፡ ወደ፡ ኢትዮጵያ፡ ባልመጣም፡ ነበር፡ እንዳንልም፡ ከዚህ፡ በላይ፡ እንዳየነ፡ ካባ፡ ብንያሚን፡ ዘመን፡ ዠምሮ፡ እስካቡነ፡ ቄርሎስ፡ ድረስ፡ ያለርስዎ፡ እንደመጣ፡ እንዲሁም፡ ሊመጣ፡ ነበረ። ለርስዎ፡ ምንም፡ ሌላ፡ መከራ፡ ባይመጣብዎ፡ አገሬን፡ ልቀቅልኝ፡ ማለት፡ የስብከትም፡ መዘጋት፡ ሊሆን፡ እንደ፡ ነበረ፡ የታወቀ፡ ነው። በንደዚህ፡ ያለ፡ ጭ | ንቅ፡ ጨለማ፡ ለተከበበ፡ ልብ፡ ግን፡ የሚያበራ፡ እምኀበ፡ አቡሃ፡ ለብርሃን፡ ከብርሃን፡ ባለቤት፡ እንዳለ፡ ከሰማይ፡ የመጣች፡ ካልሆነች፡ በተፈጠረች፡ በአእምሮ፡ ብርሃን፡ ብቻ፡ መለየቱ፡ የማይቻ፡፡ ነበረ። ዳግመኛም፡ በዚያ፡ ጊዜ፡ ከወንድሞችዎ፡ ጋራ፡ እንዳይማከሩ፡ አንድስንኳ፡ ከርስዎ፡ ጋራ፡ አልነረም። በፍጹም፡ ልብዎ፡ የሚወዱዋትና፡ የሚገዙላትን፡ የብርሃንን፡ እናት፡ አማላጅ፡ አድርገው፡ በጌታዎ፡ ፊት፡ ወድቀው፡ በጸለዩ፡ ጊዜ፡ ከእግዜር፡ የተላከ፡ መልአክ፡ ፊልጶስን፡ ሑር፡ ትልዎ፡ ለዝ፡ ሠረገላ፡ (ግብረ፡ ሐዋ፡ ፰ ፳፱) እንዳለው፡ ለርስዎም፡ እንዴሁ፡ ሆነ። መልእክተኞችን፡ አለመከተል፡ ለኢትዮጵያ፡ ጨለማን፤ ቢከተሉ፡ ግን፡ ብርሃንን፡ እንድታመጣ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ በልብዎ፡ ውስጥ፡ ገለጠልዎ። ያገራችን፡ ሰዎች፡ ቅዱስ፡ ፊልጶስ፡ ባጠመ ቀው፡ በኀሰዋ፡ ለህንደኬ፡ ምክንያት፡ ወዳገራችን፡ ጥምቀት፡ ገብታ፡ ነበረች፡ ይላሉ። ነገር፡ | ነገር፡ ግን፡ ሲያነበው፡ የነበረን፡ ቅዱስ፡ መጻፍ፡ ምስጢሩን፡ ሳያውቀው፡ እንደ፡ ነበረ፡ ያመጣት፡ ቅድስት፡ ጥምቀትም፡ ዓይነተኛ፡ ሹም፡ ሐዋርያዋ፡ እስኪመጣላት፡ ድረስ፡ አልሰፋችም፡ ነበረች። በመጽሐፈ፡ ነገሥትና፡ በወንጌል፡ የተጠራቸው፡ የዓዜብ፡ ንግሥት፡ ስምዋም፡ ማክዳ፡ የተባለ፡ ጥበብን፡ ፈልጋ፡ ጥበበኛውን፡ ሰሎሞን፡ ለመገናኘት፡ እስከ፡ የሩሳሌም፡ ድረስ፡ ከሔደች፡ ስትመለስም፡ እግዜርን፡ ማምለክ፡ ተቀብላ፡ እንደ፡ መጣች፡ ርግጥ፡ ይመስላል። ታሪከ፡ ነገሥት፡ ግን፡ ምንይልክ፡ ልጅዋ፡ ካባቱ፡ ከሰሎሞን፡ የኦሪትን፡ ሕግ፡ ተቀብሎ፡ ወደናቱ፡ እንደ፡ ተመለሰ፡ ወውእቱ፡ ወጽአ፡ ምድረ፡ ኢትዮጵያ፡ ምስለ፡ ፲ወ፪ ሕግ፡ ይላል። ከርሱም፡ በኋላ፡ ያገራችን፡ ሰዎች፡ የነቢያትን፡ መጻሕፍት፡ ተቀብለው፡ እንደ፡ ነበሩ፡ ቅዱስ፡ ሉቃስ፡ በግብረ፡ ሐዋርያት፡ ገለጠ። ዳግመኛም፡ ታሪ | ከ፡ ነገሥት፡ ወሕዝበ፡ ኢትዮጵያ፡ ቦእለ፡ ነበሩ፡ እንዘ፡ ያመልኩ፡ ዓርዌ፡ ወቦ፡ እለ፡ ሀለው፡ በሕገ፡ ኦሪት፡ ወእምዝ፡ መሀሮሙ አቡነ፡ ሰላማ፡ ዜና፡ የሱስ፡ ክርስቶስ። ወገብረ፡ ተአምራተ፡ ወመንክራተ፡ በቅድሜሆሙ፡ አምኑ፡ ወተጠምቁ፡ ጥምቀተ፡ ክርስትና። ወእምነቶሙሰ፡ ኮነ፡ እምልደተ፡ ክርስቶስ፡ በ፫፻ወ፵ ዓመት፡ ይላል። ስንክሣር፡ ዘአመ፡ ፳ወ፮ ለሐምሌ፡ መጽአ፡ ፩ ብእሲ፡ እምነ፡ ብሔረ፡ ጽርዕ፡ ዘስሙ፡ ሜሮጵዮስ፡ ሊቀ፡ ጠበብት፡ እንዘ፡ ይፈቅድ፡ ይርአይ፡ ለብሔረ፡ ኢትጵያ፡ ወምስለሁ፡ ፪ ደቂቅ፡ እምአዝማዲሁ። ስሙ፡ ለ፩ ፍሬምናጦስ፡ ወለካልዑ፡ አድስዮስ፡ ወቦ፡ እለ፡ ይሰምይዎ፡ ሲድራኮስ።
ወጠመቶሙ፡ ሀገሮሙ፡ ፍሬምናጦስኒ፡ በጽሐ፡ እስክንድርያ፡ ኀበ፡ ሊቀ፡ ጳጳሳት፡ አባ፡ አትናቴዎስ።
ወዘከመ፡ አምኑ፡ በክርስቶስ፡ ሎቱ፡ | ስብሐት፡ እንዘ፡ አልቦሙ፡ ጳጳሳት፡ ወቀሳውስት። ወእምዝ፡ ሤሞ፡ አባ፡ አትናቴዎስ፡ ፍሬምናጦስ፡ ከመ፡ ይኩን፡ ጳጳስ፡ ለብሔረ፡ አግዓዚ፡ ዘኢትዮጵያ። ወፈነዎ፡ ምስለ፡ ዓቢይ፡ ክብር።
ወበእተዝ፡ ተሰምየ፡ አባ፡ ሰላማ፡ ይላል። ከሣቴ፡ ብርሃን፡ ሰላማ፡ ሳይመጡ፡ የብሉይ፡ ኪዳን፡ ቅዱሳት፡ መጻሕፍትና፡ ጥምቀት፡ ምንም፡ ላገራችን፡ ሰዎች፡ ቢኖሩዋቼው፡ ያለ፡ ፯ የኪዳን፡ ምስጢራትና፡ ያለ፡ ጳጳስ፡ ያለ፡ ቤተ፡ ክርስቲያናትም፡ ፍጹም፡ ብርሃን፡ አልነረም። ዳግመኛም፡ ታሪክ፡ እንዳለ፡ ሌሎቹ፡ ዘንዶን፡ ሲያመልኩ፡ ነበሩ። ቅዱስ፡ ፍሬምናጦስ፡ ግን፡ ከእስክንድርያ፡ ሊቀ፡ ጳጳሳት፡ ከቅዱስ፡ አትናቴዎስ፡ ተሹመው፡ በመጡ፡ ጊዜ፡ የጐደለን፡ ሁሉ፡ መሉ፡ አቀኑም። በዘንዶ፡ ላጋንንት፡ ስትደረግ፡ በነበረች፡ እጅግ፡ ክፉ፡ አምልኮ፡ ጨለማን፡ አርቀው፡ ኢትዮጵያን፡ ስላበሩ፡ ከፊጣሪዋ | ም፡ ጋራ፡ ስላስታረቁ፡ ከሣቴ፡ ብርሃን፡ ሰላማ፡ ተባሉ። ይህም፡ የቀደመው፡ ዘመን፡ ነገር፡ በዘመናችን፡ ለተደረገው፡ ይቀርባል። የእስክንድርያ፡ ሊቀ፡ ጳጳሳት፡ ዲዮስቆሮስ፡ ከቅድስት፡ ጉባዔ፡ ኬልቄዶን፡ ስለ፡ ተለየ፡ የግብጽ ና፡ የኢትዮጵያ፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ባሰተኛ፡ ትምርቱ፡ ጨለማ፡ ተጋረዱ። ካምላክም፡ ጋራ፡ ተጣሉ። ወንጌል፡ ለእመ፡ ኢሰምዓ፡ ለቤተ፡ ክርስቲያን፡ ይኩንከ፡ ከመ፡ ዓረማዊ፡ ያለውን፡ ረስተው፡ የተገዘተውን፡ አመኑ። እመቦ፡ ዘይተሉ፡ ኖላዌ፡ እኩየ፡ ሞቱ፡ ክሡት፡ (ፍትሐ፡ ነገሥት፡ አን፤ ፭ ድስቅ፡ ዘ፯) ያለውንም፡ እያወቁ፡ እርሱን፡ በመከተላቸው፡ ከጌታችን፡ ከየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ጋራ፡ በብርቱ፡ ተጣሉ። ከሰላም፡ ንጉሥ፡ ግን፡ የሸፈተ፡ ዕረፍትን፡ አያገኛትምና፡ በፊት፡ እርስ፡ በርሳቸው፡ ተጣልተው፡ በሃይማኖት፡ ወደ፡ ሶስት፡ ወገን፡ ተከፈሉ። ዳግመኛም፡ በትምርታቸው፡ ከግብጾች፡ እንዲበልጡ፡ ባዩ፡ ጊዜ፡ ከጳጳሳቸውብ፡ | ጋራ፡ ተጣሉ፡ በሃይማኖትም፡ ተለዩ፡ መዓርገ፡ ክህነትን፡ ብቻ፡ ልትሰጠን፡ አስመጣነው፡ እንጂ፡ ሃይማኖትን፡ ልታስተምረን፡ አይዶለም፡ አሉት። ዳግመኛም፡ በእጃቸው፡ ያሉቱ፡ ቅዱሳት፡ መጻሕፍትና፡ የሊቃውንቶችም፡ መጻሕፍቶች፡ የኒቅያ ና፡ የኤፌሶን ም፡ ጉባዔ፡ በጌታችን፡ በየሱስ፡ ክርስቶስ፡ አንድ፡ ፈጣሪ፡ አካል፡ ብቻ፡ እንዳለ፡ ሁለት፡ ባሕርያት፡ በዚኸው፡ በፈጣሪ፡ አካ፡፡ ተወሐዱ፡ እንጂ፡ ሁለት፡ አካላት፡ እንደሌሉት፡ እየነገሩዋቸው፡ አካል፡ ከአካል፡ ባሕርይም፡ ከባሕርይ፡ ጋራ፡ ተዋሕዶዋል፡ እያሉ፡ አንድ፡ አካል፡ አንድ፡ ባሕርይ፡ ይላሉ። የሁላችን፡ በርሱ፡ እግዜር፡ አኖረበት። ቀረበ፡ ተጨነቀም፡ አፉንም፡ አልገለጠም፡ እንደ፡ በግ፡ ወደ፡ መታረድ፡ ይሔዳል፡ እንደ፡ ጥቦትም፡ በሸላቹ፡ ፊት፡ ዝም፡ እንዲል፡ አፉን፡ አይከፍትም። ከመጨነት፡ ከፍርድም፡ ተነሣ። ተውልዱንም፡ ማን፡ ይነግርለታል፡ ሕይወቱ፡ | ከምድር፡ ተቈርጣለችና፡ ስለ፡ ወገኔ፡ ኃጢአት፡ ተቀሠፈ፡ ያለውን፡ የነቢይ፡ ኢሳይያስ፡ ቃል፡ (፶፫) ኅፅዋ፡ ለህንዳኬ፡ ቅዱስ፡ ፊልጶስ፡ እስኪተረጕምለት፡ ድረስ፡ ምስጢሩን፡ እንዳላወቀ፡ እነዚህም፡ የመድኃኒታችነን፡ የል ደቱን፡ ምሥጢር፡ እንደሚገባ፡ አላወቁም። ነገር፡ ግን፡ ጌታችን፡ መነሂ፡ ይብልዎ፡ ይኩን፡ ሰብእ፡ ለወልደ፡ እጓለ፡ እመሕያው፡ ብሎ፡ በጠየቀ፡ ጊዜ፡ ሌሎች፡ ሐዋርያት፡ ምሥጢሩን፡ አላወቁም። ቅዱስ፡ ጴጥሮስ፡ ግን፡ እግዜር፡ አብ፡ ገልጦለት፡ አንተ፡ ውእቱ፡ መሢሕ፡ ወልዱ፡ ለእግዚአብሔር፡ ሕያው፡ ብሎ፡ መለሰ። ማቴ፡ ፲፮ ፲፫ ፲፮። ዛሬም፡ ከርሱ፡ ቅድስት፡ ወምበር፡ የተለዩም፡ ያለ፡ ሁለት፡ አካላት፡ ባሕርያት፡ ሁለት፡ እንደሆኑ፡ አላወቁም። በወንጌል፡ ዮሐንስ፡ እምቅድመ፡ ይትወለድ፡ አብርሃም፡ ሃሎኩ፡ አነ፡ ያለው ፡ | ዳግመኛም፡ እስመ፡ አብ፡ የአብየኒ፡ ያለው፡ ይህነንም፡ የመሰለ፡ ሌላውን፡ ለ | ፈጣሪና፡ ለፍጡር፡ አካል፡ ከሰጡ፡ ልደቱን፡ በሚገባ፡ እንዳላስተማሩለት፡ ይታያል። ዳግመኛም፡ መወለድ፡ የአካል፡ ነውና፡ ፍጡሪቱ፡ ባሕርየ፡ ትሰብእት፡ በአካለ፡ ቃል፡ ልደትን፡ ከእግዜር፡ አብ፡ አገኘት። ስለዚህ፡ እኔ፡ ካባቴ፡ ጋራ፡ ትክክል፡ ነኝ፡ እኔ፡ ከአብ፡ አንሳለኍ፡ ማለት፡ ለእውነተኛው፡ ለፈጣሪ፡ አካል፡ ይገባል፡ እንጂ፡ ፍጡር፡ አካል፡ ከቶ፡ ከአብ፡ አልተወለደምና፡ እኔ፡ ከአብ፡ ጋራ፡ ትክክል፡ ነኝ፡ ወይም፡ እኔ፡ ካባቴ፡ አንሳለኍ፡ ማለቱ፡ ባሰት፡ ይሆናል። ከእግዜር፡ ጥበብን፡ ጻድቅነትን፡ ሥልጣንም፡ ያልተቀበለ፡ ነቢይ፡ ዳንኤል፡ ናቡክደኖጾርን፡ ንጉሡ፡ የሚጠይቀውን፡ ምሥጢር፡ ጠቢባንና፡ ከዋክብት፡ ቈጣሮች፡ አስማተኞችና፡ ምዋርተኞች፡ ለንጉሡ፡ ይነግሩት፡ ዘንድ፡ አችሉም፡ (፪ ፳፯) እንዳለ፡ እንደሻው፡ ሊኖር፡ ከቅዱስ፡ ጴጥሮስ፡ ወምበር፡ የተለየም፡ ይህነን፡ ምሥጢር፡ ሊያውቅ፡ እንዳይቻለው፡ ርግጥ፡ ነው። | ስለዚህ፡ ምስጋና፡ ይግባውና፡ አምላካችን፡ ግን፡ ይህነን፡ ብርሃን፡ እንዲገልጥልን፡ እንደፊተኛው፡ ያሉ፡ ከሣቴ፡ ብርሃን፡ ሰላማን፡ ሊያስመጣልን፡ ወደ፡ ደጃዝማች፡ ውቤን፡ በዚያ፡ ዘመን፡ አቡንን፡ ለማስመጣት፡ አንቀሳቀሰ፡ መናፍቁና፡ ካቶሊኩ፡ ጳጳስም፡ ባንድጊዜ፡ ባገራችን፡ ባይታዩ፡ መልካሙን፡ ተክፉው፡ መለየት፡ አይቀናም፡ ነበርና፡ ፍሬምናጦስ፡ በፊት፡ መጥቶ፡ ኋላ፡ ወዳገሩ፡ እንደ፡ ተመለሰ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብም፡ ኢትዮጵያን፡ አምልኮ፡ ለማቅናት፡ ከመልእክተኞቹ፡ ጋራ፡ ወደ፡ ምስር፡ ለመመለስ፡ የግዜር፡ ፈቃድ፡ ስለ፡ ሆነ፡ ከገዡ፡ ተለመኑ። መንፈስ፡ ቅዱስም፡ ቀድሞ፡ ሑር፡ ትልዎ፡ ለዝ፡ ሠረገላ፡ እንዳለ፡ ኋላም፡ እኒህን፡ መልእክተኞች፡ መከተል፡ አትፍራ፡ የሚልን፡ ስለ፡ ገለጠልዎ፡ ባንድ፡ ሔዱ። መልእክተኞች፡ ወደ፡ ግብጽ፡ ደርሰው፡ ጳጳስ፡ የሚሆን፡ ይህ፡ የኽያ፡ ፪ ወይ፡ የኽያ፡ ዓራት፡ ዓመት፡ ልጅ፡ እንድ | ርያስ፡ ነው፡ ብለው፡ ቢያሳዩዋቸው፡ በፊት፡ ሁሉ፡ እንዴት፡ ይህነን፡ እንሾማለን፡ ብለው፡ አደነቁ። አለቃ፡ ሐብተ፡ ሥላሴ፡ የመልእክተኞቹ፡ አለቃ፡ በትረክ፡ ጴጥሮስ፡ አባታችን፡ ሆይ፡ ባገራችን፡ ሃይማኖት፡ ቢሆን፡ በሌላም፡ ቢሆን፡ ብዙ፡ ጠብ፡ አለና፡ የሚያሰማማን፡ ሽማግሌ፡ መንፈሳዊ፡ ጥበበኛም፡ ሰው፡ ልትሾምልን፡ እንለምንሃለን፡ አሉ። በትረክም፡ ለጊዜው፡ አላውቀውም፡ እንዴት፡ ይህነን፡ አሽከር፡ አሾማለኍ፡ አለ። ኋላ፡ የእንድርያስ፡ መምር፡ ሊዬደር፡ ፀረ፡ ማርያም፡ እጁን፡ ወይም፡ ከረጢቱን፡ ስለ፡ መላለት፡ በፊትም፡ እንዳየነ፡ ሙሴ፡ ሌዢአን፡ እንዳሉ፡ የእንግሊዝ፡ ኮንሱል፡ ስለ፡ ለመነው፡ በነገታው፡ መልእክተኞችን፡ አስጠርቶ፡ እንዲዚህ፡ ያለ፡ መልካም፡ አሽከር፡ የለም። እርሱን፡ ነው፡ የምሾምላችኍ። የርሱ፡ ክፋት፡ በራሴ፡ ላይ፡ ነው፡ አላቸው። ሌሎች፡ በየልባቸው፡ ታ | ዝበውት፡ ዝም፡ አሉ። ለእውነት፡ እጅግ፡ የቀኑ፡ የሚናደዱም፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ግን፡ ትላንትና፡ አላውቀውም፡ አልኸነ። ባንዲት፡ ሌሊትን፡ ጥበቡን፡ ምግባሩን፡ አወቅኸው፡ አሉ። ነገር፡ ግን፡ እንደ፡ እንግሊዞች፡ ተረት፡ ነገርን፡ ብትፈልግ፡ ክፈል፡ ይላሉና፡ መልእክተኞችን፡ በሁለት፡ ከፈሉዋቸው። እስከ፡ ሁለት፡ ወር፡ የሚሆን፡ በዚህ፡ ነገር፡ ምክንያት፡ እርስበርሳቸው፡ ከግብጾችም፡ ጋራ፡ ተጣሉ። ኁላ፡ ግን፡ አይሆንም፡ ያሉቱ፡ አለቃ፡ ሐብተ፡ ሥላሴና፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ተሸንፈው፡ እንድርያስ፡ ጐበዝ፡ ተሾመ፡ መሾሙ፡ ግን፡ በኢሰላም፡ እንደሆነች፡ እያዩ፡ መልእክተኞች፡ ስሙ፡ ሰላማ፡ ይሁንልን፡ ስላሉ፡ አቡነ፡ ሰላማ፡ ተባሉ። ነገር፡ ግን፡ ስም፡ ያለ፡ ግብር፡ ከንቱ፡ ናትና፡ ይህነን፡ ስም፡ በዚያ፡ ለነበሩ፡ ለሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ እንደሆነ፡ ኋላ፡ በማመጣው፡ ይታውቃል። እንግዴህ፡ በዚያ፡ ዘመን፡ የተደረገ፡ ነገር፡ ሁሉ፡ በው | ጭ፡ የግብጽ ን፡ ጳጳስ፡ ለማስመጣት፡ ነው። በውስጥ፡ ግን፡ ኢትዮጵያን፡ ከጌታችን፡ ከኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ጋራ፡ ለማስታረቅ፡ ከእውነተኛይቱም፡ እናትዋ፡ ከቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ካቶሊካዊት፡ ሐዋርያዊት፡ ሮማዊት፡ ጋራ፡ እንዲያስታርቁ፡ ከጌታችን፡ ከየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ምስለኔ፡ በስም፡ ፲፮ኛ፡ ጎርጎርዮስ፡ የተላኩ፡ ሁለተኛ፡ ሰላማ፡ ከሣቴ፡ ብርሃን፡ ለማስመጣት፡ ሆነ። እነሆ፡ ሶስቱ፡ መልእክተኞችና፡ ሌሎቹ፡ ወደ፡ ሮማ፡ ከደረሱ፡ በኋላ፡ ከብፅዕ፡ አባታችን፡ ጎርጎርዮስ፡ ተገናኝተው፡ ሲሰናበቱ፡ አባታችን፡ ሆይ፡ መምርን፡ ስጠነ፡ ብለው፡ ለመኑ። እጅግ፡ የተቀደሰችን፡ እጁን፡ ወደ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ዘርግቶ፡ እነሆ፡ እርሱ፡ ነው፡ መምራችኍ፡ ከናንተ፡ ጋራ፡ ይመለሳል፡ አላቸው። | ይህን፡ ሊታወቅ፡ ከደጃዝማች፡ ውቤ፡ ለምነው፡ እሺ፡ ይሁንልህ፡ ያሉዎ፡ | ነገር፡ መዠመርያ፡ የመላ፡ | ባታችነም፡ በዚያ፡ ጊዜ፡ እንዳንድ፡ መንገደኛ፡ ሰው፡ ሲያዩ፡ ከነበረቱ፡ ገዢ፡ ይህነን፡ እሺታና፡ መልእክት፡ መገኘቱ፡ እጅግ፡ ያስደንቀኛል። ሰይጣን፡ በብልሃቱና፡ በተንኰሉ፡ ይህችን፡ ያባታችንን፡ ጥበብ፡ አውቆ፡ እንዲያፈርሱዋት፡ ለሁለቱ፡ ወገኖች፡ ወዳጆቹ፡ ነገረ። ይህም፡ ሊታወቅ፡ አባታችን፡ ከመልእክተኞች፡ ጋራ፡ ወደ፡ ምስር፡ በደረሱ፡ ጊዜ፡ ግብጾችና፡ ፕሮተስታንቲ፡ መልእክተኞች፡ ወደ፡ ሮም፡ እንዳይሔዱ፡ ብዙ፡ ተንኰልንና፡ አሰትን፡ አደረጉ፡ ተናገሩም። በምስር፡ በዚያ፡ ጊዜ፡ የነበረ፡ የግብጾች፡ በትረክ፡ አባ፡ ጴጥሮስ፡ ይባላል። ዳግመኛም፡ ግብጾች፡ ሳዊሮስ፡ ዘእስሙናይን፡ ባ፲ኛ፡ ድርሳኑ፡ ይፈቅዱ፡ ነገሥተ፡ ዮናናውያን፡ ይወልጡ፡ ሃይማኖተ፡ እምኔሆሙ፡ መጠው፡ ነፍሶሙ፡ ለነገሥተ፡ ዓረብ፡ ተንባላት፡ እንዳለ፡ የኬልቄዶን፡ ጉባዔ፡ ሃይመኖት፡ እንዳይቀበሉ፡ ቀድሞ፡ ከ | እስላሞች፡ ጋራ፡ እንደ፡ ተማማሉ፡ በኋላ፡ ዘመንም፡ ጥግ፡ እንዲሆኑዋቸው፡ ከፕሮተስታንቶች፡ ጋራ፡ አንድነት፡ አድርገዋል። ስለዚህ፡ ሊዬዳር፡ የሚባል፡ የፕሮተስታንቶች፡ መምር፡ የግብጻውያን፡ ልጆች፡ የሚያስተምር፡ በትረክ፡ ጴጥሮስ፡ ባጠገቡ፡ ቤትን፡ ሰጥቶት፡ በዚያ፡ ዘመን፡ ከዚያ፡ ነበረ። እንድርያስ፡ የሚባል፡ የ፳፪ወይ፡ የ፳፬ት፡ ዓመት፡ ጐበዝ፡ ከርሱ፡ የተማረ፡ ግብጻዊ፡ ብላቴና፡ ነበረ። በትሪክ፡ በፊት፡ እርሱን፡ አሽከር፡ ነው፡ እንዴት፡ ለዚህ፡ ጳጳስናን፡ እሾማለኍ፡ ብሎ፡ አይሆንም፡ አለ። ኋላ፡ ግን፡ መምሩ፡ ሊዬዳር፡ ሙሴ፡ ሌዢአንም፡ እንዳሉ፡ በምስር፡ የነበረ፡ ኮንሱል፡ እንግሊዝ፡ አሾሙት። አቡነ፡ ሰላማ፡ የተባሉ፡ እርሳቸው፡ ናቸው። ከተሾሙ፡ በኋላ፡ የመልእክተኞችቹ፡ አለቃ፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ ሐብተ፡ ሥላሴ፡ ውል፡ አለንና፡ ወደ፡ ሮም፡ ልንሔድ፡ ነነ፡ ቢሉ፡ በትረክ፡ ልጆቼ፡ ሆይ፡ ወደ፡ ሮም፡ ከመሔድ፡ | እስላም፡ መሆን፡ ይሻላችኋል። ምን፡ ልታዩ፡ ትሔዳለችኍ፡ በዚያ፡ እስከ፡ እኩል፡ ቀን፡ ድረስ፡ መነኵሴ፡ ከዚያ፡ በኋላ፡ ግን፡ ከምሽቱ፡ ጋራ፡ የሚታይን፡ ሰው፡ ልታዩን፡ ትደክማለችኍ። ከቶ፡ ወደዚያ፡ እንዳትሔዱ፡ ብሎ፡ ገዘታቸው። ዳግመኛም፡ ነገርን፡ ብትፈለግ፡ ክፈል፡ የሚል፡ ተረት፡ በእንግሊዞች፡ አለ፡ ይላሉና፡ መልእክተኞችን፡ በሁለት፡ ከፈልዋቸው። ከ፮ት፡ ለ፫ቱ፡ ፵፵ ብር፡ ሰጥተው፡ አንወድም፡ እንዲሉ፡ አደረጉዋቸው። እነዚሁም፡ ከዚህ፡ በላይ፡ የተጠሩ፡ ባላምበራስ፡ ኪዳነ፡ ማርያምና፡ አባ፡ እንግዳ፡ አባ፡ ገብረ፡ ሕይወትም፡ ናቸው። ሶስቱ፡ ሌሎችም፡ አንዱ፡ የመልእክተኞች፡ አለቃ፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ ሀብተ፡ ሥላሴ፤ ሁለተኛም፡ ኋላ፡ ስለ፡ ካቶሊክ፡ ሃይማኖት፡ የሞቱ፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፤ ሶስተኛም፡ የደጃዝማች፡ ውቤ፡ የነፍስ፡ አባት፡ ርእሰ፡ ደብር፡ ወልዱ፡ ናቸው። እኑህ፡ የኢሩሳሌምን፡ ሊስሙ፡ ከምስር፡ ሲነሡ፡ ከዚያ፡ ተመልሰው፡ እስኪመጡ፡ | ድረስ፡ በላዕላይ፡ ግብጽ፡ እንዲቈዩዋቸው፡ አቡነ፡ ሰላማንና፡ ሶስቱን፡ ወንድሞቻቸውን፡ አምለው፡ ነበሩ። እነዚያ፡ ግን፡ ማላቸውን፡ ከድተው፡ ካቡን፡ ጋራ፡ ወዳገራችን፡ ተነሡ። ከሥጋዌም፡ በኋላ፡ ባ፲፰፻፴፫ኛ፡ ዓመት፡ በጥቅምት፡ ወደ፡ አዳቡን፡ ገቡ። ስለዚህ፡ ሙሴ፡ ሌዢአን፡ ሙሴ፡ ደዢቆብ፡ አቡነ፡ ሰላማን፡ መርቶ፡ ፩ ወደ፡ ትግሬ፡ መጣ፡ ማለታቸው፡ ውሽት፡ ነው። እንግዴህ፡ እናለቃ፡ ሀብተ፡ ሥላሴ፡ ወደ፡ የሩሳሌም፡ ሊሔዱ፡ ወደ፡ እስክንድርያ፡ በደረሱ፡ ጊዜ፡ ዕምቢታቸው፡ በእግዚእትነ፡ ማርያም፡ አማላጅነት፡ በእግዜር፡ ኃይል፡ ተለወጠች። ከጥበብዎ፡ የምትበልጥ፡ የትዕግሥት፡ ብዛት፡ በሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ልብ፡ ነበረች። ውላቸውን፡ ካፈረሱብኝ፡ ሰዎች፡ እንግዴህ፡ ምናለኝ፡ ሳይሉ፡ ወደ፡ የሩሳሌም፡ ሊወስዱዋቸው፡ በ፻፳ ብር፡ መርከብ፡ ተከራይተው፡ ሳሉ፡ እንግዶች፡ ወዳንዲት፡ ወይዘሮ፡ በእስ | ክንድርያ፡ የነበረ፡ የቶስካና፡ ኮንሱል፡ ምሽት፡ ቤት፡ ተጠሩ። ይህች፡ የከበረች፡ ሴት፡ | እግዜርን፡ የምትፈራ፡ መንፈሳዊት፡ ነበረችና፡ የርስዋን፡ ቃል፡ እንደ፡ እግዝእትነ፡ ማርያም፡ ቃል፡ ስለ፡ ሰሙ፡ ባንደግዜ፡ ልባቸው፡ ተለወጠ፡ እንግዴህ፡ ወደ፡ ሮም፡ ይውሰዱን፡ አሉዎ። እርስዎም፡ እሺ፡ ብለው፡ እስከ፡ ሮም፡ አደርሱዋቸው። መልእክተኞች፡ ከነዚያም፡ ጋራ፡ ፳፫ት፡ የሚሆኑ፡ ሰዎች፡ ወደዚያ፡ ደርሰው፡ ያምልኮን፡ ሥራትና፡ የቅዱሳን፡ ሐዋርያት፡ ጴጥሮስና፡ ጳውሎስ፡ ቤተ፡ ክርስቲያኖችን፡ ማየት፡ ለ፫ቱ፡ ባለቤቱ፡ ወምበርን፡ አቅርቦላቸዋልና፡ ይልቁንም፡ በስም፡ ፲፮ኛ፡ ጎርጎርዮስ፡ ስለርሳቸው፡ የደረገውን፡ እጅግ፡ የሚያስደንቅን፡ ትሕትናን፡ፍቅርን፡ አይተው፡ እጅግ፡ አደነቁ። ዳግመኛም፡ በነሐሴ፡ በመቤታችን፡ በፍልሰታ፡ በዓል፡ እንዳባትነቱ የጌታችን፡ ምስለኔም፡ እንደ፡ መሆኑ፡ ከልጆቹ፡ ክብርን፡ ሲቀበል፡ አይ | ተው፡ በዚያ፡ ታላቅ፡ ቤተ፡ ክርስቲያንም፡ የመላው፡ ሕዝብ፡ በየማርጉ፡ በጸጥታ፡ መኖሩን፡ ሲለጠጥም፡ ሁሉ፡ እንዳንድ፡ ሰው፡ ባንድግዜ፡ መስገዳቸውን፡ ደረታቸውንም፡ እየደቁ፡ ዕንባን፡ ማፍሰሳቸውን፡ አይተው፡ በእውነት፡ እኒህ፡ ሰዎች፡ ክርስቲያኖች፡ ናቸው፡ ብለው፡ አደነቁ። መጽሐፈ፡ ነገሥት፡ ቀዳማዊ፡ እርሱም፡ ፫ኛ፡ የሚሆን፡ ባ፲ኛ፡ ምዕራፍ፡ የዓዜብ፡ ንግሥት፡ ካገርዋ፡ ወደ፡ የሩሳሌም፡ መጥታ፡ የሰሎሞንን፡ ጥበብ፡ የሎላልቱንም፡ መሠራት፡ ልብሳቸውንም፡ የጸጅ፡ አሳላፎቹን፡ አቋቋም። አይታ፡ ከዚያ፡ በኋላ፡ ነፍስ፡ አልቀረላትም፡ እንዳለ፡ የግዛትዋ፡ ሰዎችም፡ በኋላ፡ ዘመን፡ ከሰሎሞን፡ ይልቅ፡ ወደሚበልጠው፡ ወደ፡ ጌታችን፡ ምስለኔ፡ ቀርበው፡ ሥራውንና፡ ፍቅሩን፡ ባይናቸው፡ ስላዩ፡ እጅግ፡ ደሳላቸው። ጠላት፡ ስለርሱ፡ የነገራቸውም፡ ሁሉ፡ ውሽ | ት፡ እንደሆነ፡ አዩ። አለቃ፡ ሐብተ፡ ሥላሴ፡ ልጄ ፡ አፈ፡ ወርቅ፡ ባይሆንብኝ፡ ዳግመኛም፡ የቍራ፡ መልእክተኛ፡ የማልባል፡ ብሆን፡ ከሮም፡ ወጥቶ፡ ወደ፡ ኢትዮጵያ፡ ተመልሶ፡ መምጣት፡ ከመንግሥተ፡ ሰማይ፡ ወደ፡ ገሃነበ፡ እሳት፡ እንደ፡ መውረድ፡ ያለ፡ ነው፡ አሉ። መልእክተኞች፡ በሔዱ፡ በ፲፮ ወር፡ ወዳገራችን፡ ተመለሱ። ይልቁንም፡ ሲሔዱና፡ ሲመለሱ፡ ያባታችንን፡ ፍቅርንና፡ ትዕግሥትን፡ ትሕትናን፡ አይተው፡ እጅግ፡ አደነቁ። ወዲያ፡ ሊሄዱ፡ በጀልባ፡ ከምጥዋ፡ ከተጫኑ፡ በኋላ፡ አንድ፡ ቀን፡ ባሕረኞች፡ ያገራችነን፡ ሰዎች፡ አጥቅተው፡ ተጣሉዋቸው፡ ረገጡዋቸውም። ወደ፡ የሩሳሌም፡ የሚሔዱቱ፡ በዚያ፡ የነበሩቱ፡ ከ፷ የሚበዙ፡ መነኮሳት፡ ነበሩና፡ ወንድሞቻቸው፡ ሲበደሉ፡ አይተው፡ ሁሉ፡ በእስላሞች፡ ላይ፡ ተነሡባቸውአባታችን፡ በፊት፡ እስላሞችን፡ አስታግሠው፡ ካበረዱ፡ በኋላ፡ መነኮሳ | ቱን፡ ወንድሞቼ፡ ሆይ፡ ጌታችን፡ ስለኛ፡ መከራን፡ እንደ፡ ተቀበለ፡ ሳታስቡ፡ ሳትታገሡም፡ የሩሳሌምን፡ መሳም፡ ምን፡ ይጠቅማችኋል፡ እያሉ፡ ከቅዱሳት፡ መጻሕፍትም፡ እየጠቀሱ፡ ገሠፁዋቸው። እነዚያም፡ አደነቁ። እረግ፡ እኒህ፡ ሰው፡ ክርስቲያን፡ ናቸውሳ፡ ተባባሉ። ሊቀ፡ ካህናት፡ ሀብተ፡ ሥላሴና፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ አማሬ፡ ክንፉም፡ የተማሩ፡ ሰዎች፡ ነበሩና፡ አባታችነን፡ አካል፡ ያለ፡ ባሕርይ፡ ባሕርይም፡ ያለ፡ አካል፡ አይገኝምና፡ በየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሁለት፡ ባሕርያት፡ አሉት፡ ካሉ፡ በግድ፡ ሁለት፡ አካል፡ አሉት፡ ያሰኝብዋል፡ ብለው፡ ጠየቁ። እርስዎም፡ ትምርታችኍስ፡ እንዲህ፡ ከሆነ፡ ሥላሴን፡ ባካል፡ ሶስት፡ በባሕርይ፡ አንድ፡ ማለት፡ እንዴት፡ ይሆንላችኋል፡ ብለው፡ ጠየቁ። ከዚያ፡ ዠምሮም፡ እስኪመለሱ፡ ድረስ፡ ጠላት፡ በጉባዔ፡ ኬልቄዶን፡ ላይ፡ ሁለት፡ ሠሪ፡ በየሱስ፡ ክርስቶስ፡ | ካለ፡ አልተወሐደምም፡ ይላሉ፡ ንስጥሮሳውያን፡ ናቸው፡ ብሎ፡ የጻፈውን፡ መረመሩ። ባሰትም፡ እንደ፡ ሆነ፡ አውቀው፡ አማሬ፡ ክንፉና፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ሰባት፡ የሚሆኑ፡ ሌሎችም፡ ካቶሊክ፡ ሃይማኖትን፡ ተቀበሉ። ሊቀ፡ ካህናት፡ ሀብተ፡ ሥላሴም፡ ምንም፡ በሹመት፡ ምክንያት፡ ካቶሊክ፡ ባይሆኑ፡ እርስዋንና፡ በሮም፡ ያዩትንም፡ ያምልኮ፡ መልካምነት፡ ሁሉ፡ ይልቁንም፡ ያባታችነን፡ መንፈሳዊነትና፡ ደግነትን፡ ለጌታቸውና፡ ለካህናቱ፡ ለመኳንንቶችም፡ ሁሉ፡ ለመንገር፡ እንዳንድ፡ ሐዋርያ፡ ሆኑ፡ ስለዚህ፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ መንግሥታቸው፡ እንዳትፈርስ፡ ከመፍራት፡ በቀር፡ ውነተኛ፡ ሃይማኖት፡ እንደሆነች፡ አወቁ። ሞንሰኘር፡ ደዢቆብም፡ ከዚህ፡ በላይ፡ እንዳየነ፡ ከበፊት፡ ይልቅ፡ አከበሩ፡ ወደዱ። እርሳቸው፡ እንዳጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ያቡነ፡ ሰላማን፡ ክፉይቱን፡ ፈቃድ፡ ቢፈጽሙ፡ | የካቶሊክ፡ ሃይማኖት፡ በትግሬ፡ ልትነገር፡ የማይቻል፡ እንደነበረ፡ የታወቀ፡ ነው።።። | ደጃዝማች፡ ውቤ፡ አቡንን፡ የሚያስመጡበት፡ ገንዘብ፡ ከግዛታቸው፡ ሁሉ፡ ለማስወጣት፡ አዋጅን፡ ባስነገሩ፡ ጊዜ፡ በሁሉ፡ አገር፡ ስለ፡ ተሰማ፡ ወደ፡ የሩሳሌም፡ የሚሔዱ፡ መነኮሳት፡ ከሸዋ ና፡ ከጐዢም፡ ካማራና፡ ትግሬ፡ የሚሆኑ፡ ወደ፡ ምጽዋ፡ ደርሰው፡ ነበሩና፡ አባታችንም፡ የመርከብን፡ ዋጋ፡ ስለ፡ ሁሉ፡ ሰጥተው፡ አሻግረዋቼው፡ ነበሩና፡ እነዚያም፡ ያዩትን፡ የሰሙትን፡ ይልቁንም፡ ያባታችነን፡ በጕነትና፡ ትዕግሥትን፡ በያገራቸው፡ ለየወዳጃቼውም፡ ነገሩ። | አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ወዲያ፡ አገር፡ ሳይሻገሩ፡ ጕንድጕንዴ፡ በምትባል፡ ደብር፡ ይኖሩ፡ ነበሩ። ስለዚህ፡ ከመምር፡ ተክለ፡ ጊዮርጊስና፡ ካባቴ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ የጐልዓ፡ ከጌታዬ፡ ወልደ፡ ሥላ | ሴም፡ ከሌሎችም፡ ያጋሜ፡ ካህናት፡ የታወቁ፡ የተወደዱ፡ የከበሩም፡ ነበሩ። ከዚያም፡ ወደ፡ ጐንደር፡ ሲመለሱ፡ ኋላ፡ አባ፡ ተክለ፡ ጊዮርጊስ፡ የተባሉ፡ አሽከር፡ ከርስዎ፡ ሊማሩ፡ ባንድ፡ ሔዱ። እግዴህ፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ከዚህ፡ በፊት፡ እንዳልኍ፡ ከሮም፡ ከተመለሱ፡ በኋላ፡ አባታችንን፡ ወዳጋሜ፡ መሩ። የካቶሊክን፡ ሃይማኖትም፡ ለኒህ፡ ሁሉ፡ ስላወሩ፡ እነዚያም፡ ምክርዎን፡ ስለ፡ ሰሙ፡ ይህች፡ ሀይማኖት፡ ባጋሜ ና፡ በዳበኵነይቶ፡ ተነገረች፡ ተተከለችም። በጐልዓ፡ ፩ድ፡ በሣዕሤዕም፡ ፪ት፡ ወይም፡ ፫ት፡ ተተከለች።በዳበኵነይቶም፡ አንድ፡ አብያተ፡ ክርስቲያናት፡ ለካቶሊካውያን፡ ሆኑ። በእንክጨውም፡ ታላቅ፡ አገር፡ ብዙ፡ ካቶሊካውያን፡ ነበሩ። ምንልባት፡ ባልሳሳት፡ እንጂ፡ ፫ት፡ ዲያቆናት፡ ፲፯ ቀሳውስት፡ ፭ት፡ ሺህ፡ የሚሆኑ፡ ምእመናን፡ በነዚህ፡ አገሮች፡ ተገኙ። ባገርም፡ በሰፈርም፡ በጋዳማትም፡ | ያባታችን፡ ስም፡ በ፬ት፡ ዓመት፡ መወራት፡ እንደበዛ፡ ሰምተው፡ አቡነ፡ ሰላማ፡ በፊት፡ በጐንደር፡ ሁነው፡ ኋላም፡ ከዚያ፡ ተሰደው፡ ወደ፡ ትግሬ፡ ወዳዳቡን፡ በመጡ፡ ጊዜ፡ ከግዝትና፡ ከተንኰል፡ ከመናደድ፡ አላረፉም። ነገር፡ ግን፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ የፕሮተስታንቲ፡ ተማሪ፡ መሆናቸውን፡ ይልቁንም፡ ልንጽፈው፡ በማይገባ፡ ነውር፡ መኖራቸውን፡ ሰምተዋልና፡ ግዝታቸውን፡ ከንቱ፡ አደረጉት። ዳግመኛም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ ሀብተ፡ ሥላሴን፡ እንዴት፡ ወጠጤ፡ ጳጳስ፡ አመጣህልኝ፡ እያሉ፡ ሲገሥፁዋቸው፡ ነበሩ። ነገር፡ ግን፡ ፀሩ፡ ለሰብእ፡ ሰብአ፡ ቤቱ፡ እንዳለ፡ ካቶሊክ፡ ነኝ፡ በሚሉ፡ ከኤውሮፓ፡ በመጡ፡ ጨዋ፡ ሰው፡ ምክንያት፡ በካቶሊካውያን፡ ላይ፡ ብዙ፡ መከራና፡ ስደት፡ ሆነ። ፬ት፡ ዓመት፡ ያህል፡ በላይ፡ እንዳልኍ፡ ባጋሜ፡ የነፍስ፡ ብርሃን፡ መገለጥ፡ ዠምራ፡ ሳለች፡ ጨለማ፡ ጋረደቻት፡ በዚያ፡ ዘመን፡ አንድ፡ የፍራንሲያ፡ ሰው፡ አቡነ፡ ያዕቆብንና፡ | አቡነ፡ ማሳያን፡ ወዳጅ፡ መስሎ፡ ሊገናኝ፡ ወደ፡ ጐልዓ፡ መጣ። ወደ፡ ጋላ፡ አገር፡ የሚያልፉቱም፡ ሞንሰኘር፡ ማሳያ፡ በዚያ፡ ዘመን፡ ራስ፡ ዓሊ ና፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ ሁለቱ፡ ገዦች፡ ተጣልተው፡ ያማራ፡ አገር፡ መንገድ፡ ተዘግቶብዎ፡ እንዳንድ፡ ቄስ፡ መስለው፡ በጐልዓ፡ አንድ፡ ዓመት፡ ያህል፡ ተቀምጠው፡ ነበረ። መዓርገ፡ ክህነትም፡ በስውር፡ ሰጥተው፡ ነበሩ፡ ያ፡ የመጣው፡ እንግዳው፡ ሰው፡ በሁለቱ፡ ዘንድ፡ የከበረ፡ ነበርና፡ ምሥጢሩን፡ ሁሉ፡ ገለጡለት። በዚያም፡ ዘመን፡ አቡነ፡ ሰላማ፡ ባዳቡን፡ ነበሩ። ይህ፡ ታላቅ፡ ሰው፡ ወደርሳቸው፡ ሒዶ፡ ባጋሜ፡ ጳጳስ፡ እንዳለ፡ እንዳቀሰሰና፡ እንዳዛቈነ፡ ሌላውንም፡ ሁሉ፡ ነገራቸው። ይህም፡ ብቻ፡ አይዶለም፡ ታናሽ፡ ከይወንድሙ፡ ካገራቸው፡ ያመጣትን፡ የሞንሰኘር፡ ማሳያ፡ መልእክትንም፡ ላቡነ፡ ሰላማ፡ አሳልፎ፡ ሰጣቸው። እርሳቸውም፡ የተጻፈችበትን፡ ቈንቋ፡ የማያውቁ፡ ስለ፡ ሆኑ፡ እርሱ፡ ተረጐመላቸው። ስለዚህ፡ አቡን፡ | ከበፊት፡ ይልቅ፡ የባሱ፡ ሆኑ። አባ፡ ዮሴፍ፡ የሚባልን፡ መልእክቲቱን፡ ሊያሳይ፡ ቶሎ፡ ወደ፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ ሰደዱ። እርሳቸውም፡ በዚያ፡ ጊዜ፡ በማይጣህሎ፡ ነበሩ። ሙሴ፡ ሞንቶሪ፡ እርሳቸው፡ አባ፡ ፍሬምናጦስ፡ ጐንደር፡ መጥተው፡ ባድዋ፡ ነበሩ። የሸዋ፡ ንጉሥ፡ ሣህለ፡ ሥላሴ ና፡ ራስ፡ ዓሊ፡ እርሳቸውን፡ በስውር፡ ጳጳስን፡ ሊያመጡ፡ ልከዋቸው፡ ነበሩ። ይህነን፡ ግን፡ ሰምተው፡ ያቡን፡ ሰዎች፡ ተከትለው፡ ወደ፡ ማይጣህሎ፡ ደረሱ። ሌባ፡ ነውና፡ ይህችን፡ ያቡነ፡ ማሳያን፡ መልእክት፡ የሰጠውን፡ እንዲጥድልኝ፡ ተማጥኘዋለኍ፡ አሉ። ይህነንም፡ ብለው፡ ዝም፡ እንዳይሉ፡ በላይ፡ የተናገርኋቸው፡ ሁለቱ፡ ገዦች፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ እንዳይሰሙት፡ ያሉዋቸውን፡ ጳጳስ፡ ላመጣ፡ ነኝና፡ እርስዎሳ፡ ይወዳሉን፡ ብለው፡ ጠየቁዋቸው። ይህም፡ ቅለት፡ ወረቀቱ፡ ከሰጠው፡የከፋ፡ ሆነ። ስለዚህ፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ ባቡነ፡ ሰላማ፡ ፈንታ፡ ሊሆኑ፡ የመጡ፡ መስልዋቸው፡ እኔ፡ ሳልሰማ፡ | እንዴት፡ ይህ፡ ነገር፡ ተደረገ፡ ብለው፡ ተቈጡ። ያ፡ ጳጳስ፡ በመጣበት፡ መንገድ፡ ይመለስ፡ አሉ። ያቡን፡ ሰዎች፡ ቃላጤን፡ ተቀብለው፡ በታላቅ፡ ደስታ፡ ተመልሰው፡ ሞንሰኘር፡ ማሳያን፡ ሊያባርሩ፡ ወደ፡ ጐልዓ፡ መጡ። ነገር፡ ግን፡ ያ፡ መልእክታቸውን፡ አሳልፎ፡ የሰጠው፡ ሰው፡ ወረቀትም፡ ባቡን፡ እጅ፡ ገባች፡ እርሳቸውም፡ በርስዎ፡ ላይ፡ እጅግ፡ ተናደዋል፡ ብሎ፡ ጽፎለዎ፡ ነበርና፡ ፈጥነውም፡ ከጐልዓ፡ ወደ፡ ምጽዋ፡ ወርደው፡ ነበሩና፡ ያቡን፡ ሰዎች፡ ቃላጤውን፡ ይዘው፡ በመጡ፡ ጊዜ፡ አላገኙዋቸውም። ነገር፡ ግን፡ በዚህ፡ ምክንያት፡ የተዠመረ፡ ነገር፡ ከዚህ፡ እንዳልኍ፡ በካቶሊካውያን፡ ላይ፡ ታላቅ፡ መከራንና፡ ስደትን፡ አስመጣ። እንግዴህ፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ የሔዱባትን፡ ምክንያትና፡ እርስዋም፡ ያበቀለቻትን፡ መልካም፡ ፍሬን፡ ሳያውቁ፡ ሙሴ፡ ደዢቆብ፡ ነገሩን፡ በመሳሳት፡ ዠመረ፡ ማለታቸው፡ እርሳቸው፡ ይልቅ፡፡ ተሣሥተዋል። ከዚያ፡ ዠምሮ፡ እስካሁ | ን፡ ፵ ዓመት፡ ድረስ፡ መከራን፡ የምትቀበል፡ ባጋሜ ና፡ በዳበኵነይቶ፡ ባከለጕዛይ፡ ያለች፡ ካቶሊካዊት፡ ቤተ፡ ክርስቲያንም፡ ከዚህ፡ በላይ፡ እንዳየነ፡ ከመልእክተኞች፡ ጋራ፡ ወደ፡ ሮም፡ በመመለስዎ፡ ምክንያት፡ የተሠራች፡ እንደሆነች፡ የተገለጠ፡ ነውና፡ እንዴት፡ አያውቁ፡ ብንልም፡ እንግዲያስ፡ መንቀፋቸው፡ የልባቸው፡ ጥመት፡ ነው።
chapter ()
Alignment Start a translation alignment with Alpheios Alignment. You can also add morphological annotations there. See instructions in GitHub.
Versions See parallel versions if any is available
Quotations Check for marked up quotations of a passage in this section
back to top
| ፬ኛ፡ ክፍል። | ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ፲፭ት፡ ዓመት፡ ያህል፡ በትግሬ፡ ከኖሩ፡ በኋላ፡ በኛ፡ ቍጥር፡ ባ፲፰፻፵፮ ዓመት፡ሐላይ፡ ወደ፡ ጐንደር፡ ለመሔድ፡ ተነሡ። ደጃዝማች፡ ውቤንም፡ ለመሰናበት፡ መንገድዎን፡ በእንደርታ ና፡ በሰለዋ፡ አድርገው፡ ወደ፡ በለሳም፡ ተሻግረው፡ በየካቲት፡ ወደ፡ ጐንደር፡ ገቡ። አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልና፡ በዚያም፡ የነበሩ፡ ካቶሊካውያን፡ በመገናኘታቸው፡ ደስ፡ አላቸው። ያን፡ ጊዜም፡ ከትግሬ፡ ወደዚያ፡ የመ | ጡበት፡ ፩ ምክንያት፡ ባንድ፡ ላይ፡ የክህነትን፡ መዓርግ፡ ለመፈጸም፡ ነው። ፪ኛም፡ ምነው፡ ወደ፡ ሸዋ፡ አትሔዱ፡ የምትል፡ ትእዛዝ፡ ብዙ፡ ጊዜ፡ ተከርዲናል፡ ባርናቦ፡ መጥታብዎ፡ ነበርና፡ ወደዚያ፡ ለማለፍ፡ ነው። በ፪ኛው፡ ዓመት፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ የተባሉ፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ ራስ፡ ዓሊን፡ ድል፡ አድርገው፡ በዚያ፡ ጊዜ፡ በጐዣም፡ ነበሩ። ነገር፡ ግን፡ በበጌምድር፡ ሁሉ፡ የርሳቸው፡ ሹማምቶች፡ ነበሩና፡ እንግዳ፡ ነጭ፡ ሰው፡ ያለ፡ ገዢው፡ ፈቃድ፡ ማለፍ፡ የማይቻል፡ ነበረ። ስለዚህ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ገዡ፡ እሺ፡ ቢሉ፡ በዚያ፡ ለመኖር፡ አይሆንም፡ ግን፡ ቢሉ፡ ለማለፍ፡ ፈቃድን፡ ለመለን፡ አባ፡ ተክለ፡ ሃይማኖትን፡ ከመልእክትዎ፡ ጋራ፡ ወደ፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ እስከ፡ ጎዢም፡ ላኩ። ገዡም፡ በገዙት፡ ቤት፡ በጐንደር፡ ሳያስተምሩ፡ እንደ፡ ሁሉ፡ ሰው፡ ቢቀመጡ፡ ግድ፡ የለኝም፡ ብለው፡ መለሱ። ከዚህ፡ በኋላ፡ አቡነ፡ ሰላማ፡ ትግሬ፡ ተነሥተው፡ በዚኸው፡ ዓመት፡ በግንቦት፡ | ፲፪ኛ፡ ቀን፡ ወደ፡ ጐንደር፡ ገቡ። ባማርኛ፡ ቋንቋ፡ ተጽፎ፡ እንዳለ፡ አቡን፡ በርስዎና፡ በካቶሊካውያን፡ ላይ፡ ያደረጉት፡ መከራና፡ ግፍ፡ ብዙ፡ ነውና፡ በዚህ፡ መጻፍ፡ አይቻለኝም። | ሙሴ፡ ሌዢአን፡ ፩ በዚያ፡ ዘመን፡ ሁለግዜ፡ በገዛው፡ በውቤ፡ ላይ፡ ለማስፈራት፡ ባቡን፡ እጅ፡ የዘበበለች፡ ሚዛን፡ ነበረች፡ በዚህችም፡ ምክንያት፡ የሙሴ፡ ደዢቆብ፡ ወደ፡ ጐንደር፡ መድረስ፡ እጅግ፡ አሳዘኝ፡ የሆነች፡ በሥራትም፡ ያልሆነች፡ መድረሱ፡ በምክንያት፡ ካቡን፡ ጋራ፡ መጣላቱ፡ ባምልኮ፡ ነገሮች፡ ያወታደሮችን፡ የመግዛት፡ ጥበብ፡ ብልሃት፡ በሁለት፡ መኸል፡ ለማስገባት፡ ወደ፡ ጐንደር፡ መድረሱ፡ ያልታረመ፡ ነገር፡ ነበረ፡ ይላሉ። ምላሽ። ወኃሠሡ፡ ሊቃነ፡ ካህናት፡ ወጸሐፍት፡ ይትመየጥዎ፡ ወየአኃዝዎ። ወይቤሉ፡ አኮ፡ በበዓል፡ ከመ፡ ኢይትሀወኩ፡ ሕዝብ፡ ማርቆስ፡ ፲፬ ፩ ይላል። ምስጋና፡ ይግ | ባውና፡ ሰላምን፡ ያመጣ፡ ያለም፡ ሁሉ፡ መድኃኒት፡ ጌታችን፡ የሱስ፡ ክርስቶስ፡ ግን፡ በዚያ፡ ቀን፡ ለበዓል፡ ለሚሰበሰቡ፡ ለእሥራኤል፡ ወገኖች፡ ሁሉ፡ መድኃኒታቸው፡ እርሱ፡ እንደሆነ፡ ለመግለጥ፡ የሕማማቱንም፡ ወሬ፡ በያገራቸው፡ ሲመለሱ፡ እንዲያወሩ፡ የሊቃነ፡ ካህናትን፡ አሳብ፡ ለማፍረስ፡ በፋሲካቸቅ፡ በዓል፡ ሊሞት፡ ወደ፡ የሩሳሌም፡ መጥተዋልና፡ ሙሴ፡ ሌዢአን፡ ጌታችነንም፡ ነቅፈው፡ ይሆናል። ዳግመኛም፡ ከመዝ፡ የዓሥርዎ፡ አይሁድ፡ የሩሳሌም፡ ወያገብእዎ፡ ለአሕዛብ። ወዘንተ፡ ሰሚዓነ፡ አስተብቋዕናሁ፡ ለጳውሎስ፡ ከመ፡ ኢይዕርግ፡ የሩሳሌም፡ አንሰኬ፡ አኮ፡ ባሕቲቶ፡ ማሕመሜ፡ ወመዋቅሕተ፡ ዘእሴፎ፡ ዓዲ፡ ለመቂትኒ፡ ጥቡዕ፡ አነ፡ በየሩሳሌም፡ በመውጣቱ፡ እርሱንም፡ ለመግደል፡ አይሁድ፡ ስለ፡ ተነሡ፡ የሩሳሌም፡ ሁ | ሉዋ፡ ታውካለችና፡ ቅዱስ፡ ጳውሎስንም፡ ሊሰድቡ፡ ይደፍሩ፡ ይመስለኛል። ፩ ግብረ፡ ሐዋ፤ ፳፩ ፲፩ ፲፬። ዳግመኛም፡ ባምልኮ፡ ምክንያት፡ የጦርን፡ መግዛት፡ በማኸል፡ እንዲያስገባ፡ ነው፡ አሉ። ከዚህ፡ በፊት፡ እንዳልኍ፡ የሞንሰኘር፡ ማሳያ፡ ወረቀት፡ ክፉ፡ ሰው፡ ላቡን፡ ከሰጠ፡ ዠምሮ፡ በትግሬ፡ ያሉ፡ ካቶሊካውያን፡ ከመከራና፡ ከዕሥራት፡ አላረፉም፡ ነበሩ። ባይበዛም፡ ከዚያ፡ ዠምሮ፡ ወደ፡ ጐንደር፡ እስኪሔዱ፡ ድረስ፡ ዓሥር፡ ዓመት፡ ይሆናል። እንኪያው፡ ምነው፡ ጦር፡ ያልመጣ። ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ በብዙ፡ ገንዘብ፡ ቦታን፡ በጐልዓ፡ ገዝተው፡ የጸሎትን፡ ቤትና፡ የተማሪ፡ ቤት፡ ሌላንም፡ ታላላቅ፡ ቤት፡ ሠርተው፡ ዓራት፡ ዓመት፡ ያህል፡ በዚያ፡ ከተቀመጡ፡ በኋላ፡ ወደ፡ ምንኵሉ፡ እንደተሰደዱ፡ ዳግመኛም፡ በዚያ፡ የሠሩትን፡ ቤት፡ ሰምሐርን፡ ሊዘርፍ፡ የወረደ፡ የደጃዝማች፡ ውቤ፡ ጦር፡ እንደ፡ ተኰሰው፡ የፈረንሳዊ፡ ኮ | ንሱል፡ ደጉቴን፡ ቤቱንም፡ እንደ፡ በዘበዘው፡ ሁሉ፡ የሚያውቀው፡ ታሪክ፡ ነው። ደጃዝማች፡ ውቤም፡ በዚህ፡ ምክንያት፡ ሠግተው፡ ከሙሴ፡ ደጉቴን፡ በኋላ፡ ወዲያው፡ በምጽዋ፡ ኮንሱልነትን፡ ወደ፡ ተሾሙ፡ ሙሴ፡ ሮላንድ፡ የፍቅር፡ መልእክትን፡ በዚያ፡ ዘመን፡ እንደ፡ ጻፉ፡ በሙሴ፡ ሌዢአን፡ መጻፍ፡ መልእክታቸው፡ ተጽፉለች። ገጽ፡ ፪፻፶፬ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ከጐልዓ፡ በተሰደዱ፡ ዓመቱ፡ ሙሴ፡ ሮላንድ፡ ምጽዋ፡ እስከ፡ ሐውዜን፡ ወጥተው፡ ከደጃዝማች፡ ውቤ፡ ተገናኙ። ስለ፡ ሚስዮን፡ ስንኳንስ፡ አንዲት፡ መልካም፡ ነገር፡ ሊናገሩ፡ የሩቦ፡ ሰዓት፡ መንገድ፡ የምትሆን፡ ሳሉ፡ ከሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ስንኳ፡ አልተገናኙም። ካቶሊካውያን፡ ከሚያሰደዱ፡ ካቡነ፡ ሰላማ፡ መናፍቅ፡ ጳጳስ፡ ግን፡ ሊገናኙ፡ ከሐውዜን፡ እስካዳቡን፡ የሁለት፡ ቀን፡ መንገድ፡ የሚሆን፡ ሒደው፡ በፍቅር፡ ተገናኙ። ዳግመኛም፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ከፈረንሳዊ፡ ከምጽዋ፡ ኮን | ሱል፡ ደሌይ፡ ከዚህ፡ የባሰ፡ ግፍ፡ አግኝተዋል። ከዚህ፡ በላይ፡ እንዳልኍ፡ አቡነ፡ ሰላማ፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ ባምባጫራ፡ በተገናኙ፡ ጊዜ፡ አባ፡ ያዕቆብን፡ አባርልኝ፡ ሰዎቹን፡ ግን፡ ዓሥረህ፡ ስጠኝ፡ አሉዋቸው። እርሳቸውም፡ ይህነን፡ ነገር፡ በሐምሌ፡ ፱ኛ፡ ቀን፡ ከሥጋዌም፡ በኋላ፡ ባ፲፰፻፵፮ት፡ ፈጸሙላቸው። አባታችነን፡ አብራሂም፡ ወደ፡ ሚባል፡ የመተማ፡ ገጅ፡ በብዙ፡ ጥንቃቄ፡ ጥበቃ፡ ሰደዱ። ነገር፡ ግን፡ ብፁዓን፡ ሐዋርያት፡ የጴጥሮስና፡ የጳውሎስ፡ አምላክ፡ መልአኩን፡ ሰዶ፡ ባርያውን፡ ያዕቆብ፡ ከጠላቶች፡ ስላወጣ፡ ስለ፡ ጠበቀም፡ ከመተማ፡ ወዳዳርድኃ፡ እርስዋም፡ በጐንደር፡ አጠገብ፡ ያለች፡ አገር። ከርስዋም፡ ወደ፡ ሐላይ፡ ተመለሱ። ይህም፡ ከዚያ፡ ከወጡ፡ በኋላ፡ ባንድ፡ ዓመት፡ ሆነ። በዚህ፡ ጊዜ፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ ደጃዝማች፡ ውቤን፡ ሽረው፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ተባሉ። ሙሴ፡ ሌዢአን፡ አቡነ፡ ሰላማን፡ ያሾመ፡ በምስር፡ የነበረ፡ የእንግሊዝ፡ ኮንሱ | ል፡ ነው፡ የፕሮተስታንቲም፡ የሊኤደር፡ ተማሪ፡ ነበረ፡ ገጽ፡ ፵፫ እንዳለ፡ አቡነ፡ ሰላማ፡ ስለ፡ እንግሊዞች፡ አምልኮና፡ የመንግሥት፡ ሥራት፡ ዓይነተኛ፡ ሥራተኛ፡ ነበሩ። ሙሴ፡ ፕሎውደን፡ የእንግሊዝ፡ ኮንሱልም፡ ከሮም፡ የተላኩ፡ ካህናት፡ በኢትዮጵያ፡ ካሉ፡ ጕዳያችን፡ አይቀናም፡ ብለው፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ እንዲያስለቅቁላቸው፡ አቡነ፡ ሰላማን፡ ሲጐተጕቱ፡ ነበሩ። ይህነንም፡ እንዲያደርጉ፡ በምጽዋ፡ የነበሩ፡ ምስለኔያቸው፡ ሙሴ፡ ባሮኒ፡ ሙሴ፡ ደልሞንቴ፡ እንዳሉም፡ በያመቱ፡ ከእንግሊዝ፡ መንግሥት፡ ላቡነ፡ ሰላማ፡ ስምንት፡ መቶ፡ ብር፡ በኔ፡ እጅ፡ አለፈ፡ አሉ። ኋላ፡ ሊቀ፡ መኳስ፡ የተባሉ፡ ቤል፡ ዮሐንስም፡ የእንግሊዝ፡ ወገን፡ ነበሩና፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ ጐንደር፡ ወደ፡ መተማ፡ ለማባረር፡ ከገዢው፡ መልእክተኞች፡ ጋራ፡ እንደ፡ መጡ፡ ባባታችን፡ ገድል፡ ባማርኛ፡ ተጽፎዋል። ነገር፡ ግን፡ እኒህ፡ የሌላ፡ ወገን፡ ሰዎች፡ ናቸውና፡ በካቶሊካውያን፡ ላይ፡ ቢ | ነሡ፡ አያስደንቅም። ይልቁንስ፡ የሚያሳዝን፡ ካቶሊካውያን፡ ከሚባሉቱ፡ ከፈረንሳውያን፡ ወገኖች፡ የሚሲዮን፡ ጠላቶች፡ በመሆናቸው፡ ነው። እነሆ፡ ከዚህ፡ በፊት፡ እንዳልኍ፡ አንዱ፡ የሞንሰኘር፡ ማሳያን፡ መልእክት፡ ላቡነ፡ ሰላማ፡ አሳልፎ፡ ሰጠ። ባገራችን፡ ቴዎፍሎስ፡ ሲባሉ፡ የነበሩቱ፡ ሙሴ፡ ለፌብርም፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ ከጐልዓ፡ ለማስለቀቅ፡ ከደጃዝማች፡ ውቤ፡ ከተላኩቱ፡ ጋራ፡ ሊመጡ፡ አላፈሩም። በላይ፡ የጠራኍ፡ ሙሴ፡ ደሌይም፡ ሙሴ፡ ፕሎውዶንን፡ ደስ፡ ለማሰኘት፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ መተማ፡ ወደ፡ ሐላይ፡ በተመለሱ፡ ጊዜ፡ ባለሰበካው፡ ለምን፡ በዚየ፡ ይቀመጣሉ፡ ይልቀቁላቸው፡ ብለው፡ መልእክትን፡ ጻፉለዎ። የኢትዮጵያ፡ ሰዎች፡ ወደ፡ እውነተኛይቱ፡ እናታቸው፡ ቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ እንዲመለሱ፡ ሊመጥሩ፡ ለወንጌል፡ መልእክተኞች፡ በመልካም፡ ልብ፡ የሚረዱ፡ በፍራንሲያ፡ ብዙ፡ ምእመናን፡ እንዳ | ሉ፡ ሰማኍ። ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ግን፡ እነዚያን፡ ለማሳዘን፡ ሙሴ፡ ደዢቆብ፡ በዚያ፡ ጊዜ፡ ካቡን፡ ጋራ፡ ለመጣላት፡ ባመልኮም፡ ምክንያት፡ ጦርን፡ ለማስነሣት፡ ብለው፡ መጻፋቸው፡ ግን፡ ከሌሎቹ፡ ነገር፡ ትከፋለች። | ነገር፡ ግን፡ በዚያ፡ ዘመን፡ የሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ወደ፡ ጐንደር፡ ደርሰው፡ ከልጆችዎ፡ ጋራ፡ መከራን፡ መቀበል፡ ከበፊት፡ ይልቅ፡ የካቶሊካዊት፡ ሃይማኖት፡ ክብርን፡ እንዳበለጠ፡ በማስከትልልህ፡ ነገር፡ ይገልጥልሃል። እንዲህ፡ ሆነ፡ አቡን፡ ወደ፡ ጐንደር፡ ከገቡ፡ በኋላ፡ ደጃዝማች፡ ካሳም፡ ጐሹ፡ ብሩን፡ ዓሥረው፡ በሰኔ፡ ወዳምባጫራ፡ መጡ፡ ሁለቱም፡ ከተማከሩ፡ በኋላ፡ ያዲስ፡ ሃይማኖት፡ አዋጅ፡ በፊት፡ ባምባጫራ፡ ኋላም፡ በጐንደር ና፡ ታላቅ፡ ገቢያ፡ ባለበት፡ ሁሉ፡ ተነገረ። እስከ፡ ሁለት፡ ሳምንት፡ ባባቴ፡ ባቡነ፡ ሰላማ፡ ሃይማኖት፡ ያልገባ፡ ከፍ፡ ብዬ፡ አንገቱን፡ ዝቅ፡ ብዬ፡ ባቱን፡ አቍርጠዋለኍ፡ የሚል፡ ነው። ያገራችን፡ ሰዎች፡ ግን፡ አ | ንዱ፡ ወገን፡ ቅባት፡ ፪ኛውም፡ የጸጋ፡ ልጅ፡ ፫ኛውም፡ ወልድ፡ ቅብ፡ የሚሉ፡ በሶስት፡ ወገን፡ የተከፈሉ፡ ነበሩ። የዚያን፡ ጊዜ፡ ያዋጁ፡ ሃይማኖት፡ | ግን፡ ክርስቶስ፡ በሰውነቱ፡ አምላክ፡ በሰውነቱም፡ እንደ፡ አብና፡ እንደ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ ያውቃል፡ ማለት፡ ሆነ። ሶስቱም፡ ወገን፡ ሁሉ፡ በመፍራት፡ እየሃይማኖታቸውን፡ ካዱ። | ከዚህ፡ በላይ፡ እንዳየነ፡ የደጃዝማች፡ ውቤ፡ መልእክተኞች፡ ሮምን፡ አይተው፡ ስለ፡ ተመለሱ፡ የካቶሊክ፡ ሃይማኖትና፡ የሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ መልካም፡ ስም፡ ባገር፡ ሁሉ፡ ተዘርግታ፡ ነበረች። ነገር፡ ግን፡ ሁሉ፡ እየሃይማኖታቸውን፡ ሲክዱ፡ በእግዝእትነ፡ ማርያም፡ አመላጅነት፡ በጌታችን፡ በየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ኃይል፡ ጸንተው፡ ሃይማኖታቸውን፡ ገልጠዋልና፡ ወኢይኄይልዋል፡ አናቅጸ፡ ሲኦል፡ የተባለ፡ ቃል፡ በዚያ፡ ጊዜ፡ ሲሆን፡ አይተው፡ ሁሉ፡ እዳ | ለያንዳንዱ፡ ሁለት፡ ክንድ፡ ተሰንዝር፡ ይሆናል። ማኸሉን፡ ነድለው፡ ሁለቱን፡ እግር፡ አስተብተው፡ እግሩን፡ እንዳያወጣ፡ በሁለት፡ ማኸል፡ ማዝን፡ ያለበትን፡ የእንጨት፡ ችንካር፡ ቸነከሩበት። ተንጋሎ፡ ከመተኛት፡ በቀር፡ ወደ፡ ቀኝ፡ ወይም፡ ወደ፡ ግራ፡ መንቀሳቅስ፡ የለም። እንደ፡ ሰው፡ ባሕርይ፡ በግድ፡ የሚሆነውም፡ ነገር፡ በዚያው፡ በተኙበት፡ ነበረ። ሃይማኖታቸውን፡ ሳይክዱ፡ በንደዚህ፡ ያለ፡ ሥቃይ፡ መኖራቸው፡ ለሁሉ፡ እጅግ፡ አስደነቀ። አቡንንም፡ አስነቀፈ። እርሳቸውም፡ እጅግ፡ ተናደው፡ ወደ፡ ንጉሥ፡ ላኩ። እኒያ፡ ያባ፡ ያዕቆብ፡ ሰዎች፡ በክፋታቸው፡ ጸንተዋልና፡ ቅጣልኝ፡ ብለው፡ አሳላፊ፡ ወልደ፡ ዮሐንስ፡ የሚባል፡ ሎሌያቸውን፡ ላኩ። ዓሥረህ፡ ስጠኝ፡ ብለውኝ፡ ሰጥቸዎ፡ አሉኍና፡ ቅጣት፡ የሚገባቼው፡ እንደሆን፡ ፍትሐ፡ ነገሥት፡ አሳይተው፡ ይቅጡዋቸው፡ የማይገባ፡ ግን፡ እንደሆን፡ ይተውዋቼው፡ ብለ | ው፡ መለሱ። ስለዚህ፡ አቡን፡ ዕሥሮችን፡ እንግዴህ፡ ካሳ፡ ቅጣቸው፡ ብሎኛል፡ ባትመለሱ፡ ሞታችኍቅርብ፡ ናት። ስንኳን፡ እናተን፡ የማይገባትን፡ ሴቲቱን፡ ስንኳ፡ ገረፍኋት፡ አሉ። የኒህ፡ ሴትም፡ ነገር፡ በኋላ፡ እናገራለኍ። ዕሥሮች፡ ግን፡ በብርቱ፡ ስለ፡ ሃይማኖታቸው፡ ሞትን፡ እጅግ፡ ይመኑ፡ ነበሩና፡ ከሥጋችን፡ በቀር፡ ነፍሳችነን፡ ምንምን፡ አንሰጥዎም፡ ብለው፡ ቢመልሱላቸው፡ እጅግ፡ ተናደዱ። በታኅሣሥ፡ ፳፯ኛ፡ ቀን፡ አሙስ፡ ወደ፡ እኩል፡ ቀን፡ በሚሆን፡ ባ፲፰፻፵፯ ዓመተ፡ ሥጋዌ፡ ባደባባይ፡ ላይ፡ ተቀምጠው፡ በያንዳንዱ፡ እያስመጡ፡ ገረፉዋቸው። ይህነንም፡ አድርገው፡ የማይክዱላቼው፡ ስለ፡ ሆኑ፡ ተቈጥተው፡ ወዲያው፡ ወደ፡ ነበሩበት፡ ግንድ፡ እንዲያስገቡዋቸው፡ አዘዙ። ከዚህ፡ በኋላ፡ አቡንና፡ ንጉሥ፡ በዚያው፡ ዓመት፡ ወደ፡ ሸዋ፡ በዘመቱ፡ ጊዜ፡ ወይእዜኒ፡ ምንት፡ ብኪ፡ በፍኖተ፡ ግብጽ፡ ከመ፡ ትስተዪ፡ ማየ፡ ሕሙገ፡ ኤርም | ያስ። ፪ ያለውን፡ ያውቃሉና፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ በጉባዔ፡ ኬልቄዶን፡ ከረገማት፡ ከደፋት፡ ከደፈረሰችም፡ ኑፋቄ፡ ዉሀን፡ ሳይቀምሱ፡ በእመቤታችን፡ አመላጅነት፡ በእግዜር፡ ቸርነት፡ በተያዙ፡ በ፲፪ኛው፡ ወር፡ በሰኔ፡ ፮ኛ፡ ቀን፡ ከፈርዖን፡ ባርነት፡ ወጡ። | እንኳንስ፡ እናንተ፡ ሴቲቱን፡ እንኳ፡ ገርፌ፡ አለኍ፡ ያሉዋቼው፡ ሴት፡ ሐብቱ፡ ለምለም፡ የሚባሉ፡ የደብተራ፡ ኃይሉ፡ ምሽት፡ ናቼው። እኒህም፡ ከመልእክተኞች፡ ጋራ፡ ወደ፡ ሮም፡ የደረሱ፡ ናቸው። ሞንሰኘር፡ ደዢቆብና፡ ወንድሞቻቸው፡ መነኮሳት፡ ሲያዙ፡ ባንድ፡ ነበሩ፡ እግዜር፡ አወጣቸው። ምሽታቸው፡ ግን፡ በሚታቸው፡ ቤት፡ በበአታ፡ ተያዙ። የናታቸውና፡ የሚታቸውም፡ ብዙ፡ ገንዘብ፡ ነበረ። ሁሉም፡ ተቈጠረ፡ የንጉሥና፡ ያቡን፡ ወታደሮች፡ እንደ፡ ሻቸው፡ በዚያ፡ ሲመገቡ፡ ሲያስጨንቁ፡ ከሰነበቱ፡ በኋላ፡ ሴቲቱን፡ ወዳቡን፡ አመጡ። ባልሽ፡ ካ | ለበት፡ አስፈልገሽ፡ እንድታመጪ፡ ባንድነትም፡ ሃይማኖትን፡ ልትገቡ፡ አውሽ፡ አሉዋቼው። እስከ፡ ሁለት፡ ወር፡ አውሰው፡ ተለቀቁ። ከዚህ፡ በኋላ፡ ባ፬ኛ፡ ወር፡ በጥቅምት፡ አቡን፡ ሴቲቱን፡ አስመጥተው፡ ባልሽ፡ ከጠፋ፡ እንግዴህ፡ አንቺ፡ ወደ፡ ሃይማኖቴ፡ ግቢ፡ አሉዋቼው። ሁሉን፡ የሚችል፡ አምላክ፡ ግን፡ በደካሞች፡ ልብ፡ አድኖ፡ ትዕቢተኞችን፡ ማዋረድ፡ ልማዱ፡ ነውና፡ ዳግመኛም፡ ያገራችን፡ ሰዎች፡ እውነተኛይቱን፡ ሃይማኖት፡ አላወቅነም፡ እንዳይሉ፡ ምክንያት፡ እንዲያሳጣቸው፡ በሴቲቱ፡ ልብ፡ ጸጋውን፡ አሳደረ። ነገር፡ ግን፡ አቡን፡ ለርሳቸው፡ የተናገሩትን፡ እርሳቸውም፡ የመለሱትን፡ የተቀበሉትንም፡ ሥቃይ፡ የካቶሊካውያን፡ ታሪክ፡ በተጻፈበት፡ በግዕዝ፡ ተጽፎዋል። በዚህስ፡ የተዠመረን፡ ለማያያዝ፡ ብቻ፡ ጥቂት፡ እናገራለሁ። ሴቲቱ፡ ባቡንና፡ በጉባዔው፡ ፊት፡ ቁመው፡ ሳይፈሩ፡ | እኔ፡ ሴት፡ ነኝ፡ ትምርት፡ አልተማርሁም፡ ነገር፡ ግን፡ ሮማውያን፡ አባቶቼ፡ ያስተማሩኝ፡ ሃይማኖት፡ እውንተኛ፡ እንደ፡ ሆነች፡ በምግባራቸው፡ አውቄ፡ አምኜ፡ አለሁ። ባሌንም፡ እስከ፡ ሞት፡ ድረስ፡ እንዳልከዳ፡ ምያለኍ። እነዚያ፡ የግቢ፡ ቃል፡ ኪዳን፡ ከቶ፡ አለሞት፡ በቀር፡ አይፈርሰም፡ ይላሉ። እርስዎ፡ ግን፡ ለሌላ፡ አጋባሻለኊ፡ አሉ፡ እነሆ፡ በዚህ፡ አውቃለኍ፡ አሉ። አቡን፡ ይህነን፡ ሰምተው፡ ተቈጡ። ሴቲቱ፡ በእግር፡ ብረት፡ ታሠሩ። ከዚህ፡ በኋላ፡ በ፫ኛ፡ ቀን፡ ይመስለኛል። አቡን፡ ሁለተኛ፡ ጠይቀው፡ አባብለውም፡ ከሴቲቱ፡ ተስፋን፡ ስላጡ፡ በፊት፡ ባለንጋ፡ ኋላም፡ በጅራፍ፡ ገረፉዋቼው። ሲገረፉም፡ ከተወለደ፡ ፬ት፡ ወር፡ የሚሆነው፡ ጨቅላ፡ በጫንቃቸው፡ አዝለው፡ ነበረ። ሁለት፡ ወይ፡ ፫ት፡ ግርፋት፡ ከወደቀበት፡ በኋላም፡ አቡን፡ አውርደው፡ ጣሉት። ጊዜው፡ ጨለማ፡ ነበረና፡ ልጅ፡ የሌላት፡ አንዲት፡ ሴት፡ | ወስዳ፡ ሸሽችው። ስለዚህ፡ ለሴቲቱ፡ ከሰንሰለቱና፡ ከግርፋቱ፡ ይልቅ፡ እርሱን፡ እስኪያመጡላቸው፡ ድረስ፡ የባሰ፡ መከራ፡ ሆነባቸው። ከዚህ፡ በኋላ፡ በነገታው፡ የሴቲቱ፡ ቤተ፡ ዘመድ፡ ተሰብስቦ፡ መጥቶ፡ ከጥዋት፡ ዠምሮ፡ እስከ፡ ማታ፡ እንዲክዱ፡ ለመኑዋቸው። አንዳንዱ፡ ሁለቱን፡ ሕፃናት፡ ልጆቻቸውን፡ ሌሎቹም፡ ደንጊያ፡ ተሸክመው፡ በልመና፡ አስጨነቁዋቼው። እርሳቸው፡ ግን፡ እንዳያዩና፡ እንዳይሰሙ፡ በልብሳቸው፡ ተሸፈኑ። ከዚህ፡ በኋላ፡ አቡን፡ ወደርሳቸው፡ አስመጥተው፡ በፊት፡ አባበሉ። ኋላም፡ በቍስቋም፡ ሊቈርብ፡ እነሆ፡ ካሳ፡ ሊመጣ፡ ነው። እኔ፡ እንዳባትነቴ፡ ገረፍሁሽ፡ እርሱ፡ ግን፡ ከንፈርሽን፡ ይፎን ንሻል፡ ጡትሺንም፡ ይቈርጥሻል፡ እያሉ፡ ይህነን፡ በመሰለ፡ አስፈራሩዋቸው። ሴቲቱ፡ ግን፡ በእግዜር፡ ኃይል፡ ጠኑ። ዘመዶቻቸው፡ የኔታ፡ ሆይ፡ ይህ፡ ድርቅናዋ፡ በፈቃድዋ፡ አይምሰለዎ። ባልዋ፡ ተንኰለኛ፡ ነው፡ እስከ፡ ፈረንጅ፡ አገር፡ ሒዶ፡ ነበርና፡ | መድኃኒት፡ አድርጎባት፡ ነው። ይህነን፡ መድኃኒት፡ ግን፡ ለመፍታት፡ ገድለ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ እያስደገምነ፡ እንድናስጠምቃት፡ ይስጡነ፡ ብለው፡ ለመኑ። ፳፰ት፡ ቀን፡ ያህል፡ በእግር፡ ብረት፡ ከታሠሩ፡ በኋላ፡ በዋስ፡ አስፈትተው፡ ወደ፡ ቤታቼው፡ አስመለሱዋቸው። ዳግመኛም፡ በ፪ኛው፡ ዓመት፡ አቡንን፡ ንጉሥ፡ ከሸዋ፡ ከተመለሱ፡ በኋላ፡ እኒህ፡ ሴት፡ ተይዘው፡ የተቀበሉት፡ ሥቃይ፡ ከፊተኛው፡ እጅግ፡ የበረታ፡ ነው። ርጉዝ፡ ነበሩ። በፊት፡ በጭራ፡ የፊጢኝ፡ ታሠሩ። ኋላም፡ በግድ፡ አገቡዋቸው። በሥራትም፡ ሳሉ፡ ወለዱ። የቀረው፡ ነገራቸው፡ ሁሉ፡ በፊት፡ እንዳልኍ፡ በግዕዝ፡ ተጽፎዋል። ያቡን፡ ጭከናና፡ የኒህ፡ ሴት፡ ጥናት፡ በኢትዮጵያ፡ ሁሉ፡ ተወራ። እቴጌ፡ ተዋበች፡ ያጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ምሽት፡ ይህነን፡ ሰምተው፡ በሴት፡ ላይ፡ እንደዚህ፡ ያለን፡ ሥቃይ፡ የሚያደርጉ፡ እኒህ፡ አቡን፡ ምን፡ ያሉ፡ ጨካኝ፡ ናቸው፡ እያሉ፡ እን | ደነቀፉ፡ ሰማኍ። ዳግመኛም፡ ሸዌ፡ ወልደ፡ ሥላሴ፡ አለቃም፡ የሚባሉቱ፡ ምንም፡ በሃይማኖት፡ የካቶሊካውያን፡ ጠላት፡ ቢሆኑ፡ የኒህን፡ ሴት፡ ሥቃይ፡ ሰምተው፡ ወዳቡን፡ መጡ። እርሳቸውን፡ አቡን፡ ይፈሩዋቸዋል፡ ያከብሩዋቸው፡ ማል። ይህ፡ ግን፡ ስለ፡ መማራቸው፡ ወይም፡ ስለ፡ ሌላ፡ ምክንያት፡ እንደሆነ፡ አላውቅም። ጳጳሳችን፡ ስለ፡ ሃይማኖት፡ ሴትን፡ ማሠርና፡ መግረፍ፡ በምን፡ መጻፍ፡ ባፈ፡ ወርቅን፡ ቄርሎስን፡ ከቶ፡ በማናቸው፡ መጻፍ፡ አገኙት፡ ብለው፡ ገሠፁዋቸው። ዳግመኛም፡ በጐንደር ና፡ መከራቸው፡ በተሰማበት፡ በሌላ፡ አገር፡ ሕዝቡ፡ ሊቃውንቶቻቸውንና፡ ካህናቶቻቸውን፡ ነቀፉ። እመጫቲቱ፡ ሴት፡ ስንኳ፡ ስለ፡ ሃይማኖትዋ፡ እንዲህ፡ ሥቃይ፡ ስትቀበል፡ እንዴት፡ ካዱ፡ እያሉ፡ አደነቁ። እንግዴህ፡ ይህ፡ ስለ፡ ካቶሊካዊት፡ ሃይማኖት፡ የሆነ፡ ታላቅ፡ ምስክርና፡ ክብር፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ በዚያ፡ ዘመን፡ በጐንደር፡ | ስለ፡ ተገኙ፡ ከሆነ፡ በፍጹም፡ የጌታችን፡ የሱስ፡ ክርስቶስ፡ ጠላት፡ ካልሆነ፡ ሊነቅፍ፡ አይቻለውም። ሌላውም፡ የርሱን፡ መንቀፍ፡ ሰምቶ፡ በእግዜር፡ መልእክተኛ፡ በሞንሰኘር፡ ደዢቆብና፡ ላይ፡ ቢፈርድ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ በዳዊት፡ አፍ፡ አሌ፡ ሎን፡ ለከናፍረ፡ ጕሕሉት፡ እለ፡ ይነብባ፡ ዓመፃ፡ ላዕለ፡ ጻድቅ፡ ያለው፡ በርሱ፡ ላይ፡ ይሆናል። | ከዚህ፡ በላይ፡ የጠራኋቼው፡ ምክንያት፡ የካቶሊክ፡ ሃይማኖት፡ ባጋሜ ና፡ በዳባኵነይቶ፡ የተነገረች፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ አጤ፡ ዮሐንስን፡ ለመምከር፡ ከሞንሰኘር፡ ደዢቆብና፡ በፊት፡ መጥተው፡ በዚያ፡ ዘመን፡ በጐንደር፡ ነበሩ። በእጨጌውና፡ በሊቃውንቱ፡ በካህናቱም፡ ዘንድ፡ ስለ፡ ትምርትዎ፡ እጅግ፡ የታወቁ፡ ነበሩ። ስለዚህም፡ ወደ፡ ሮም፡ ሳይሔዱ፡ ላቶ፡ ዮ | ሐንስ፡ ያጼ፡ ተክለ፡ ጊዮርጊስ፡ ልጅ፡ ኋላ፡ አጼ፡ ዮሐንስ፡ ለተባሉቱ፡ መምር፡ ነበሩ። እርስዎም፡ ላጼ፡ ፋሲል፡ ስድስተኛ፡ ትውልድ፡ ነዎ። የራስ፡ ዓሊን፡ እናት፡ እተጌ፡ መነንን፡ አግብተው፡ የነገሡባትም፡ ጊዜ፡ ከጌታችን፡ ልደት፡ በኋላ፡ ባ፲፰፻፴፪ኛ፡ ዓመት፡ ነው። ስለዚህ፡ ባንድ፡ አካል፡ የተወሐዱ፡ የጌታችን፡ የየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ባሕርያት፡ ሁለት፡ እ ንደሆኑ፡ መጻፋችን፡ ይናገራል፡ አባቶቻችንም፡ በተዓቅቦ፡ ሁለት፡ ባሕርይ፡ ካሉ፡ ብለው፡ ሮማውያንም፡ ከቶ፡ ንስጥሮሳውያን፡ እንዳልሆኑ፡ በእውነት፡ ተወሐደ፡ እንዲሉ፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ሰምተው፡ ካቶሊክ፡ ሆኑ። ኋላ፡ ግን፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ከርሳቸው፡ ጋራ፡ በመቅደላ፡ ሲያኖሩዋቸው፡ ነበሩ። እርሳቸው፡ ግን፡ ድል፡ ከሆኑ፡ በኋላ፡ ወዳክሱም፡ መጡ። ከጌታችንም፡ ልደት፡ በኋላ፡ ባ፲፰፻፷፮ ዓመት፡ አመ፡ ፲፬ ለጥቅምት፡ ካቶሊክ፡ ሃይማኖትን፡ ታምነው፡ አረፉ። ያባትዎ፡ መ | ቃብር፡ በዚያ፡ ነውና፡ በዚያው፡ ተቀበሩ። አቡነ፡ ሰላማ፡ ይህነን፡ ሁሉ፡ ሰምተው፡ ከሁሉ፡ ይልቅ፡ ባባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ላይ፡ እጅግ፡ ሲናደዱ፡ ነበሩ። በታኅሣሥ፡ ፳፮ኛ፡ ቀን፡ ከጌታችን፡ ልደት፡ በኋላ፡ ባ፲፰፻፵፯ ዓመት፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ አጼ፡ ቴዎ፡ ካምባጫራ፡ መጥተው፡ ታኃሜዳ፡ በሚባለው፡ ሰፈሩ። አቡን፡ ከዚህ፡ በላይ፡ እንዳልኍ፡ የካቶሊካውያንን፡ ጫንቃ፡ በመናደድና፡ በጅራፍ፡ ሲያሳርሱ፡ ውለው፡ ደክምዋቸው፡ ሳለ፡ ይልቁንም፡ የልባቸው፡ ክፋት፡ የፈለገችው፡ ባለመሆኑ፡ እጅግ፡ አዝነው፡ ሳለ፡ ማተውን፡ በዚያች፡ ቀን፡ በታኅሣሥ፡ ፳፯ት፡ የልደት፡ ዕለት፡ በይስሐቅ፡ ደብር፡ ቀድሰው፡ እንዲያቈርቡኝ፡ ይምጡ፡ ብለው፡ ላኩባቼው። አቡን፡ እጨጌም፡ የጐንደርም፡ ካህናት፡ ሁሉ፡ በነገታው፡ ወደዚያው፡ ተነሡ። ምስጋና፡ ይግባውና፡ ጌታችን፡ የሱስ፡ ክርስቶስ፡ ወባሕቱ፡ ትመጽእ፡ ሰዓት፡ ከመ፡ ኵሉ፡ | ዘይቀትለክሙ፡ ይመስሎ፡ ከመ፡ ዘመሥዋዕተ፡ ያበውእ፡ ለእግዚአብሔር፡ ዮሐ፡ ወን፡ ፲፮ ፩። እንዳለ፡ አቡን፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልን፡ በዚያ፡ እንዲሠዉዋቸው፡ ይዘዋቸው፡ ሔዱ። አቡን፡ ከቀደሱ፡ ገዢውም፡ ከቈረቡ፡ በኋላ፡ በ፪ኛው፡ ቀን፡ ሠኞ፡ ደጃዝማች፡ በማኸል፡ አቡንና፡ እጨጌም፡ በቀኝና፡ በግራ፡ የቀሩትም፡ መኳንንት፡ እንደ፡ መዓርጋቸው፡ ተራ፡ በዚያ፡ ተቀምጠው፡ ሳሉ፡ ታላቅ፡ መጋቢያ፡ ሆኖ፡ ሳለ፡ ልብስዎ፡ የተገፈፉቱ፡ በሰንሰለትም፡ የታሠሩቱ፡ በረኃብና፡ በሌላውም፡ ሥቃይ፡ የመነመኑቱ፡ የክርስቶስ፡ በግ፡ በነዚህ፡ ፊት፡ ቆሙ። አቡን፡ ገዢውን፡ እነሆ፡ እህ፡ ሰው፡ ትእዛዝኸን፡ መፈጸም፡ እምቢ፡ አለ። በዚያ፡ ለቀሩቱም፡ ዓራቱ፡ በክፋታቸው፡ እንዲጠኑ፡ አብነታቸው፡ እርሱ፡ ነው። ስለዚህ፡ እንድትቀጣልኝ፡ ወዳንተ፡ አመጣሁት፡ አሉ። ገዢውም፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልን፡ አባቴ፡ የፈረንጅን፡ ገንዘብ፡ | ለማግኘት፡ ሃይማኖትሁን፡ የተውኍ፡ ይመስለኛልና፡ አሁንም፡ ሹመትንም፡ በቅሎም፡ አድርጌ፡ እስጥኃለኍ፡ ወደ፡ ሃይማኖታችን፡ ግቡ፡ አሉ። እህነንም፡ የመሰለ፡ ሌላን፡ ቃል፡ ተናገሩ። አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ግን፡ የኔታ፡ ሆይ፡ እኔ፡ ይህ፡ ሁሉ፡ የተናገሩትን፡ ገንዘብ፡ ፈልጌ፡ ሹመትንም፡ ፈልጌ፡ እንዳልሆንኍ፡ በዚህ፡ ያለ፡ ሁሉ፡ ካህን፡ ያውቅልኛል። ቀድሞ፡ በሃይማኖት፡ ያገራችን፡ ሰዎች፡ ወደ፡ ሶስት፡ ወገን፡ መከፈልን፡ በርሱም፡ ምክንያት፡ የመጣን፡ ጥል፡ አይቼ፡ ከሊቀ፡ ጳጳሳት፡ አባ፡ ጴጥሮስ፡ ምስር፡ በትረክ፡ ሶስቱ፡ ባንዲት፡ ሃይማኖት፡ እንዲሆኑ፡ የምትናገርን፡ መልእክት፡ ባመጣ፡ አቡን፡ ቀሙኝ፡ አሉ። ነገርዎንም፡ ሳይጨረሱ፡ አቡን፡ እነሆ፡ ዛሬ፡ በዚያ፡ ባመጣኍ፡ መልእክት፡ ሃይማኖት፡ ግባ፡ አሉዎ። እርስዎ፡ ግን፡ እጅግ፡ መልካም፡ እውነተኛም፡ ሃይማኖት፡ መርጨ፡ እዣለኍና፡ ዛሬስ፡ አልፈልተውም፡ አ | ሉ። በዚህ፡ ጊዜ፡ ይመስለኛል፡ የጐንደር፡ አደባባይ፡ አቡነ፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ አለቃ፡ ገብረ፡ ማርያም፡ ኦሪት፡ አዕረፈ፡ እምኵሉ፡ ግብረ፡ እያለ፡ በየለቱ፡ ነፍስን፡ ይፈጥራል፡ የሚሉ፡ የፈረንጆች፡ ሃይማኖት፡ ደግሞ፡ ቁም፡ ነገር፡ ሆነ። የኔታ፡ እኔን፡ ያከራክሩኝ፡ ብለው፡ ደነፉ። አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ግን፡ በለዘብታ፡ ወንድሜ፡ ሆይ፡ አቡየሂ፡ እስከ፡ ይእዜ፡ ይገብር፡ ወአነሂ፡ እግበር፡ ያለውን፡ ባታውቁ፡ ነው፡ ብለው፡ በመለሱ፡ ጊዜ፡ በዚያ፡ ያሉ፡ ጉባዔ፡ ሁሉ፡ በመልካም፡ አተያየት፡፡ ወደርስዎ፡ እንደ፡ ተመለከተ፡ አለቃም፡ ለዚህ፡ ነገር፡ ምላሽን፡ አጥተው፡ እንዳፈሩ፡ አይተው፡ ገዢው፡ ማን፡ ተከራከልኝ፡ አለው፡ ብለው፡ ባለቃ፡ ላይ፡ ተቈጡ። አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልን፡ አባቴ፡ | እንግዴህ፡ በፍትሐ፡ ነገሥት፡ ፍርድ፡ ወይ፡ ትሞታለኍ፡ ወይም፡ ትድናለኍ፡ አሉዎ። እርስዎም፡ እንዲህ፡ ከሆነስ፡ ዛሬ፡ ያድርጉል ኛ፡ አሉ። ግዚው፡ ተቈጡ። | አንተ፡ ብለው፡ በገዛ፡ እጅህ፡ ትሞት፡ እንደሆን፡ እንጂ፡ ዛሬስ፡ አይሆንም፡ አሉ፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልም፡ በገዛ፡ እጄ፡ የምሞት፡ ይሁዳን፡ ነኝ፡ አሉ። እንዳሉትም፡ ይህ፡ በገዛ፡ እጃቸው፡ ኋላ፡ ለሞቱቱ፡ ላጼ፡ ቴዎድሮስ፡ እውነተኛ፡ ትንቢት፡ ሆነ። ከዚህ፡ በኋላ፡ ገዢው፡ አፈ፡ ንጉሥ፡ ቃንዚሌ፡ ወርቁን፡ ንሣ፡ ይህነን፡ መነኵሴን፡ ተቀብለህ፡ አስጠብቅ፡ አሉ። ካቡን፡ ሰንሰለት፡ ወደ፡ ገዢው፡ ሰንሰለት፡ ሲያልፉ፡ ለብሰዋት፡፡ የነገረችን፡ ጨርቅ፡ ገፈፈዎ። ቃንዚሌ፡ ወርቁ፡ በማዕድ፡ ከርሳቸው፡ ጋራ፡ እያስቀመጡ፡ መገቡዎ። እንዳባትዎም፡ አከበሩም። ነገር፡ ግን፡ ጌታቸውን፡ ስለ፡ ፈሩ፡ ልብስን፡ አልሰጡዎም። ደጃዝማች፡ ውቤንም፡ ከተሻሩ፡ ባኋላ፡ መታሠራቸው፡ በርሳቸው፡ ዘንድ፡ ስለ፡ ሆነ፡ ከርሳቸው፡ ጋራ፡ ማብላት፡ ቀረብዎ። ከዚህ፡ በኋላ፡ በሁለተኛው። ወር፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ ደጃዝማች፡ | ውቤን፡ ደቦላ፡ በምትባል፡ በስሜን፡ ባለች፡ ተዋግተው፡ ድል፡ አድርገው፡ በሶስተኛው፡ ቀን፡ እሑድ፡ በየካቲት፡ ሁለተኛ፡ ቀን፡ ከጌታችንም፡ ልደት፡ በኋላ፡ ባ፲፰፻፵፯ ዓመት፡ደረስጌ፡ ነግሠው፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ተባሉ። ከነገሡም፡ በኋላ፡ ዋልድባን፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ ግዛት፡ የነበረም፡ ሁሉ፡ ሌላ ው፡ ገዳም፡ ካህንም፡ ሁሉ፡ ወዳቡን፡ መጥቶ፡ ሃይማኖትን፡ እንዲቀበል፡ ባላባትም፡ ነኝ፡ የሚል፡ ሁሉ፡ ወደዚያ፡ እንዲመጣ፡ አዋጅ፡ ተነገረ። ስለዚህ፡ ሁሉ፡ ወዳቡንና፡ ወደርሳቸው፡ ተሰበሰበ። ሁሉን፡ ለማስፈራት፡ በዚህ፡ ወር፡ ንጉሥ፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ወደ፡ ፈታቸው፡ አስመጥተው። በብርቱ፡ አስገረፉዋቸው። ከሰንሰለቱ፡ በላይ፡ የፊጥኝ፡ ታሠሩ። ወደ፡ ግራና፡ ወደ፡ ቀኝ፡ ተገተሩ። ረዣዢም፡ አኮርማጅን፡ የያዙ፡ ዓራት፡ ሰዎች፡ ቀረቡ። ባንድ፡ ግዜ፡ ሁለቱ፡ ሲገርፉዎ፡ ሁለቱም፡ ሲደክሙ፡ ሁለቱ፡ ፈንታቸውን፡ እ | ንዲዠምሩ፡ ሃይማኖቱን፡ እስኪለውጥ፡ በሉት፡ አሉ። ዳግመኛም፡ ንጉሥ፡ የሮም ን፡ አምልኮ፡ በብርቱና፡ በክፉ፡ ሲሰድቡ፡ ነበሩ። ለዚህ፡ ምን፡ ክርስትና፡ አለውና፡ ማተብ፡ ያሥራል፡ ቈርጣችኍ፡ ጣሉት፡ አሉ። ስለዚህ፡ እስካፖላሬና፡ መስቀል፡ የእመቤታችንም፡ መዳይልያ፡ ባንገትዎ፡ የነበረን፡ በጥሰው፡ ጣሉት። አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ግን፡ እርሳቸው፡ የሰደቡትን፡ ሲያመስግኑ፡ ሲታመኑም፡ ነበሩ። እንዲህ፡ እያሉ። ጌታዬን፡ አምላኪዬን፡ አምላክነቱን፡ እንዳመንኍ፡ ሰውነቱንም፡ ከቶ፡ አልክዳውም፡ እያሉ፡ በታላቅ፡ ቃል፡ ስብሐት፡ ለአብ፡ ስብሐት፡ ለወልድ፡ ስብሐት፡ ለመንፈስ፡ ቅዱስ፡ እያሉ፡ ሲያመስገኑ፡ ነበሩ። በዚህ፡ ማኸል፡ ወደቁ። የሞቱ፡ መስሎዋቸው፡ ገራፎች፡ ተግ፡ አሉ፡ በዚያ፡ አደባባይ፡ የነበረው፡ ሰው፡ ሁሉ፡ በግርፋትዎ፡ ብዛት፡ ሲፈራ፡ ሲንቀጠቀም፡ ነበረ። እርስዎ፡ ግ | ን፡ በመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ኃይል፡ መበርታትዎን፡ ስለ፡ ሃይማኖትም፡ ምንምን፡ መፍራትን፡ ሳያሳዩ፡ በጀግንነት፡ መዋጋትዎን፡ ለማሳየት፡ በዚያ፡ ወድቀው፡ ሳሉ፡ ገራፎችን፡ ደካማችኍን፡ አሉ። ንጉሥ፡ ይህነን፡ ሰምተው፡ ያደንቁ፡ ይመስል፡ ተቈጡ። ገራፎችን፡ ከበፊት፡ አብልጠው፡ እንዲጥሉባቸው፡ አዘዙ። ከሱሪ፡ በቀር፡ ሌላ፡ ልብስ፡ አልነበረዎም። እርስዋም፡ በግርፋቱ፡ ብዛት፡ ተበዝታ፡ ዕራቁትዎን፡ ሆኑ። አንዲቱ፡ ዓይኑዎ፡ ቀድሞ፡ ጠፍታለች። ነገር፡ ግን፡ ስለ፡ እውቀትዎ፡ ብዛት፡ ዓራት፡ ዓይን፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ሲባሉ፡ ነበሩ። ንጉሥ፡ ደኅናይቱን፡ ዓይኑን፡ በለው፡ አሉ። ከሌላው፡ ገላዎ፡ ደም፡ አልወጣም፡ ከርስዋ፡ ግን፡ ብዙ፡ ደም፡ ፈሰሰ። ዳግመኛም፡ በግዕዝ፡ ከተማ፡ ነፍስት፡ የተባለውን፡ ሕዋስ፡ የሽንት፡ መንገድ፡ ስሙን፡ እየጠፋ፡ ያነን፡ በለው፡ አሉ። ገራፎችም፡ ጌታቸውን፡ ስለ፡ ፈሩ፡ በፍጹም፡ ኃይላቸው፡ ቀጠቀ | ጡ። ነገር፡ ግን፡ ያለ፡ እግዜር፡ ፈቃድ፡ አንዲት፡ ቅጠል፡ ስንኳ፡ አትወድቅም፡ የተባለው፡ እንዲገለጥ፡ ስንኳንስ፡ ነፍስዎን፡ ከሥጋዎ፡ ሊለዩ፡ ድምጽዎን፡ ስንኳ፡ ማድክም፡ አልተቻላቸውም። በዚያ፡ አደባባይ፡ የነበሩ፡ አንዱ፡ ወገን፡ አለመሞታቸው፡ ይህን፡ ያህልም፡ ሲገረፉ፡ ከገላቸው፡ ደም፡ አለመውጣት፡ የመድኃኒት፡ ነው፡ አሉ። የሚበዙቱ፡ ግን፡ ይህስ፡ ለቅዱስ፡ ጊዮርጊስ፡ እንደ፡ ተደረገለት፡ ያለ፡ ተአምራት፡ ነው፡ አሉ። ስለዚህ፡ ከዚያ፡ በኋላ፡ አባ፡ ገብረ፡ ሚካኤልን፡ ማለት፡ ትተው፡ ሰማዕት፡ ጊዮርጊስ፡ ሲሉዎ፡ ነበሩ። ዓይንም፡ በዚያ፡ ቀን፡ ምንምን፡ የማታይ፡ ሆነች። በሚከተለው፡ ሌሊት፡ ግን፡ እንጃ፡ ከእግዝእትነ፡ ማርያም፡ የተላከች፡ ይመስለኛል፡ አንዲት፡ ሴት፡ ያይንዎን፡ ቍስል፡ አጠበች፡ ለስታ፡ ቅቤን፡ ቀባችዎ። ወዲያው፡ ቦግ፡ አለ። ከበፊት፡ ይልቅ፡ የበራ፡ ሆነ። ከተገረፉ፡ በኋላ፡ በሁለተኛ፡ ወይ | ም፡ በሶስተኛ፡ ወን፡ ንጉሥን፡ ከነሠራዊትዎ፡ ጋራ፡ የሚያንቀጠቅጥ፡ ወሬ ፡ መጣ። ስለዚህ፡ ከስሜን፡ ወደ፡ ጋላ፡ አገር፡ ሊዘምቱ፡ ተነሡ። ምክንያቱ፡ ግን፡ ኋላ፡ እጽፋለሁ። አቡንና፡ ንጉሥ፡ እግዜር፡ በፊታቸው፡ ያደርገውን፡ የባርያውን፡ ጥናት፡ ስላላመኑ፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልን፡ አንለቅም፡ አሉ። ቍረኛን፡ አግብተው፡ ነዱዋቸው። በጐንደር፡ ያለች፡ የቅዱስ፡ ገብርኤል፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ እርስዋም፡ ያቡን፡ መኖርያ፡ በምትሆን፡ ያሉ፡ አለቃ፡ ወልደ፡ ጊዮርጊስ፡ እንዲህ፡ አሉኝ። እኛ፡ የተመቱ፡ ቀን፡ የሞቱ፡ መስሎነ፡ ነበረ። ኋላ፡ ግን፡ ዓይንዎ፡ ጠፉ፡ እንጂ፡ አልሞቱም፡ አሉነ። ኋላም፡ ከስሜን፡ እስከ፡ ወገራ፡ ስንጓዝ፡ ዓይንዎ፡ በፍጹም፡ እንደዳኑ፡ ጕልበትዎም፡ እጅግ፡ ስለጠናልዎ፡ እየተቈናዱ፡ ከፊታውራሮች፡ ጋራ፡ ሲሔዱ፡ አየሁዎ፡ አሉ። የሚጓቸውም፡ አባቴ፡ እግዜር፡ ያስፈታዎ፡ በምን፡ ምክንያት፡ ታሥረዋል፡ ይለዎ፡ ነበር። ሌሎቹ፡ ግ | ን፡ ሠልስትና፡ ስለ፡ ሃይማኖት፡ የተገረፉ፡ እኒህ፡ አይደሉምን፡ ያነን፡ ሁሉ፡ ሥቃይ፡ ተቀብለው፡ እንዴት፡ ሳይሞቱ፡ ቀሩ። አሁንስ፡ እንዴት፡ መንገድን፡ ቻሉ፡ እያሉ፡ ሲያደንቁ፡ ነበሩ። እግዜር፡ ሕዝቡ፡ ወደ፡ ቅድስት፡ የምስክር፡ ድንኳን፡ የሚሰበሰብበትን፡ መለከቶች፡ እንዲያሠራ፡ ሙሴን፡ አዞት፡ ነበረ። ከነዚያም፡ አንዱ፡ በዚያ፡ ዘመን፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ሆኑ። የሚጓዘው፡ ሠራዊት፡ ባንድ፡ ወገን፡ የንጉሥን፡ የነጋሪትን፡ ድምጽ፡ በሌላ፡ ወገንም፡ ያባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልን፡ ድምጽ፡ ይሰማ፡ ነበረ። የተቈራኘዎ፡ ጐበዝ፡ ጌታው፡ ቃንዚሌ፡ ወርቁ፡ ሲያከብሩዎ፡ አይትዋልና፡ እርሱም፡ አይደፋዎም፡ ነበረ። ከዚህ፡ በላይ፡ እንዳልኍ፡ ቶሎ፡ ቶሎ፡ ሒደው፡ ከፍ፡ ያለን፡ ስፍራ፡ ሲያገኙ፡ በዚያ፡ ተቀምጠው፡ በታላቅ፡ ቃል፡ መከራዎ፡ ስለ፡ ካቶኪካዊት፡ ሃይማኖት፡ ምክንያት፡ እንደሆነ፡ ጌታችን፡ የሱስ፡ ክርስ | ቶስ፡ ፍጹን፡ አምላክ፡ ፍጹም፡ ሰውም፡ እንደ፡ ሆነ፤ ዳግመኛም፡ ያ፡ ጊዜ፡ ሰሙነ፡ ሕማማት፡ ነበረና፡ ወንድሞቼ፡ ልጆቼ፡ ሁለተኛይቱ፡ የሰውነቱ፡ ባሕይማ፡ በተዋሕዶ፡ ከጠፋች፡ እንዴት፡ መድኃኔ፡ ዓለም፡ ተባለ፡ እያሉ። ይህነንም፡ የመሰለ፡ ሌላን፡ ቃል፡ ምንምን፡ ሳይፈሩ፡ ሊነግሩ፡ ነበሩ። ይህም፡ ከዚያ፡ ዠምሮ፡ እስካረፉበት፡ እስከ፡ ወርሂመኖ፡ የጋላ፡ አገር፡ ድረስ፡ ሆነ። | ንጉሥ፡ በሽሎ፡ የሚባልን፡ ታላቅ፡ ወንዝ፡ ተሻግረው፡ ባባ፡ በሚባል፡ ሰፍረው፡ ሳሉ፡ ሙሴ፡ ፕሎውዶን፡ የእንግሊዝ፡ ኰንሱል፡ ከምጽዋ፡ ተነሥተው፡ መጥተው፡ በዚያ፡ ተገናኙ። ኮንሱል፡ እንደ፡ መሆናቸው፡ አክብረው፡ ተቀብሉዋቸው፡ ይላሉ። ከተገናኙ፡ በኋላ፡ ግን፡ ንጉሥ፡ ታላቅ፡ መጋቢያ፡ አደረጉ። አቡንና፡ እጨጌ፡ በግራቸውና፡ በቀኛቸው፡ ተቀምጠው፡ እር | ሳቸውና፡ እነዚያም፡ ለየክብራቸው፡ የሚገባን፡ ተሸልመው፡ በግርማ፡ ነበሩ። ንጉሥ፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልን፡ አስመጥተው፡ እኔ፡ አባ፡ ታጠቅ፡ ክርስቶስ፡ ኃይል፡ ሁሉን፡ ዳኘኍ፡ ሁሉን፡ ቃኝኍ፡ መኳንንት፡ ሁላችኍ፡ እዩልኝ፡ ስሙልኝ፡ አሉ። ሶስት፡ ታላላቅ፡ ድንኳን፡ ተቀጣጥሎ፡ ተተክሎ፡ ነበረ። በዚያም፡ ያማራ ና፡ የትግሬ፡ መኳንንቶች፡ መልተውበት፡ ነበሩ። አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ በዚህ፡ ጊዜ፡ የመሰሉትን፡ ሰምተህ፡ እንዳትነቅፍ፡ ጌታችን፡ በፈሪሳውያን፡ ላይ፡ የተናገረው፡ በመንጌል፡ ፩ ያለውን፡ ዘለፋ፡ ትመልከት። ዳግመኛም፡ ቅዱስ፡ እስጢፋኖስ፡ ቀዳሜ፡ ሰማዕት፡ ኦጽኑዓነ፡ ክሳድ፡ ወጽሉላነ፡ ልብ፡ ወጽሙማነ፡ ዕዝን፡ እለ፡ ዘልፈ፡ ተቃወምክምዎ፡ ለመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ግብረ፡ ሐዋ፡ ፳፩ ያለውን፡ ታውቃለህ። ሊቀ፡ ካህና | ት፡ አማንኑ፡ ከመዝ፡ ትቤ፡ ብሎ፡ ለጠየቀው፡ የመሲሕን፡ ነገር፡ ከመዠመርያው፡ እስከ፡ መጨረሻው፡ በትሕትና፡ ካስረዳ፡ በኋላ፡ እንዴት፡ ይህነን፡ ያህል፡ ምስክር፡ እያወቃችኍ፡ አምላካችኍን፡ ክርስቶስን፡ እንደ፡ ሌባ፡ ቈጠራችሁት፡ እንዴትስ፡ ገደካችሁት፡ ብሎ፡ መዝለፉ፡ በልቡ፡ ባደረ፡ በመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ላዕለ፡ ሳውል፡ ዘውእቱ፡ ጳውሎስ፡ ወነጸሮ፡ ወይቤሎ፡ ኦጽጉበ፡ ኃጢአት፡ ወኵሉ፡ እከይ፡ ወልዱ፡ ለሰይጣን፡ ፀራ፡ ለኵላ፡ ጽድቅ፡ አበይከ፡ ትኀድግ፡ እንዘ፡ ተአሉ፡ ፍኖተ፡ እግዚአብሔር፡ ርቱዓ፡ ግብረ፡ ሐዋ፡ ፲፫ ፲ አለው። አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልም፡ ከታሠሩ፡ ዠምሮ፡ እስከዚያ፡ ጊዜ፡ ድረስ፡ ንጉሡንና፡ አቡኑን፡ በክብር፡ ስም፡ ሲጠሩ፡ ነበሩ። ከሐምሌ፡ ዠምረው፡ እስከ፡ ግንቦት፡ ድረስ፡ የካቶሊክ፡ ሃይማኖት፡ ብቻ፡ እውነተኛ፡ እን | ደ፡ ሆነች፡ በቃልዎ፡ ይልቁንም፡ ብርቱ፡ ሥቃይ፡ በመቀበልዎ፡ አስረድተው፡ ነበሩ። አቡንና፡ ንጉሥ፡ ግን፡ ይህነን፡ የእግዜር፡ ኃይል፡ ንቀው፡ ወትሮ፡ በቅድስት፡ ሃይማኖት፡ ላይ፡ ስድብን፡ ስላበዙ፡ መንፈስ፡ ቅዱስም፡ የሰውን፡ ትዕቢት፡ ለማዋረድ፡ ለምእመኑ፡ ለባርያው፡ ኃይሉን፡ መላ። አንተ፡ እያሉ፡ በጀግንነት፡ ቃል፡ ምንምን፡ ሳይፈሩ፡ የኔ፡ ዳኛ፡ በላይ፡ ጌታዬ፡ የሱስ፡ ክርስቶስ፡ ከርሱም፡ በታች፡ የሮም፡ ሊቀ፡ ጳጳስ፡ ነው፡ ዳኛዬ። አንተ፡ ለመቅሠፍት፡ ነህ፡ አቡንህም፡ ሰይጣን፡ ነው፡ አሉ። ጥያቄ፤ ኮንሱል፡ ፕሎውዶን፡ በዚያ፡ ነበሩና፡ ይህሳ፡ ከባሕር፡ ወዲያ፡ የመጣው፡ አይዳኝህንም። ምላሽ። አዎይ፡ ደግሞ፡ ዛሬስ፡ ረቡና፡ ዓርብ፡ የሚያውቁ፡ ፀረ፡ ማርያም፡ የሮማውያን፡ ዳኞች፡ ሆኑ። | ከርሱማ፡ አንተ፡ አትሻልምን፡ አሉ። ከዚህ፡ በኋላ፡ ንጉሥ፡ አውጥታችኍ፡ ደብድቡ፡ አሉ። እርስዎም፡ ለዚህስ፡ ዳኛ፡ ነህ፡ አሉ። እያዳፉ፡ ባለወግ፡ ወደሚደበደቡበት፡ አድርሶ፡ የፍጥኝ፡ ታሥረው፡ ነፍጠኛም፡ መጥቶ፡ ሊተኵስብዎ፡ ቀርቦ፡ ሳለ፡ ተው፡ ባይ፡ መጣ። ኮንሱል፡ ፕሎውደን፡ ቁመው፡ ጃንሆይ፡ ስለኔ፡ ብለው፡ ይማሩልኝ፡ ብለው፡ ለመኑ። ነገር፡ ግን፡ ይህነን፡ ስለ፡ ጥበባቸው፡ ያደረጉት፡ ይመስለኛል። በዚያ፡ ዓመት፡ በኤውሮፓ፡ ዡርናል፡ በሚባለው፡ የወሬ፡ ወረቀት፡ እንግሊዞች፡ ወይም፡ ፀረ፡ ማርያም፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ ስለ፡ ማባረራቸው፡ አጼ፡ ቴዎድሮስን፡ እያመሰገኑ፡ ጽፈው፡ ነበሩ። የካቶሊካውያን፡ ዡርናል፡ ግን፡ የሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ ስደትና፡ የወንድሞቻቸውን፡ ሥቃይ፡ ሰምተው፡ አሁን፡ ባፍሪቃ፡ ባለች፡ በኢትዮጵያ፡ አዲስ፡ ዲዮቅልጢያኖስ፡ ተነሣ፡ ብለው፡ ሲያትሙ፡ ነበሩና፡ መመናቼው፡ ያጼ፡ ቴዎድሮ | ስ፡ ስም፡ ጭራሽ፡ እንዳከፋ፡ ነው። | ከዚህ፡ በኋላ፡ ንጉሥ፡ ከዚያ፡ ወደ፡ ሌላ፡ አገር፡ አልፈው፡ በሰፈሩ፡ ጊዜ፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልን፡ ዳግመኛ፡ በብርቱ፡ እንስገረፉዎ፡ ሰማኍ። ወደ፡ ወርሄመኖ፡ ወደ፡ ሰዲቅ፡ አብሮዬ፡ አገር፡ በዕሥራትና፡ በግርፋት፡ በመንገድም፡ ለእግዜር፡ ፲፫፡ ወር፡ ካገለገሉ፡ በኋላ፡ በዘያው፡ ዓመት፡ በነሐሴ፡ ፳፫ኛ፡ ወይ፡ ፳፬ኛ፡ ቀን፡ ፩ ታሥረው፡ ሳሉ፡ በራብና፡ በሆድ፡ ተቅማጥ፡ አረፉ። ጌታችን፡ የሱስ፡ ክርስቶስ፡ በቅድስት፡ ድንግል፡ ማርያም፡ እናቱ፡ አመላጅነት፡ የእውነተኛይቱ፡ ሃይማኖት፡ ምስክርና፡ መብራት፡ እንዲሆኑን፡ የሚያጠና፡ ጸውን፡ ስለ፡ ሰጠዎ፡ ለዘላለም፡ ይክበር፡ ይመስገን። አሜን። ነገር፡ ግን፡ የርስዎ፡ ነገር፡ ከመዠመርያው፡ እስከ፡ መጨረሻው፡ የካቶሊካውያን፡ ታሪክ፡ በተጻፈበት፡ መጻፍ፡ በግዕዝ፡ ተጽፎዋል። ከዚያው፡ ግን፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ በዚያ፡ ዘመን፡ የሙሴ፡ | ደዢቆብ፡ ካቡን፡ ጋራ፡ ለመጣላት፡ ወደ፡ ጐንደር፡ መድረሱ፡ ያልታመረች፡ ማለታቸው፡ የመሳሳት፡ ወይም፡ የጥመት፡ መሆንዋን፡ እንድታይ፡ ይህነን፡ ጻፍሁልህ። |
chapter ()
Alignment Start a translation alignment with Alpheios Alignment. You can also add morphological annotations there. See instructions in GitHub.
Versions See parallel versions if any is available
Quotations Check for marked up quotations of a passage in this section
back to top
፭ኛ፡ ክፍል። | ታሪከ፡ ነገሥት፡ እንዳለ፡ የምንይልሕክ፡ ልጆች፡ ባፈራዋናት፡ እስከ፡ ተሻሩቱ፡ እስከ፡ አጼ፡ ተክለ፡ ጊዮርጊስ፡ ድረስ፡ የኢትዮጵያ፡ ከነገሥታት፡ ነበሩ። ፩ የእግዜርን፡ ሕግ፡ ስላልጠበቁ፡ ግን፡ በጌምድርን፡ የገዙ፡ የወረሴክ፡ ወገን፡ ታላቁ፡ ዓሊ፡ ያጼ፡ በካፋ፡ ልጅ፡ ወለተ፡ እስራኤልንም፡ ያገቡ፡ ራስ፡ ኃይሉ፡ የጎዢም፡ ሸፍተው፡ ባፍራዋናት፡ ጌታቸውን፡ አጼ፡ ተክለ፡ ጊዮርጊስን፡ ወጉ፡ ሻሩም። ከዚያም፡ ዘመን፡ ዠምሮ፡ እኒህ፡ ሁለቱ፡ ራሶችና፡ የስሜኑ፡ ራስ፡ ገብሬ ፤ የትግሬውም፡ ራስ፡ በያገራቸው፡ ለራሳቸው፡ እንደ፡ ንጉሦች፡ ሆኑ። በጌምድርን፡ ከገዙቱ፡ ከራስ፡ ጉግሣ፡ ዠምሮ፡ እስከ፡ ኋለኛው፡ ራስ፡ ዓሊ፡ ድረስ፡ ፶፰ት፡ ዓመት፡ | ጋሎች፡ ገዙ። ሙሴ፡ ለዤአን፡ ግን፡ ፴፪ት፡ ዓመት፡ ነው፡ ማለታቸው፡ ተሳስተው፡ ነው። የጎዢሙም፡ ከራስ፡ ኃይሉ፡ ዥምሮ፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ የገደሉዋቸው፡ ደጃዝማች፡ ጐሹ፡ ሶስተኛ፡ ትውልድ፡ ይመስለኛል። የስሜኑም፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ ለራስ፡ ገብሬ፡ ሶስተኛ፡ ናቸው። እኒህ፡ ሁሉም፡ ሥልጣናቸው፡ የልጅ፡ ልጅ፡ መምጣትዋን፡ አይተው፡ በትዕቢታቸው፡ የእግዜር፡ መንገድ፡ ተው። እግዜር፡ ግን፡ ኃይሉን፡ ሊያሳያቸው፡ ሁላቸው፡ ያላሰብዋትን፡ ሰይፉን፡ ያልታወቁ፡ በነበሩ፡ ሰው፡ እጅ፡ መዘዘባቸው። ፩ በሁለት፡ ዓመት፡ እኒህን፡ ሁሉ፡ አጠፋች። ከኒህም፡ በኋላ፡ ወዲያው፡ በጋሎች ና፡ በሸዎች፡ አንገት፡ ላይ፡ ተቀመጠች፡ ከዚህ፡ በፊትም፡ እንዳልኍ፡ በሃይማኖት፡ በሶስት፡ የተከፈሉም፡ መምህራን፡ አንዱ፡ ላይ፡ እኔ፡ እበልጣለኍ፡ ሃይማኖቴም፡ ከሁሉ፡ ትበልጣለች፡ እያለ፡ ሲመካ፡ ነበረ። ያለ፡ ጳጳስ፡ ቄስ፡ አይገኝምና፡ ያለቄ | ስም፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ አይከፈትምና፡ ያለዚህም፡ ሪም፡ አይገኝምና፡ ብሎ፡ በሃይማኖት፡ የማይገጥመውን፡ ጳጳስ፡ አደረገ። ቄሱ፡ በመቅደስ፡ ጳጳሱን፡ ብፁዕ፡ አባ፡ ሰላማ፡ ይል፡ ነበረ። ደብተራው፡ ግን፡ በቅኔ፡ መዓልት፡ ስሙ፡ እንዘ፡ ብርሃን፡ መንገለ፡ ጽልመት፡ ይመርሃነ። ሌላውም፡ ኢያምጻእነ፡ ሰላመ፡ አላ፡ መጥባሕተ፡ ግብጽ፡ እያለ፡ ሲሰድብ፡ ነበረ። ይህም፡ | ግብዝነት፡ አምልኮ፡ ለእግዜር፡ እጅግ፡ ፀርፈት፡ ነበረና፡ እኒህንም፡ ሁሉ፡ ደመሰሰች። እንግዴህ፡ እኒህን፡ ሁሉ፡ ስላሸነፉ፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ከተደነቁ፡ ስማቸውም፡ ባለም፡ ሁሉ፡ ከታወቀች፡ ይልቁንም፡ በላይ፡ የተጠሩ፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ እርሳቸውን፡ ያሸነፉ፡ በሁሉ፡ ኢትዮጵያ፡ እንደ፡ ተደነቁ፡ የታወቀ፡ ነው። ወከደነ፡ አድባረ፡ ጽላሎታ፡ እንዳለም፡ በርስዎ፡ መጥናት፡ የካቶሊካዊት፡ ሐዋርያዊት፡ ሮማዊት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ሃይማኖት፡ ጥላ፡ የኢትዮጵያ፡ መምህራን፡ ተራሮች | ን፡ እንደ፡ ጋረደ፡ በሁሉ፡ ዘንድ፡ የተገለጠ፡ ነው። አጼ፡ ቴዎድሮስም፡ ባለቤታቸው፡ ከዚህ፡ ደካማ፡ በቀር፡ ሁሉን፡ አቸነፍሁ፡ እንዳሉ፡ ከዚህ፡ በላይ፡ አይተናል። ከዚህም፡ በኋላ፡ ባገሬ፡ ከሁለት፡ ሰዎች፡ በቀር፡ ሌላ፡ አላገኘሁም፡ አስልም፡ ብለው፡ ሁሉ፡ ባሰለመ፡ ይመስለኛል፡ አሉ። እንግዴህ፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ሳይነግሡ፡ ካቶሊካውያንን፡ ላቡን፡ ከሰጡ፡ በኋላ፡ በ፫ኛው፡ ወር፡ ይመስለኛል፡ የደብረ፡ ዳሞ፡ መምር፡ አስካልን፡ ሊቀ፡ ጣባብት፡ ወልደ፡ ሩፋኤልን፡ ሌሎችንም፡ ሊቃውንቶች፡ ሰብስበው፡ በሃይማኖት፡ በሃይማቶት፡ (!) (!)corrected by Daria Elagina ምክንያት፡ መግደል፡ ይገባልን፡ ብለው፡ ጠየቁ። እነዚያም፡ ፍትሐ፡ ነገሥት፡ በፊት፡ መጠየቅ፡ መምከር፡ እምቢ፡ ግን፡ ቢሉ፡ አውግዘው፡ ይለዩት፡ ይላልና፡ ስደት፡ ይገባዋል፡ እንጂ፡ መግደልስ፡ አያዝም፡ ብለዋቸው፡ ነበሩ። በፊተኛውም፡ እንዳየነ፡ ባለቤታቸው፡ በፍትሐ፡ ነገሥት፡ ትሞታለኍ፡ ወይም፡ ትድናለኍ፡ ብለ | ዋቸው፡ ነበሩ። ከዚያም፡ በፊት፡ አቡን፡ ባምባጫራ፡ በመዥመርያ፡ ሲገናኙ፡ ያዕቆብን፡ አባርልኝ፡ ቢሉዋቸው፡ ንጉሥ፡ በፊት፡ አስመጥቼ፡ ልጠይቀው። አቡን፡ ግን፡ በግምባሩ፡ የሚያስት፡ አለበትና፡ መገናኘትስ፡ አይሆንም፡ አሉዋቸው። ንጉሥ፡ በነፍስህ፡ እያዝኃለኍ፡ ይበሉኝ፡ እንጂ፡ አንገት፡ አንገቱን፡ በጐራዴ፡ እቈርጠዋለኍ፡ አሉ። አቡን፡ በዘመናችን፡ የወንጌልን፡ ሥራ፡ የጠበቀ፡ እንደርሱ፡ አይገኝምና፡ ሞትስ፡ አይገባውም፡ አሉ። ዳግመኛም፡ ከዚህ፡ በኋላ፡ በ፫ኛው፡ ወር፡ በመስቀል፡ በዓል፡ እንዲያቈርቡዋቸው፡ አቡንና፡ እጨጌን፡ ወዳምባጫራ፡ አስጠሩ። ሁሉም፡ ወደዚያ፡ በተሳቡ፡ ጊዜ፡ አቡን፡ ደጃዝማች፡ ካሳን፡ አጼ፡ ቴ፡ | በግፍ፡ ያሠርኸውን፡ ሳትፈታ፡ የተጣላኸውንም፡ ሳትታረቅ፡ ላቈርብህ፡ አይገባኝም፡ አሉ። ገዢው፡ ግን፡ ይህነን፡ ሰምተው፡ ባቡን፡ ላይ፡ ተቈጡ። ይህ፡ ግብጥ፡ እኔ፡ እንደ፡ ደጃዝማች፡ ውቤን፡ መስሎታ | ል። በስናር፡ እኮ፡ መስደድ፡ አውቃለኍ። አንተ፡ ብትተወው፡ የነፍስ፡ አባቴ፡ መምር፡ ወልደ፡ ትንሣኤ፡ አያቈርቡኝምን፡ አሉ። ሶስት፡ ቀን፡ ካለፈ፡ በኋላ፡ | ግን፡ አቡን፡ በመፍራት፡ ቃላቸውን፡ ለወጡ፡ አቈረቡዋቼው። ሙሴ፡ ሌዢአን፡ ግን፡ አቡን፡ ካሳን፡ ሠራዊቱንም፡ ግዘተ። ካሳም፡ ይህ፡ ግዝት፡ ከንቱ፡ ነው፡ አላቸው፡ አቡነ፡ ያዕቆብ፡ ከርሱ፡ የሚበልጥ፡ ሥልጣን፡ አለውና፡ ከዚህ፡ ግብጥ፡ ግዝት፡ ሊፈታን፡ ይቻላል፡ አለ፡ ማለታቸው፡ ባሰት፡ ነው፡ ገጽ፡ ፵፯ እንግዴህ፡ በመፍራት፡ ካህናትና፡ እጨጌ፡ ሃይማኖታቸውን፡ እንደካዱ፡ አቡንም፡ አይገባህም፡ እያሉ፡ በመፍራት፡ ካቈረቡ፡ ሁሉ፡ አሰተኞች፡ እንደሆኑ፡ ከእርሰ፡ ሊቃነ፡ ጳጳሳት፡ ሮማዊ፡ ተልከው፡ የመጡ፡ ክቡር፡ አባታችን፡ አቡነ፡ ያዕቆብ፡ ግን፡ እውነተኛ፡ እንደሆኑ፡ ለንጉሥና፡ ላገራችን፡ ሰው፡ ሁሉ፡ በግልጥ፡ ታየ። ይህነን፡ ሁሉ፡ እየሰሙ፡ እያወቁም፡ እንደ፡ ጲላጦስ፡ ጽድቅን፡ ባመጥ፡ ለወጡ። ደጃዝማች፡ | ውቤን፡ በሻሩ፡ ጊዜ፡ በትዕቢት፡ ምክንያት፡ የተናገሩትን፡ ረስተው፡ አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ በግፍ፡ ቀጡ። ሮማዊት፡ ቤተ፡ ክርስቲያንንም፡ ሰደቡ። ይህም፡ አመጥ፡ በእግዜር፡ ፊት፡ ቆመ። ጽድቁ፡ ግን፡ ዳኝነትዋን፡ አደረገችበት። | ሳኦል፡ ለመንግሥት፡ ከእግዜር፡ ተመረጠ፡ ነገሠም። ነገር፡ ግን፡ የነቢዩን፡ የሳሙኤልን፡ ልብስ፡ ስለ፡ ቀደደ፡ ሠጠጣ፡ ለመንግሥትከ፡ እንዳለው፡ ላጼ፡ ቴዎድሮስም፡ እንዲሁ፡ ሆነ። ከነገሡ፡ በኋላ፡ በደስታ፡ ፵ ቀን፡ ያህል፡ በስሜን፡ ነበሩ። አባቴ፡ ገብረ፡ ሚካኤልን፡ ካስገረፉ፡ በኋላ፡ በጥቂት፡ ቀን፡ ግን፡ እጅግ፡ የሚያሳዝናቸው፡ ወሬ፡ ከዋድላ፡ መጣባቼው። በዚያ፡ ዘመን፡ ወርቂት፡ የምትባል፡ ጋላ፡ እስላም፡ የወርሄመኖ፡ ገዢ፡ የዋድላን፡ አገር፡ ዘረፈች፡ ቤተ፡ ክርስቲያን ም፡ ተኰሰች። ንጉሥ፡ ከነገሡ፡ በኋላ፡ ወዲያው፡ እስላምም፡ በግድ፡ ወደ፡ ክርስትና፡ እንዲገባ፡ አዋጅ፡ አስነግ | ረው፡ ሥጋን፡ ማብላት፡ ማተብንም፡ ማሰር፡ ዠምረው፡ ነበሩ። የተነሣችበት፡ በዚህ፡ ምክንያት፡ ይመስለኛል። ደብራቸው፡ የተቃጠለችባቸው፡ ካህናት፡ መጥተው፡ ቢጮሁባቼው፡ በነገሡ፡ በሁለተኛው፡ ወር፡ ከስሜን፡ ተነሡ። በሰፈራቸውና፡ በታላላቅ፡ ገቢያም፡ አዋጅን፡ አስነገሩ። ቃሉም፡ ጋላ፡ ተነሥትዋልና፡ እንግዴህ፡ ክርስቲያን፡ የሆንህ፡ እርሱን፡ ለማጥፋት፡ ተከተለኝ፡ ማለት፡ ነበረ። ያቡንና፡ የእጨጌ፡ መቋምያ፡ ወምበርም፡ የያዙቱ፡ ካዋጅ፡ ነጋሪ፡ በኋላ፡ ይህ፡ ቃል፡ የመፍኋኔ፡ ዓለም፡ እግዝትነ፡ ማርያም፡ ነው። የሰው፡ አይዶለምና፡ ክርስቲያን፡ የሆንህ፡ ሁሉ፡ እንዳትቀር፡ ገዝተውሃል፡ አሉ። ከስሜን፡ ተሻግረው፡ አይብ፡ በዕንቅብ፡ በሚባል፡ በበጌምድር፡ እርስዋም፡ በደብረ፡ ታቦር፡ አጠገብ፡ ባለች፡ ሰፈሩ። በዚያም፡ ሳሉ፡ በስሜን፡ የተሾሙቱ፡ የደጃዝማች፡ መርሶ፡ ልጆች፡ ከደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ፈርተው፡ ሸሽተው፡ ወደርሳቸው፡ | መጡ። የጎዣሙ፡ ደጃዝማች፡ ተድላም፡ ካይብ፡ በዕንቅብ፡ አምልጠው፡ አገራቸውን፡ ገቡ፡ ያዙም። በፊትም፡ ለጠራኋቸው፡ ራስ፡ ኃይሉ፡ ሶስተኛ፡ ትውልድ፡ ናቸው። ስለዚህ፡ ባላገሩ፡ በደስታ፡ ተቀበላቸው። ሙሴ፡ ለዤአን፡ ባ፶ ኛ፡ ገጽ፡ ቴዎድሮስ፡ ከሾመው፡ ግብርንም፡ ከሰጠ፡ በኋላ፡ ተድላ፡ ጓሉ፡ ሸፈተ፡ ማለታቸው፡ ተሳስተዋል። አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ከሞቱ፡ በኋላ፡ ታመው፡ ባጋራቸው፡ ሞቱ። የደጃዝማች፡ ንጉሤም፡ ነገር፡ እንዲህ፡ ነው። አባታቸው፡ አገው፡ ወልደ፡ ሚካኤል፡ ሳህላንና፡ አበርገሌን፡ ሌላውንም፡ በዚያ፡ ወገን፡ ያለን፡ የነጋሪት፡ አገር፡ ገዢ፡ ነበሩ። ጀግና፡ ተዋጊ፡ ሰውም፡ ነበሩ። ደጃዝማች፡ ውቤም፡ የወይዘሮ፡ እኅቱ፡ የእታቸውን፡ ልጅ፡ አጋቡዋቼው። አሁን፡ ራስ፡ ከተባሉቱ፡ ከባልጋዳ፡ አርአያ፡ ጋራ፡ ተዋግተው፡ ሞቱ። ደጃዝማች፡ ውቤም፡ ልጅ፡ ንጉሤን፡ ባባታቸው፡ ፈንታ፡ ሾሙ። እንዳባታቸውም፡ በጀግንነት፡ ተጠሩ። ንጉሥና፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ ሲዋጉ፡ | እጃቸውን፡ ቈስለው፡ በፈረስ፡ አምልጠው፡ ወደ፡ ደርስጌ፡ ተማጠኑ። ንጉሥም፡ ምሬሃለኍ፡ ከዳንህ፡ በኋላ፡ ተከተለኝ፡ አሉዋቸው፡ ይላሉ። ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ግን፡ ንጉሤ፡ ካሳ፡ ታች፡ ነበረ፡ ስሙን፡ አላውቅም፡ እንጂ፡ የነጋሪት፡ አገር፡ ሹሞት፡ ነበረ፡ ማለታቸው፡ ተሳስተዋል፡ ገጽ፡ ፶፱ ከዚህ፡ በላይ፡ እንዳልኍ፡ ግን፡ ባይብ፡ በዕንቅብ፡ ሰፍረው፡ ሳሉ፡ ከደርስጌ፡ ወዳገራቼው፡ ወደ፡ ሳህላ፡ ወርደው፡ ንጉሥ፡ የሾሙት፡ በዚያ፡ የነበረውን፡ አባ፡ ታቦር፡ ጐሹን፡ መቱ። ከዚህም፡ በኋላ፡ የደጃዝማች፡ ውቤ፡ መኳንንት፡ የነበሩቱ፡ አንዱ፡ ወገን፡ ልጅ፡ ንጉሤ፡ የተባሉትን፡ የደጃዝማች፡ ውቤን፡ ልጅ፡ ባልጋ፡ አስቀመጡ። ሌላው፡ ወገን፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤን፡ ስለ፡ ወደደ፡ ልጅ፡ ንጉሤን፡ አውርደው፡ እርሳቸውን፡ አስቀመጡ። በእንጨት፡ ካብ፡ የነበሩ፡ በፊት፡ የጠራኋቸው፡ የደጃዝማች፡ መርሶ፡ ልጆች፡ ልጅ፡ ንጉሤ፡ መጣባችኍ፡ ቢሉዋቼው፡ ሸሹ። ነገር፡ | ግን፡ ኃይሌ፡ የምርጫ፡ ከንጉሥ፡ የተሾመ፡ ሰባት፡ መቶም፡ የሚሆን፡ ነፍጥ፡ የሰጡት፡ በጠለምት፡ ብርቱ፡ ሰው፡ ነበረ። እርሱንም፡ መቱት። ከዚህም፡ በኋላ፡ ከስሜን፡ ወደ፡ ደምቢያ፡ ሒደው፡ ባላምባራስ፡ ገልሞን ና፡ በዚያ፡ የነበሩትን፡ የንጉሥ፡ ምስለኔዮችን፡ መቱ። የደጃዝማች፡ ክንፉ፡ እርሳቸውም፡ ያጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ወንድም፡ ልጅ፡ ዳጃዝማች፡ መኰነንን፡ በዚያ፡ ሹመው፡ ተመለሱ። ነገር፡ ግን፡ መኰነን፡ በንጉሥ፡ ምስለኔ፡ ተመቱ። ዳጃዝማች፡ ውቤ፡ የገዙትን፡ ባማራ፡ አገር፡ እስከ፡ ጐንደር፡ ያለውን፡ አገር፡ ለርሳቸው፡ ተገዛ። ደጃዝማች፡ ተሰማ፡ ወንድማቸውን፡ በዚያ፡ ትተው፡ ወደ፡ ትግሬ፡ ተሻገሩ። ኃራኀር፡ በሚባል፡ በሐውዜን፡ አጠገብ፡ ካቶ፡ ኃይለ፡ ማርያም፡ አባ፡ ጐርፉ፡ የትግሬ፡ ምስለኔ፡ በብርቱ፡ ተዋጉ፡ ድል፡ አደረጉ፡ ገደሉ። ከዚህም፡ በኋላ፡ በሐማሴን፡ የነበሩቱን፡ ደጃዝማች፡ ኃይሉን፡ መቱ። ወገራ፡ ምላሽ፡ አማራ ና፡ ትግሬ፡ ለደጃዝ | ማች፡ ውቤ፡ እንደነበረች፡ እንዲሁም፡ ለርሳቸው፡ አምስት፡ ዓመት፡ ከስድስት፡ ወር፡ ተገዛች። |
chapter ()
Alignment Start a translation alignment with Alpheios Alignment. You can also add morphological annotations there. See instructions in GitHub.
Versions See parallel versions if any is available
Quotations Check for marked up quotations of a passage in this section
back to top
፮ ክፍል። | ከዚህ፡ በፊት፡ እንዳልኍ፡ ራስ፡ ኃይሉና፡ ታላቁ፡ ራስ፡ ዓሊ፡ አጼ፡ ተክለ፡ ጊዮርጊስን፡ ባፈራዋናት፡ መቱ። ከጌታችንም፡ ልደት፡ እስከ፡ እርስዎ፡ ድረስ፡ ፲፯፹፪ ዓመት፡ ካራት፡ ወር፡ ይሆናል። ከዚያም፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ እስኪነግሡ፡ ፻፴፫ ዓመት፡ ይሆናል። እንግዴህ፡ የፊተኞቹ፡ አባቶቻችን፡ ስንኳ፡ ቀምበርን፡ ቢያከብዱባቸው፡ ለእውነተኛው፡ ንጉሥ፡ ያልተገዙ፡ እኛ፡ ይልቅ፡ የገዦቹ፡ ልጆች፡ ስንሆን፡ እንዴት፡ ለቋረኛ፡ እንገዛለን፡ እርሱ፡ የማይገባው፡ ሲሆን፡ ንጉሥ፡ ነኝ፡ እንዳለ፡ እኔም፡ ለራሴ፡ እንደርሱ፡ እነግሣለኍ፡ ብሎ፡ በያገሩ፡ ሁሉ፡ ተነሣ፡ በጌምድር ና፡ ደምብያ፡ ብቻ፡ | ግን፡ እስከ፡ ጊዜው፡ ድረስ፡ ላጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ቀሩላቸው። ደጃዝማች፡ ውቤ፡ ራስ፡ ዓሊ፡ ሽፍታ፡ አልነበሩም። በግዛታቸውም፡ | የተቀመጠ፡ ይልቁንም፡ እንግዳ፡ ሰው፡ እንዲጠብቁት፡ ቢገናኛቸው፡ ደጅም፡ ቢጠናቸው፡ ዓመጠኛ፡ ሊባል፡ አይገባም። በትግሬ፡ ተቀምጦ፡ ሳለ፡ ግን፡ እርሳቸውን፡ ንቆ፡ ለራስ፡ ዓሊ፡ ቢገብር፡ ታላቅ፡ ዓመጥ፡ በሆነበት፡ ነበረ። እንዲህ፡ ከሆነ፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ሞንሰኘር፡ ደጃቆብን፡ ያጐታቸውን፡ የደጃዝማች፡ ውቤን፡ ግዛት፡ ከያዙቱ፡ ካገው፡ ንጉሤ፡ ጋራ፡ በመፋቀርዎ፡ መንቀፋቸው፡ በሚገባ፡ አይዶለም። ከዚህ፡ በፊት፡ እንዳልኍ፡ አባ፡ ጐርፉን፡ በሰኔ፡ ድል፡ አድርገው፡ ገድለውም፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ባድዋ፡ አጠገብ፡ ሰፈሩ። ከስሜን፡ ወደ፡ ትግሬ፡ በተሻገሩ፡ ጊዜ፡ አባታችንን፡ ቀድሞ፡ ከውጊ፡ በፊት፡ ያውቁ፡ ነበሩና፡ እንዴት፡ አሉ፡ አይርሱኝ፡ ብለው፡ ላኩ። ሞንሰኘር፡ ደጃቆብም፡ የፍቅር፡ ሰላምታን፡ ሊያደርሱ፡ አባቴ፡ እምነቱን፡ ሐላይ፡ ወደርሳቸው፡ ላኩ። እርሳቸውም፡ በፍቅር፡ ተቀበሉዋቼው። ስለ፡ ካቶሊካውያን፡ መጠበቅ፡ አዝዋችኍ፡ በያላችሁበት፡ ተቀመጡ፡ አሉ። ዳግመኛም፡ በ | ዚያ፡ ጊዜ፡ ከፍራንሳዊ፡ ንጉሥ፡ ጋራ፡ ያወዳጁኝ፡ የምትልን፡ መልእክት፡ ወዳባታችን፡ ሰደዱ። እርስዎም፡ ስለ፡ ላኩብኝ፡ ነገር፡ ምጽዋ፡ ካሉቱ፡ ከፈረንሳዊ፡ ኰንሱል፡ ጋራ፡ ተገናኝተው፡ ይጠይቁ፡ ብለው፡ መለሱ። ንጉሥ፡ ከሸዋ፡ ከተመለሱ፡ በኋላ፡ በዚያ፡ ክረምት፡ ሱባጋዲስ፡ ካሳን፡ ሹመው፡ ወደ፡ ትግሬ፡ ሰደዱ። ደጃዝማች፡ ውቤ፡ እርሳቸውን፡ ዓሥረው፡ በስሜን፡ አምባ፡ ፲፭ ዓመት፡ የሚያህል፡ አኑረዋቼው፡ ነበሩ። በድሉ፡ ጊዜ፡ ግን፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ አስፈቱዋቼው። ታሥረው፡ ሳሉ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብም፡ ጐልዓ፡ ሳሉ፡ ቍጥሩን፡ አላውቅም፡ እንጂ፡ ዓሥር፡ ብር፡ ይመስለኛል፡ ሰደውላቸው፡ ነበሩ። ባጋሜ፡ ለነበሩቱ፡ ወይዘሮ፡ ሐጐሳ፡ ለምሽታቸው፡ ለልጆቻቸውም፡ ተርበው፡ ነበሩና፡ እንደ፡ ችሎትዎ፡ ዘመድ፡ ሲሆንዋቸው፡ ነበሩ። ደጃዝማች፡ ካሳ፡ ግን፡ በዕሥራት፡ ሳሉ፡ የተደረገላቸውን፡ ረስተው፡ ተሹመው፡ ሲመጡ፡ አቡን፡ ነግረዋቸው፡ | ገዝተዋቸውም፡ ነበሩና፡ ባጋሜ፡ በዳበኵነይቶ፡ ባሉ፡ ካቶሊካውያን፡ ላይ፡ እጅግ፡ ጠላት፡ ሆኑ። በመስከረም፡ መዠመርያ፡ ቀን፡ ከሥጋዌ፡ በኋላም፡ ባ፲፰፵፰ኛ፡ ዓመት፡ ባንዲት፡ ሌሊት፡ በሰባት፡ አገር፡ ላይ፡ ጦርን፡ በደንገት፡ ሰደዱ። እዳ፡ በኵነይቶ፡ እንዴት፡ ካህናቶቻችን፡ አሳልፈን፡ እንሰጣለን፡ ብለው፡ ካቶ፡ ባርያሁ፡ ጋራ፡ ተዋግተው፡ ተይዘው፡ የነበሩትን፡ አባቴ፡ ተክለ፡ ጊዮርጊስን፡ አስጣሉ። ነገር፡ ግን፡ አሞዓስ፡ የሚባልን፡ ያቶ፡ ሀሊቦ፡ ልጅ፡ እጅግ፡ መልካም፡ ጐበዝ፡ በነፍጥ፡ ገደሉባቸው። ፯ት፡ የሚሆኑም፡ አቈሰሉባቼው። ስምንት፡ የሚሆኑም፡ ያገር፡ ዓይነተኞች፡ ዓሥረው፡ እስከ፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ አድረሱዋቼው። እስከ፡ ሶስት፡ ወር፡ አሠሩዋቸው። በሃይማኖታቸው፡ ጸንተው፡ አንክድም፡ አሉዋቼው። አገራቸው፡ ዳር፡ ነውና፡ ለክፉ፡ ቀን፡ መጠጊያ፡ ይሆናሉ፡ በማለት፡ ይመስለኛል፡ ፈትተው፡ ሰደዱዋቸው። |ጐልዓ ና፡ በሣዕሤዕ፡ ባሉቱ፡ ካቶሊካውያን፡ ግን፡ እጅ | ግ፡ ጨከኑባቼው። አንክድም፡ ብለው፡ የሸሹቱን፡ መከሩን፡ ላሙን፡ የቤታቸውንም፡ ገንዘብ፡ ሁሉ፡ ወሰዱባቸው። መከራው፡ ስለ፡ ጠናባቸው፡ ብዞች፡ ሰዎች፡ ሃይማኖታቸውን፡ ካዱ። ነገር፡ ግን፡ ሰማዕቱ፡ የምትባል፡ ዕድሜዋም፡ ፲፭ት፡ ዓመት፡ የሚሆን፡ አሽከር፡ እርስዋም፡ የካቶሊካዊ፡ ያቶ፡ ገላውዴዎስ፡ የልጅ፡ ልጅ፡ የምትሆን፡ ሃይማኖትዋን፡ ሊያስክዱ፡ በብዙ፡ ፈተና፡ አስጨነቁዋት። የፊጥኝ፡ ዓሥረው፡ አንጠለጠሉዋት። ገረፉዋትም። ከዚህ፡ በኋላ፡ ግን፡ ደጃዝማች፡ ጽናትዋን፡ አይተው፡ ሰፍረውበት፡ የነበረ፡ አምባ፡ ነበርና፡ በቈርበት፡ ጠቅልላችኍ፡ ወደ፡ ገደል፡ ጣሉዋት፡ ብለው፡ አዘዙ። በዚያ፡ ጊዜ፡ የሀበሩ፡ የካቶሊካውያን፡ ጠላት፡ መምር፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ ግን፡ አይጣሉዋት። እኔ፡ አስተምራታለኍ፡ እምቢ፡ ብትለኝም፡ እስካማራ፡ አገር፡ ወስጄ፡ ላቡን፡ እስጣታለ፡ ብለው፡ ወዳገራቸው፡ ወደ፡ ተምቤን፡ ወሰዱዋት። አልክድም፡ ስላ | ለች፡ በእግር፡ ብረት፡ ዓሥረው፡ ፈጭታን፡ አደረጉዋት። በዚያ፡ አገር፡ ያሉ፡ ያዩዋትና፡ ወሬዋንም፡ የሰሙ፡ እንዴት፡ ይህች፡ ትንሽ፡ አሽከር፡ ስለ፡ ሃይማኖት፡ ይህን፡ ያህል፡ መከራ፡ ትቀበላለች፡ እያሉ፡ ሲያደንቁ፡ ነበሩ። ከዚህ፡ በኋላ፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ቢመጡባቸው፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ ሸሽተው፡ ደብለሐን፡ ወደሚባል፡ አምባ፡ ገቡ። ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ደብዳቤን፡ አስይዘው፡ ያሽከሪቱን፡ ዘመዶች፡ ወደ፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ላኩ። በዚያ፡ ጊዜም፡ አባ፡ ዲራ፡ ብሩ፡ በተምቤን፡ ተሹመው፡ ነበሩ። ስለዚህ፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ እኒህ፡ ሁሌት፡ ሰዎች፡ ያሳዩትን፡ ሰው፡ ዓሥረህ፡ ስደድልኝ፡ ብለው፡ ቃላጤን፡ ሰጥተው፡ ወደ፡ እርሳቸው፡ ወደ፡ ተምቤን፡ ሰደዱዋቼው። ስለዚህ፡ አሽከሪቱን፡ የያዙ፡ መምር፡ ገብረ፡ ሚካኤል፡ እኒህን፡ አይተው፡ ተጨነቁ። ያቡን፡ መልእክተኛ፡ ነበሩና፡ የካቶሊካውያን፡ እኵሌታን፡ ገንዘብና፡ መከርን፡ ከደጃዝማች፡ ካሳ፡ ጋራ፡ የተካፈሉ፡ | ነበሩ። በዚህ፡ ጊዜ፡ ግን፡ አስታራቆችን፡ ይዘው፡ በቄስ፡ ገብረ፡ መድኅንና፡ በገብረ፡ ሕይወት፡ በቃላጤውም፡ እግር፡ ወድቀው፡ ለመኑ። ልጃችኍ፡ እንኋት፡ የወሰድሁትንም፡ ዕቃችኍ፡ እነሆ፡ እኔን፡ ግን፡ ወደ፡ ገጁ፡ አትወሰዱኝ፡ ብለው፡ ለመኑ። እነዚህም፡ የእውነተኛይቱ፡ ቸር፡ እናት፡ የቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ልጆች፡ ናቸውና፡ ምሕረት፡ አደረጉላቸው። አሽከሪቱንና፡ ጥቂት፡ የሰጡዋቸውን፡ ገንዘብ፡ ተቀብለው፡ በታላቅ፡ ደስታ፡ ተመለሱ። ከዚህም፡ በኋላ፡ ሸሽተው፡ የነበሩቱ፡ ካቶሊካውያን፡ በያገራቸው፡ እንዲገቡ፡ ርስታቸውንና፡ ቤተ፡ ክርስቲያናቸውንም፡ እንዲያገኙ፡ ከደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ትእዛዝ፡ ወጣ። እርሳቼው፡ ግን፡ ይህነን፡ በጕነት፡ ለካቶሊካውያን፡ ማድረጋቸው፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ በፊት፡ የሚያውቁዋቸው፡ ያጐታቸውም፡ የደጃዝማች፡ ውቤ፡ ወዳጅ፡ ስለ፡ ነበሩ፡ ነው። ይልቁን፡ ግን፡ ከወዲያ፡ አገር፡ ረዳትን፡ እንዲያገኙ፡ ነው። አባታችን፡ ግን፡ ለኮንሱል፡ | ነው፡ እንጂ፡ ለኔ፡ አይገባኝም፡ ስላሉዋቼው፡ በዚያ፡ ዘመን፡ በምጽዋ፡ ወደ፡ ነበሩ፡ ሙሴ፡ በይልያርድ፡ የፍራንሲያ፡ ኮንሱል፡ ላኩ። ኮንሱልም፡ እርስዎንና፡ ሠራዊተዎን፡ ማየት፡ ያስፈልገኛል፡ ብለው፡ ስለ፡ መለሱ፡ እሺ፡ ይምጡ፡ እኔም፡ መገናኘተዎን፡ እወዳለኍ፡ ብለው፡ መርገፍ፡ ኰረቻ፡ የተሸለመች፡ የነብረዒድ፡ ሣህሉ፡ በቅሎ፡ የነበረችን፡ ሰደዱላቼው። ስለዚህ፡ ኮንሱል፡ ከምጽዋ፡ ወደ፡ ሐላይ፡ ወጡ። ከሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ጋራ፡ ተገናኙ። አስተርጓሚ፡ እንዲሆኑዋቼው፡ አባቴ፡ እምነቱን፡ ካባታችን፡ ስለ፡ ለመኑ፡ ባንድ፡ ሔዱ። በዚያም፡ ዘመን፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ባድዋ፡ አጠገብ፡ ባለች፡ በጕልዓ ም፡ ሰፍረው፡ ነበሩ። በመስከረም፡ ፲፯ኛ፡ ቀን፡ በመስቀል፡ በዓል፡ በታላቅ፡ ክብር፡ ተቀበሉዋቸው። በግራና፡ በቀኝ፡ ወታደሩ፡ ተሰልፎ፡ ነጋሪቱም፡ ሲመታላቸው፡ ነበረ። መገናኘታቼውም፡ አባ፡ ጐርፉን፡ ከገደሉ፡ በኋላ፡ ባ፲፭ኛ፡ ወር፡ ከጌታችን፡ ልደትም፡ በኋላ፡ ባ፲፰፵፱ኛ፡ ዓመ | ት፡ ሆነ። ዳጃዝማች፡ በዚያ፡ ጊዜ፡ አምና፡ ልኬብዎ፡ ነበርኍ፡ የፈለግሁት፡ ረዳት፡ ዘገየብኝ፡ አሉ። ኮንሱልም፡ እስከ፡ ሁለት፡ ወር፡ ያሉ፡ ይመስለኛል። ምላሽ። አገኛለኍ፡ አሉ። ዳግመኛም፡ ኮንሱል፡ ሚሲዮንን፡ የሚያጠፋን፡ ነገር፡ ተናገሩ። ይህም፡ እንዲህ፡ ነው፡ ባለፈው፡ ዓመት፡ ስለ፡ ላኩብኝ፡ እኔም፡ የምስር፡ ንጉስ፡ ሰይድ፡ ባሻን፡ እርስዎን፡ ሊረዳ፡ እስከ፡ ከርቱም፡ መጥትዋል፡ ብዬ፡ ሌኬብዎ፡ ነበረ፡ ምነው፡ ያላኩበት፡ አሉ። አባቴ፡ እምነቱ፡ ግን፡ ይህስ፡ በስብከታችን፡ ላይ፡ መከራን፡ ያመጣብናልና፡ አላስተረጕምም፡ ብለው፡ እምቢ፡ አሉ። ኮንሱልና፡ እርሳቸው፡ በዚህ፡ ምክንያት፡ በደጃዝማች፡ ተጣሉ። ስለዚህም፡ ነገሩን፡ ሰምተውት፡ እኔን፡ ሊረዳ፡ ከመጣ፡ ምነው፡ እንኪያው፡ ሳትልክብኝ፡ ቀረህ፡ ብለው፡ መለሱ። እርሳቼውም፡ ወዳቡነ፡ ያዕቆብ፡ ሌኬ፡ አለኍ። አባቴ፡ እምነቱም፡ አሰት፡ ነው፡ አሉ። ሰይድ፡ ባሻ፡ ወደ፡ ከርቱም፡ መድረሱ፡ ለንጉሤ | መልካም፡ ይሆናል፡ የሚል፡ ወይም፡ ይህነን፡ የመሰለን፡ ወዳባታችን፡ ወሬን፡ ጽፈውለዎ፡ ነበሩ። ሰይድ፡ ባሻም፡ በዚያ፡ ዘመን፡ ወደ፡ ከርቱም፡ የመጣበት፡ ምክንያት፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ያባቶቼ፡ መንግሥት፡ ነውና፡ ስናርን፡ ልቀእ፡ አለዚያ፡ ሰፊ፡ ሜዳን፡ ይዘህ፡ ቈየኝ፡ ብለው፡ ልከውበት፡ ነው። ስለዚህ፡ እውነት፡ መስሎት፡ ስለ፡ ፈራ፡ በዘያ፡ ዘመን፡ ብትረክነት፡ በግብጾች፡ ተሹሞ፡ የነበረን፡ የበፊት፡ ስሙ፡ አባ፡ ዳውድ፡ አባ፡ ቄርሎስ፡ የተባለውን፡ ለዕርቅ፡ ሰዶ፡ ነበረ። ወደ፡ ደብረ፡ ታቦርም፡ መድረሱ፡ ከጌታችን፡ ልደት፡ በኋላ፡ ባ፲፰፵፰ ዓመት፡ በታኅሣሥ፡ ወር፡ ሆነ። ሰይድ፡ ባሻም፡ በኋላው፡ ተከትሎ፡ ወደ፡ ከርቱም፡ መጥቶ፡ ነበረ። ዳግመኛም፡ ሙሴ፡ በሊያርድ፡ መጥዋ፡ ሲነሡ፡ ለሐላዮች፡ የሚገባውን፡ ገንዘብ፡ አልሰጥም፡ ስላሱ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ እጅግ፡ አስጨነቁ። እንዲህ፡ ሆነ። በዚያ፡ ጊዜ፡ አባቍልቶችን፡ የሚገዛ፡ ባለ፡ ታላቅ፡ መርከብ፡ ከሞሪስ፡ ወደ፡ ምጽዋ፡ | መጣ። ከዚያም፡ ወደ፡ ሐላይ፡ ሲመጣ፡ ልማዱ፡ ነው፡ የናይብ፡ ሙሐመድ፡ ሎሌ፡ ከርሱ፡ ጋራ፡ መጥቶ፡ ከሚገዛው፡ በቅሎ፡ ቍጥር፡ አንዳንድ፡ ብርን፡ ወሰደ። ሽያጩ፡ አንድ፡ ብር፡ ገዢውም፡ አንድ፡ ብርን፡ ድላል፡ ለናይብና፡ ለባላገሮች፡ ይሰጣ። ቃብጣን፡ ባላገሮችን፡ በምጽዋ፡ ሊሰጣቸው፡ ይዝዋቸው፡ በወረዱ፡ ጊዜ፡ ሙሴ፡ በሊያርድ፡ እስላም፡ በክርስቲያን፡ አገር፡ ምናለውና፡ ድላልን፡ ወስዶ፡ ለንጉሤ፡ የሚገባውን፡ እርሱ፡ ከወሰደ፡ በርሳቸው፡ ክፋት፡ መውና፡ የሐላዮችን፡ አትስጥ፡ ለንጉሤ፡ እንድሰድለት፡ ለኔ፡ ስጠኝ፡ ብለው፡ ፵ ብር፡ ይመስለኛል፡ ወሰዱ። ባላገሮች፡ መጥተው፡ ገንዘባችነን፡ ቀማነ፡ ብለው፡ አስጨነቁዎ። ከዚህ፡ በፊት፡ እንዳልኍ፡ ሙሴ፡ ኮንሱል፡ ከምጥዋ፡ ወደ፡ ሐላይ፡ በመጡ፡ ጊዜ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ናይብ፡ የወትሮ፡ ልማዱን፡ አደረገ። አሁን፡ መከልከል፡ አይሆንም፡ ጊዜው፡ አይዶለም። ቢፈልጉም፡ ባለቤታቸው፡ ደጃዝማች፡ ይከ | ለክላሉ። አሁንስ፡ ለባላገሮች፡ የሚገባቼውን፡ ይሰጡዋቸው፡ ዘንድ፡ እለመንዎ፡ አለኍ፡ ብለው፡ ጸፉላቼው። በቤትዎ፡ ባንድ፡ ሳሉ፡ መናገራቸውን፡ ስለ፡ ፈሩ፡ ከሐላይ፡ ተነሥተው፡ ወደ፡ ማይዓርዳ፡ ሲደርሱ፡ ወረቀቱን፡ አስከተሉላቸው። እርሳቸው፡ ግን፡ አልሰጥም፡ ስላሉ፡ የሐላዮችን፡ መናወጥ፡ እንደ፡ በዛች፡ አይተው፡ አባታችን፡ ገንዘቡን፡ ከፈሉ። ነገር፡ ግን፡ ኮንሱል፡ በኋላ፡ ሰጡ። ዳግመኛም፡ ሙሴ፡ በሊያርድ፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ተገናኝተው፡ ሲመለሱ፡ የነፍጥ፡ መግዢ፡ እንዲሆን፡ ከመቶ፡ ብር፡ የበዛ፡ ከርሳቼው፡ ተቀብለው፡ ነበሩ። ከተመለሱም፡ በኋላ፡ በሁለተኛው፡ ወር፡ የወዳጅነት፡ ብለው፡ ሁለት፡ ሣፅን፡ ዓረቄና፡ ሌላም፡ ነገር፡ ሰደውላቸው፡ ነበሩ። በሁለተኛው፡ ዓመት፡ ግን፡ ከምጽዋ፡ በመስከረም፡ ወዳገራቸው፡ ሲነሡ፡ ወደ፡ ንጉሠ፡ ነገሥት፡ ኖጶልዮን፡ የሚልኩት፡ ሰው፡ ለባዊና፡ ታላቅ፡ ሰው፡ ከዘመዶችዎም፡ ወገን፡ እንዲሆን፡ ኧንድ፡ ነፍጥና፡ | አንድ፡ መነጠርም፡ ገዝቼ፡ ሰድጄልዎ፡ አለኍ፡ የቀረው፡ ግን፡ አምና፡ የሰደድሁለዎ፡ ቍጥሩ፡ ከዚህ፡ ጋራ፡ ነው፡ ብለው፡ ወደ፡ ደጃዝማች፡ ጻፉ። ይህነንም፡ ወረቀት፡ ገልብጠው፡ ከዚህ፡ ዕቃ፡ ጋራ፡ ይሰደዱላቸው፡ ብለው፡ ወደ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ሰደዱ። ክቡር፡ አባታችን፡ ግን፡ ለበረከት፡ ብሎ፡ አምና፡ የሰጡትን፡ ዛሬ፡ በቍጥር፡ ማግባት፡ ለፍራንሲያ፡ ለሁሉም፡ ኤውሮፓውያን፡ ስድብ፡ ይሆናል፡ ብለው፡ ከገንዘብዎ፡ ፴ የሚሆንን፡ ብር፡ ከኮንሱል፡ እንደመጣ፡ አስመስለው፡ ለደጃዝማች፡ ሰደዱ። ነገር፡ ግን፡ ከሌሎቹ፡ ኮናስሎች፡ ላባታችን፡ ሙሴ፡ በሊያርድ፡ ይሻሉ፡ የነበሩ፡ ይመስለኛል። ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ሙሴ፡ በሊያርድን፡ ንጉሤ፡ ጋራ፡ በድግሣ፡ ተገናኘ፡ ማለታቸው፡ ተሳስተው፡ ነው፡ ገጽ፡ ፺። | ባ፲፰፶፩ኛ፡ ዓመተ፡ ሥጋዌ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ጋራ፡ በድግሣ፡ ባጠገብ፡ በሰፈሩ፡ | ጊዜ፡ ተገናኙ። ከዚህ፡ በኋላ፡ ከዚያ፡ ገሥግሠው፡ ባንድ፡ ቀን፡ ወደ፡ ጸዓድዜጋ፡ ደርሰው፡ ደጃዝማች፡ ኃይሉን፡ መቱ። ከዚህም፡ በኋላ፡ በዚያው፡ ወራት፡ ኮንሱል፡ በልያርድም፡ ምጽዋ፡ ከተነሡ፡ በኋላ፡ በሁለተኛው፡ ወር፡ ወደ፡ ንጉሠ፡ ነገሥት፡ ናጶልዮን፡ የላኩትን፡ ልጅ፡ ጣቃዬን፡ ከሚወስደው፡ በረከት፡ ጋራ፡ እስከ፡ ሐላይ፡ ሰደዱት። ወደ፡ ሮም፡ ርእሰ፡ ሊቃነ፡ ጳጳሳትና፡ ወደ፡ የነገሥታት፡ ንጉሥ፡ ናጶልዮን፡ የሚደርሱትን፡ መልእክቶች፡ አርመው፡ እንደሚገባ፡ አጽፈው፡ ይስደዱልኝ፡ ብለው፡ ወዳባታችን፡ ጻፉ። ነገር፡ ግን፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ በዚያ፡ ጊዜ፡ ከሐላይ፡ ወደ፡ ምንኵሉ፡ ወርደው፡ ነበሩና፡ መልእክተኛውና፡ አባቴ፡ እምነቱ፡ ወደርስዎ፡ ወረዱ። ባለፈው፡ ዓመት፡ አባቴ፡ እምነቱን፡ ከመልእክተኛዎ፡ ጋራ፡ እንዲሔዱላቸው፡ አባታችነን፡ ለምነው፡ ነበሩና፡ እርስዎም፡ ሳይወዱ፡ እሺ፡ ብለው፡ ነበሩና፡ ልጅ፡ ጣቃዬና፡ እርሳቼው፡ ሙሴ፡ ላፕሩስ፡ | የሚባሉም፡ ፈረንሳዊ፡ በዚኸው፡ ዓመት፡ በኅዳር፡ ከምጽዋ፡ በእስላም፡ ጀልባ፡ ተጫኑ። አባቴ፡ እምነቱ፡ ዓረቢኛ፡ ብቻ፡ ያውቃሉ። ሙሴ፡ ላፕሩስ፡ እጅግ፡ ጥቂት፡ ትግርኛ፡ ቋንቋ፡ ያውቁ፡ ነበሩና፡ እንዲያስተረጉሙላቸው፡ እርሳቸውን፡ ጨመሩ። ሙሴ፡ ለዤአን፡ ግን፡ እርሳቼውን፡ ከምሲዮነር፡ አንድ፡ የኢጣልያ፡ ቄስ፡ እርሱ፡ ነበሩ፡ ማለታቸው፡ ተሳስተው፡ ነው። ወደ፡ ሮም፡ ከደረሱ፡ በኋላ፡ ግን፡ ወደ፡ ፓሪስ፡ ሲነሡ፡ በርሳቸው፡ ፈንታ፡ ሙሴ፡ ሳፔቶ፡ አስተርጓሚያቸው፡ ሆኑ። ስለ፡ መልእክተኞቹ፡ ከዚህ፡ በኋላ፡ የሆነው፡ ነገር፡ ግን፡ በሌላው፡ ተጽፎዋል። | ደጃዝማችም፡ ለፍራንሲያ፡ ንጉሥ፡ በሰደዱቱ፡ በረከት፡ አንዱ፡ መጣምር፡ ኰረቻ፡ ነበረ። ንጉሥ፡ በፊት፡ እንዳልኍ፡ በስሜን፡ ነግሠው፡ በዚያው፡ ሳሉ፡ ባድዋ፡ የነበሩትን፡ አንጠርኞች፡ ወደርሳቸው፡ አስጠርተው፡ ነበሩ። ለሶስቱ፡ አንጠረኞች፡ ሶስት፡ መጣ | ምር፡ ኰረቻን፡ እንዲሠሩ፡ ዓራት፡ ፻፶ ብርን፡ ሰጥተዋቼው፡ ወደ፡ ጋላ፡ ዘመቱ። ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ግን፡ በፊት፡ እንዳልሁ፡ ደጃዝማች፡ ውቤ፡ ይገዙት፡ የነበረን፡ አገር፡ ሁሉ፡ ገዢ፡ በሆኑ፡ ጊዜ፡ አንጠረኞቹን፡ አስጠርተው፡ በናንተ፡ ዘንድ፡ ያለን፡ ብር፡ ለኔ፡ ይገባኛልና፡ ኰረቻውን፡ ሥሩ፡ አሉዋቼው። እነዚያም፡ እሺ፡ እንሠራለን። ነገርግን፡ መቅቢያውን፡ ወርቅ፡ አልተቀበልነም፡ ቢሉዋቸው፡ መሽከሽ፡ የሚባልን፡ ወርቅ፡ አስተዝተው፡ ሰጡዋቸው። እነዚያም፡ ሠርተው፡ አመጡላቸው። አንዱን፡ ለፍራንሲያ፡ ንጉሥ፡ ሰደዱ። ሙሴ፡ ሌዤአን፡ | ግን፡ ቴዎድሮስ፡ ፍራንሲያ፡ ጋራ፡ የቀናን፡ ወዳጅነት፡ አስቦ፡ ከላይኛውም፡ ጌታ፡ ወደ፡ ላይኛው፡ ጌታ፡ ናጶልዮን፡ የሚገባ፡ በረከት፡ እንድትሆንለት፡ ብሎ፡ ኮከብና፡ ወርቁ፡ የሚባሉትን፡ ያድዋን፡ አንጠረኞች፡ ያነን፡ ኰረቻን፡ ሥሩ፡ አላቸው። ይህች፡ ግን፡ ኰረቻ፡ በትግሬ፡ ሽፍታ፡ ተነጠቀች። ንጉሤ፡ ብላታ፡ ደስታ፡ የሚ | ባልን፡ ያድዋን፡ ሹም፡ ሰዶ፡ ገዳምን፡ አሰብሮ፡ አስወስዶ፡ በሙሴ፡ ደዢቆብ፡ ዘንድ፡ አደራን፡ አስቀመጣት። የንጉሤ፡ መልእክተኞች፡ ወደ፡ ፓሪስ፡ ደርሰው፡ በርስዋ፡ ብቻ፡ ብዙ፡ ታሪክ፡ ያለን፡ ይህችንን፡ የተሸለመችን፡ ኰረቻ፡ በረከትን፡ አቀረቡ፡ ይላሉ። በገጽ፡ ፺፫፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ በፊት፡ እንዳየነ፡ ባቡነ፡ ሰላማ፡ ምክንያት፡ ከእንግሊዝ፡ መንግሥት፡ ጋራ፡ መወዳጅትን፡ ፈለጉ፡ እንጂ፡ ከፍራንሲያ፡ ጋራ፡ እንዳልፈለጉ፡ የታወቀ፡ ነው። ከነዚያ፡ ጋራ፡ ከተጣሉ፡ በኋላ፡ ግን፡ ፈልገው፡ እንደሆነ፡ እንጃ። ይህነን፡ ገንዘብ፡ ግን፡ እንዲሠሩ፡ ላንጠረኞች፡ የሰጡ፡ መዠመርያ፡ ጊዜ፡ ከኮንሱል፡ ፕሎውደን፡ ተገናኝተው፡ ወደ፡ ጋላ ና፡ ወደ፡ ሸዋ፡ ዘመቻ፡ ሲነሡ፡ ነውና፡ ይልቅስ፡ ወደ፡ ሎንዶን፡ ሊሰዱ፡ የፈለጉ፡ ይመስላል። ዳግመኛም፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ባለቤታቸው፡ አቡነ፡ ሰላማን፡ ያሾመ፡ በምስር፡ የነበረ፡ የእንግሊዝ፡ ኮንሱል፡ ነው፡ የሊኤደ | ርም፡ ደቀ፡ መዝሙር፡ ነበረና ሃይማኖቴም፡ ፕሮትስታንቲ፡ ነው፡ ብለው፡ ጽፈዋል። እንዳሉትም፡ በዚያ፡ ጊዜ፡ አቡንና፡ ንጉሥ፡ የእንግሊዝ፡ ኮንሱልም፡ በፍቅር፡ እንዳንዲት፡ ነፍስ፡ እንደ፡ ነበሩ፡ በሁሉ፡ አገር፡ የተገለጠ፡ ነገር፡ ነው። እንዲህ፡ ከሆነ፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ቴዎድሮስ፡ ፍራንሲያ፡ ጋራ፡ ወዳጅነትን፡ ፈልጎ፡ ያሠራው፡ ነው፡ ማለት፡ የማይጋጠም፡ ነገር፡ ነውና፡ ወይ፡ የነገራቸው፡ ወይም፡ ባለቤታቸው፡ ተሳስትዋል። ሁለተኛም፡ በትግሬ፡ ሽፍታ፡ ተነጠቀች፡ ማለታቸው፡ ዓለም፡ ሁሉ፡ ከሚያውቀውና፡ በመጻፋቸውም፡ ከጻፉት፡ ታሪክ፡ ጋራ፡ አይጋጠምም። ኋላ፡ አጼ፡ ቴዎድሮስ፡ የተባሉቱ፡ ልጅ፡ ካሳ፡ እቴጌ፡ መነን፡ ሎሌ፡ ነበሩ። የልጃቸውንም፡ የራስ፡ አሊን፡ ልጅ፡ አጋብተዋቸው፡ ሳሉ፡ ሸፍተው፡ ወጉዋቸው። አሠሩዋቸውም። ኋላም፡ ታርቀው፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ ተብለው፡ ማሩ፡ ቀመስን፡ እየገዙ፡ ብዙ፡ ዘመን፡ የራስ፡ ዓሊ፡ ሎሌ፡ ነበሩ። ኋላ፡ | ግን፡ ከርሳቸውም፡ ሸፍተው፡ ወጉዋቸው። ድልም፡ አድርገው፡ ለጌታቼው፡ የነበረን፡ ሁሉ፡ ወረሱ። ደጃዝማች፡ ውቤንም፡ ወግተው፡ ድል፡ አድርገው፡ በምድርም፡ ባምባም፡ የነበረን፡ ነፍጥንና፡ ገንዘብንም፡ ሁሉ፡ ወሰዱ። ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ይህስ፡ አሸንፎ፡ መውሰድ፡ ሌብነት፡ አይባልም፡ ቢሉ፡ ግን፡ ይልቅ፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ ያባቴን፡ የውቤን፡ መንግሥት፡ ለሌላ፡ አልሰጥም፡ ብለው፡ ወዲያው፡ በጠላት፡ ላይ፡ የተነሡ፡ ስምንት፡ ጊዜ፡ የሚሆንን፡ ድል፡ አድርገው፡ ከጐንደር፡ ዳርቻ፡ አንስቶ፡ እስከ፡ ሐማሴን፡ ዳርቻ፡ ድረስ፡ ስድስት፡ ዓመት፡ የገዙት፡ ከሆኑ፡ ያች፡ ኰረቻ፡ በትግሬ፡ ሽፍታ፡ የተነጠቀች፡ ናት፡ እንዴት፡ ይገባል። ዳግመኛም፡ ዳጃዝማች፡ ንጉሤ፡ እንደ፡ ልጅ፡ ካሳ፡ ወይም፡ እንደ፡ ደጃዝማች፡ ካሳ፡ ያጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ሹምና፡ ሎሌ፡ በሁሉ፡ ኢትዮጵያ፡ የታወቀ፡ ነው። ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ግን፡ ንጉሤ፡ | ቴዎድሮስ፡ የነጋሪት፡ አገር፡ ተሹሞ፡ ነበረ፡ ማለታቸው፡ ከረዢም፡ ተራራ፡ የበለጠ፡ ውሸት፡ ነው። እንደዚህም፡ ደግሞ፡ የተካከለ፡ ሁለተኛ፡ አሰት፡ ተራራ፡ ብላታ፡ ደስታ፡ ገዳሙን፡ ሰብሮ፡ ኰረቻውን፡ በሙሴ፡ ደዢቆብ፡ ቤት፡ አኖረው፡ ማለታቼው፡ ነው። ይህም፡ ሊታወቅ፡ በዚያ፡ ዘመን፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ባድዋ፡ እንዳልነበሩ፡ በዚያም፡ ቤት፡ እንዳልነበረዎ፡ የታወቀ፡ ነው። ከዚያም፡ እስከ፡ ነበሩባት፡ እስከ፡ ሐላይ፡ የሁለት፡ ቀን፡ ተኩል፡ መንገድ፡ ይሆናል። ደጃዝማች፡ ንጉሤም፡ ኰረቻውም፡ ካንጠረኞች፡ በተቀበሉባት፡ ዓመት፡ ማይ፡ ሰገሞ፡ በምትባል፡ ባድዋ፡ አጠገብ፡ ሰፍረው፡ እንደነበሩ፡ የታወቀ፡ ነው። ብላታ፡ ደስታ፡ ዓይነተኛ፡ ሹም፡ ስለ፡ ሆኑ፡ ኰረቻይቱን፡ ይዘው፡ ካድዋ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ እስካሉባት፡ ሐላይ፡ ድረስ፡ ሲመጡ፡ ሰው፡ ባያቸው፡ ነበረ። ነገር፡ ግን፡ በፍራንሲያ፡ ከነበሩቱ፡ ከሙሴ፡ ሌዤአን፡ በቀር፡ ያየና፡ የሰማ፡ የለም። ከተቀበ | ልዋት፡ ግን፡ በኋላ፡ በስድስተኛው፡ ወር፡ በጥቅምት፡ ከዚህ፡ በፊትም፡ እንዳልኍ፡ ደጃዝማች፡ ኃይሉን፡ ከሻሩ፡ በኋላ፡ መልእልተኛቸው፡ ልጅ፡ ጣቃዬን፡ አስይዘው፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ በዚያ፡ ያሉ፡ መስሎዎ፡ እስከ፡ ሐላይ፡ መስደድዎ፡ ከዚያም፡ አባቴ፡ እምነቱ፡ መርተውት፡ አባታችን፡ እስካሉበት፡ እስከ፡ ምንኵሉ፡ እንደ፡ ወረደ፡ ከዚህም፡ ወዲያ፡ አገር፡ ሊሔዱ፡ በመርከብ፡ እንደ፡ ተጫኑ፡ እውነት፡ ነው። ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ግን፡ | የመንግሥት፡ ገንዘብ፡ ለንጉሥ፡ ነውና፡ ኰረቻውስ፡ ብሻው፡ የንጉሤ፡ ይሁን፡ ሙሴ፡ ደዢቆብ፡ የሽፍታን፡ አስተርጓሚ፡ ሊሆን፡ ስለምን፡ አባ፡ እምነቱን፡ ሰደደ፡ ቢሉ። ሽፍታ፡ እንዳልሆኑ፡ ከዚህ፡ በፊት፡ የተገለጠን፡ ማስረጃ፡ ሰጥቻለኍ። በዚያ፡ ዘመን፡ ባገራችን፡ ሌሎች፡ የኤውሮፓም፡ ሰዎች፡ ነበሩ፡ እንጂ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ብቻ፡ አልነበሩም። በዚያ፡ ዘመን፡ የኢትዮጵያ፡ አነዋወር፡ ወዳገራቸው፡ ጽፈው፡ | ነበሩ። ይልቁንም፡ በፊት፡ የጠራኋቸው፡ የፍራንሲያ፡ ኮንሱል፡ በሊያርድ፤ ንጉሤ፡ መልእክተኞችን፡ ወደርስዎ፡ ሊሰድ፡ ነው፡ ብለው፡ ወደ፡ ንጉሣቼው፡ ልከው፡ ነበሩ። ዳግመኛም፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ያገሩ፡ ገዢ፡ ካቶሊክን፡ ይወዳል፡ በግዛቱ፡ ሁሉ፡ እናስተምር፡ ነጻነትን፡ ሰጥቶናል። ዳግመኛም፡ በቀኝ፡ ቢያቆመኝ፡ ከቅድስት፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፡ ሮማዊት፡ ጋራ፡ በሃይማኖት፡ አንድ፡ እሆናለኍ፡ ብልዋል፡ መልእክተኞችንም፡ ሊሰድ፡ ነው፡ ብለው፡ አስቀድመው፡ ለከርዲናል፡ ባርናቦ፡ የፕሮታጋንዳ፡ አለቃ፡ ጽፈው፡ እሺ፡ ይምጡ፡ የምትልንም፡ ምላሽ፡ ተቀብለው፡ ነበሩ። ስለዚህም፡ መልእክተኞች፡ ወደዚያ፡ በደረሱ፡ ጊዜ፡ በመልካም፡ በታላቅ፡ ፍቅር፡ ተቀበሉዋቸው። ከብፁዕ፡ አባታችን፡ በስም፡ ዘጠነኛ፡ ፒዮስም፡ ብዙ፡ ሞገስን፡ አግኝተው፡ ወደ፡ ፓሪስ፡ ባለፉም፡ ጊዜ፡ ከንጉሠ፡ ነገሥት፡ ናጶልዮን፡ ብዙ፡ ፍቅር፡ አገኙ። ስለዚህም፡ ኮማንዳ፡ ደጃዝማች፡ ማለት፡ ይመስለኛል፡ | ሩሴልን፡ ወደ፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ እንደ፡ ላኩ፡ የታወቀ፡ ታሪክ፡ ነው። እንግዴህ፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ አስተርጓሚን፡ በመስደድዎ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ ከነቀፉ፡ የሮም፡ ርእሰ፡ ሊቃነ፡ ጳጳሳትን፡ መስደባቸው፡ ነው። ነገር፡ ግን፡ ከዚህ፡ በፊት፡ እንዳየነ፡ ሃይማኖታቸውን፡ ለጠየቃቸው፡ ሰው፡ ሁሉም፡ ቢሆን፡ ግድ፡ የለኝም፡ ብለዋልና፡ የጌታችን፡ የየሱስ፡ ክርስቶስን፡ ምስሌነን፡ መስደባቸው፡ በርሳቼው፡ ዘንድ፡ አይደነቅም። ስንኳንስ፡ መስደብ፡ እንደርሳቸው፡ ያሉ፡ ወገኖቻቸው፡ መግደሉን፡ እንዲፈልጉ፡ የታወቀ፡ ነው። ንጉሠ፡ ነገሥት፡ ናጶልዮንን፡ ግን፡ ጌታቸው፡ ናቸውና፡ ሊነቅፉ፡ ይደፍሩ፡ አይመስለኝም። ነገር፡ ግን፡ እርሳቸው፡ ሽፍታ፡ ነው፡ ወደሚሉት፡ ኮማንዳ፡ ሩሴልን፡ ከሰደዱ፡ ንጉሣቸውንም፡ እንደ፡ ሰደቡ፡ ይታያል። | ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ግን፡ የሙሴ፡ ሌዤአን፡ ነቀፋ፡ ፈርተው፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ የለመኑዋቸውን፡ አስተር | ጓሚን፡ ባይሰጡ፡ ከርሳቸው፡ ጋራ፡ መጣላት፡ ግድ፡ ሊመጣ፡ ነበረ። ከተጣሉም፡ በካቶሊካውያን፡ ላይ፡ ክፉ፡ ነገር፡ ሊያደርጉ፡ ካገራቸውም፡ ሊያባርሩ፡ ይችሉ፡ ነበር። ሙሴ፡ ሌዤአንም፡ ሙሴ፡ ደዢቆብ፡ ይህነን፡ ነገር፡ አይሆንልኝም፡ ብሎ፡ እንዴት፡ ስብከትን፡ አጠፋ፡ ባሉ፡ ነበረ። ይልቁንም፡ ደጃዝማች፡ ንጉሤ፡ መኳንንቶቻቸው፡ ባይክዱዋቸው፡ ካጼ፡ ቴዎድሮስ፡ ጋራ፡ ሊዋጉ፡ ቈርጠው፡ ነበሩና፡ | ተዋግተው፡ ድል፡ አድርገው፡ ቢሆኑ፡ ቀድሞ፡ አይሆንም፡ ብለሁኛል፡ ብለው፡ ወደ፡ እንግሊዝ፡ ንግሥት፡ ልከው፡ ቢሆኑ፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብን፡ ለመስደብ፡ ባለም፡ ሁሉ፡ ያለወረቀትና፡ ቀለም፡ ለሙሴ፡ ሌዤአን፡ ባልበቃም፡ ነበር፡ ይመስለኛል፡ ዳግመኛም፡ በወዲያ፡ አገር፡ ይልቁን፡ እንደ፡ ፈረንሳውያን፡ ልማድ፡ ስንኳንስ፡ ጳጳሱን፡ ዝቅ፡ ያለን፡ ታናሹን፡ ሰውስንኳ፡ አንተ፡ ብለው፡ አይጠሩም። ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ግን፡ በልባቸው፡ ያለ | ችን፡ ጠብና፡ ንቀት፡ ለመግለጥ፡ በመጻፋቸው፡ ክፍል፡ ሁሉ፡ ሙሴ፡ ደዢቆብ፡ ከማለት፡ በቀር፡ ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ማለት፡ አልተገኘም። ነገር፡ ግን፡ እርስዎን፡ መጥላታቼው፡ በሚገባዎ፡ ስምም፡ አለመጥራታቸው፡ የካቶሊክ፡ ወገን፡ አለመሆናቼውን፡ ለመግለጥ፡ ነው። ዳግመኛም፡ በመቶ፡ ፪ኛ፡ ገጽ፡ ለሁሉ፡ ሁከት፡ ነፍስ፡ የነበረ፡ የማይታዘዝ፡ ጳጳስ፡ ለትግሬ፡ ሁከት፤ እውነተኛ፡ አለቃው፡ በዚያ፡ ዓመት፡ ጠፋበት። የጥበብ፡ ሰዎች፡ ሙሴ፡ ደዢቆብን፡ በዕድሜውና፡ በድካሞቹ፡ ለየከበደች፡ የጣይ፡ ትኩሳት፡ ፍሪዳ፡ ሁኖ፡ በምጽዋ፡ አጠገብ፡ ሞተ፡ ይላሉ። ነገር፡ ግን፡ የመራራትን፡ ስምምነት፡ ለዚህ፡ ለከበረ፡ ሰው፡ | መንሣት፡ አይቻልም። ለአእምሮና፡ ደግሞ፡ ለከበሩ፡ ኃይላት፡ ጠላት፡ በምትሆን፡ በፈጸማት፡ ትግል፡ ከታላቂቱ፡ ጥበብ፡ በቀር፡ ስለ፡ ቤተ፡ ክርስቲያን፤ ወመለዱ፡ ያነሰ፡ ነው፡ አሉ። | ምላሽ። ሞንሰኘር፡ ደዢቆብ፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ እንደ፡ ጻፉት፡ ነፍስ፡ ለሥጋ፡ ሕይወት፡ እንደሆነች፡ እርስዎም፡ ለሁሉ፡ ሁከት፡ አንቀሳቀሽ፡ ከሆኑ፡ ለትግሬ፡ ሁከትም፡ ወይም፡ ሽግታ፡ ዓይነተኛ፡ አለቃው፡ ከነበሩ፡ የኢትዮጵያ፡ ሰው፡ ሁሉ፡ አቡነ፡ ያዕቆብ፡ እጅግ፡ መልካም፡ ሰው፡ ነበሩ፡ እያለ፡ ማመስገኑ፡ እንግዴህ፡ ተሳስቶ፡ ነው። ነገር፡ ግን፡ ቅን፡ ልቡና፡ ያለው፡ ሰው፡ በዚህ፡ ነገር፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ አንድ፡ ሰው፡ እንደ፡ ተሳሰቱ፡ ያያል፡ እንጂ፡ ያገር፡ ሁሉ፡ ሰው፡ ተሳስቶ፡ ይልም፡ አይመስለኝም። በሁሉ፡ ኢትዮጵያን፡ የተመሰገኑ፡ መሆናቸውን፡ ሙሴ፡ ሌዤአን፡ ባለቤታቸው፡ በ፵ኛ፡ ገጽ፡ እስላሞቹስንኳ፡ ሳይቀሩ፡ ያመሰግኑታል። ዛሬ፡ ቅሉ፡ ቅዱስ፡ ያዕቆብ፡ ከማ | ለት፡ በቀር፡ በሌላ፡ አይጠሩትም፡ ብለዋል። | አነ፡ ካህን፡ ተክለ፡ ሃይማኖት፡ ወልዱ፡ ለካህን፡ ተክለ፡ እግዚእ፡ ዘማርያም፡ ሠዊቶ፡ እንተ፡ ሀገረ፡ ምምሳሕ፡ ጸሐፍኩ፡ ዛተ፡ ንስቲተ፡ መጽሐፈ፡ ፩ ለአኅጕሎተ፡ ሐሰት፡ ዘተነግረት፡ በላዕለ፡ ጻድቅ፡ አቡነ፡ ያዕቆብ፡ ህየንተ፡ ሐዋርያ፡ ዘኢትዮጵያ። ዘፈነዎ፡ ጎርጎርዮስ፡ በስም፡ ፲ወ፮ስ፡ ርእሰ፡ ሊቃነ፡ ጳጳሳት፡ ዘሮም፡ ለሰቢከ፡ ወንጌል፡ እግዚእነ፡ የ፡ ክ፡ በ፲፰፴፩ ዓመተ፡ ምሕረት።

Text visualization help

Page breaks are indicated with a line and the number of the page break. Column breaks are indicated with a pipe (|) followed by the name of the column.

In the text navigation bar:

  • References are relative to the current level of the view. If you want to see further navigation levels, please click the arrow to open in another page.
  • Each reference available for the current view can be clicked to scroll to that point. alternatively you can view the section clicking on the arrow.
  • Using an hyphen between references, like LIT3122Galaw.1-2 you can get a view of these two sections only
  • Clicking on an index will call the list of relevant annotated entities and print a parallel navigation aid. This is not limited to the context but always refers to the entire text. Also these references can either be clicked if the text is present in the context or can be opened clicking on the arrow, to see them in another page.

In the text:

  • Click on ↗ to see the related items in Pelagios.
  • Click on to see the which entities within Beta maṣāḥǝft point to this identifier.
  • [!] contains additional information related to uncertainties in the encoding.
  • Superscript digits refer to notes in the apparatus which are displayed on the right.
  • to return to the top of the page, please use the back to top button
Daria Elagina

Catalogue Bibliography

  • Platonov, V. 1996. Efiopskie rukopisi v sobranijakh Sankt-Peterburga: Katalog (St Petersburg: The Russian National Library Press, 1996). page 16

Secondary Bibliography

  • Platonov, V. 2017. Rukopisnaja kniga v traditsionnoj kulture Efiopii, ed. E. Gusarova (Sankt-Peterburg: Rossijskaja natsional’naja biblioteka, 2017). page 192

  • Platonov, V. M. and S. B. Černecov 2002. ‘“Kniga uničtoženija lži, vozvedënnoj na pravednogo Abunu Iakova” Takla Hajmanota Takla Egzie - odno iz pervyh proizvedenij amharskoj literatury’, Hristianskij Vostok, 3/9 (2002), 172–268.

  • Gusarova, E. 2018. ‘Efiopskij fond’, in I. Popova, ed., Asiatic Museum - Institute of Oriental Manuscripts, RAS: Collections and Personalia. Aziatskij Muzej - Institut vostočnyh rukopisej RAN: putevoditel’, (1st ed.) (Moscow: Vostochnaya Literatura, 2018), 164–183. page 172-173

Daria Elagina
This page contains RDFa. RDF+XML graph of this resource. Alternate representations available via VoID.
Hypothes.is public annotations pointing here

Use the tag BetMas:IVEf27 in your public hypothes.is annotations which refer to this entity.

CLOSE

Suggested citation of this record

Alessandro Bausi, Daria Elagina, ʻSaint Petersburg, Institut Vostočnyh Rukopisej Rossijskoj Akademii Nauk, IV Ef. 27ʼ, in Die Schriftkultur des christlichen Äthiopiens und Eritreas: Eine multimediale Forschungsumgebung / Beta maṣāḥǝft (Last Modified: 2019-12-11) https://betamasaheft.eu/manuscripts/IVEf27 [Accessed: 2024-06-14]

To cite a precise version, please, click on load permalinks and to the desired version (see documentation on permalinks), then import the metadata or copy the below, with the correct link.

CLOSE

Revision history

  • Daria Elagina Added text transcription with encoding, added bibliographical reference. on 11.12.2019
  • Daria Elagina Small changes on 29.4.2019
  • Daria Elagina Checked the manuscript in IVR, added description. on 22.4.2019
  • Daria Elagina Created entity, added physical description and content. on 15.3.2019
CLOSE

Attribution of the content

Alessandro Bausi, general editor

Daria Elagina, editor

This file is licensed under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0.